በእግዚአብሔር
ፍቃድና ቸርነት ከኢ-አማኝነት (athiest) ወደ አማኝነት የተመለሰ አንድ ሚስኪን ደካማና ኃጥያተኛ ኢትዮጵያዊ ሰው ነው!
ኢትዮጵያ ትግራይ ክፍለ ሀገር የተወለደ እንደማንኛዉም ሰው በሕይወቱ መንገድ ጥሩም መጥፎም ገጽታ የተመለከተና ያሳለፈ በማሳለፍ ያለ ነው። እግዚአብሔርን ባለማወቅና ባለማምለክ ያሳለፋቸው ዓመታት (ጊዜያት) በሕይወቱ ውስጥ እንደከሰረበት የሚያምን ቢሆንም እግዚአብሔር ሁሉ ነገር ለምክንያትና በምክንያት ስለሚሰራ ይህንን በማመን ይጽናናል።
ነገሮች ለመረዳትና ለማወቅ ባለው ከፍተኛ ጉጉትና ተነሳሽነት ዓለማዊው የፍልስፍና የክህደት መጻሕፍት በሕይወቱ ውስጥ አሉታዊ ተጽዕኖ በመፍጠሩ እግዚአብሔር የለሽ (ህልወተ እግዚአብሔር የካደ) ሕይወቱ እንዲመራና በተለያዩ አሰናካይ ሱሶች ማለትም ትምባሆ፣ ማሪዋናና (ካናቢስ) ጫት በመታሰር በጨለማ ውስጥ እንዲኖር ሆኖ ነበር።
ኢሉሚናቲ - ስለ ኢሉሚናቲ ለማወቅ ዓለም አቀፍ የግንኝነት መረብ (Internet) በብዛት በመበርበር ማጥናት ጀመረ። ኢሉሚናቲ የሰይጣን አምላኪ የሆኑ የምስጥር ማህበረሰቦች ዓለማችንን በክፉ ሰይጣናዊ ዕቅዳቸው ለመቆጣጠርና ወደ ከፋ ጥፋት የሚያደርጉት ጉዞ 2002 ዓመተ ምሕረት ላይ በከፍተኛ ትኩረትና ያጠናበትና አስከፊው በሴራ
የተጨማለቀው መሰሪነታቸው በቂ በሆነ መጠን የተገነዘበበት ነበር። በዚህ ምክንያትን በፊት የነበረው ነገሮች የሚመለክበት አቅጣጫ ሙሉ በሙሉ የተቀየረበት ዓመት ነው።
በጥናቱ መጨረሻም እኛ ያልገባል ግን እኛን ሊቆጣጠረን የሚችል መንፈሳውዊ ዓለም
እንዳለ በመረዳቱ እውነተኛውን መንፈስ (መንፈስ ቅድስ) ማምለክና ለሱ መገዛት ትክክለኛ መንገድ መሆኑ በተቃራኒው መጓዝ ደግሞ ጥፋት መሆኑ በማወቁ የእግዚአብሔን ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ጀመረ።
የነዚህ መሰሪ ሰይጣን አምላኪዎች አካላት አካሄድ ራሱን በራሱ በማስጠናት በቂ የሚባል ግንዛቤ የያዘ በመሆኑ አቅሙ በፈቀደለት መጠን በመጻፍና በመጦመር 2001 ዓመተ ምሕረት በመሰረታት ኢትዮጵያ አውታር የህዋ ሰሌዳው በመለጠፍ
ሰዎች ግንዛቤው እንዲኖራቸው በማድረግ እንዲነቁና ሴራው በተቻላቸው መጠን እንዲያጋልጡት በተጨማሪም ኢትዮጵያዊው የሆነው ቀደምት እግዚአብሔራዊ ጥበብ በማስተዋወቅና እንዲላበሱት በማድረግ እንዲቃወሙት አድርጓል።
መጽሐፈ ቅዱስ - በፊት እንደ ተራ የፍልስፍናና ዓለማዊ
መጻሕፍቶች ይቆጥረው የነበረው ይህ ቅዱስ መጽሐፍ ማጥናት የእውነተኛው አምልኮ መሰረት መሆኑ ስላመነ መጽሓፉ በተገቢ አካሄድ ማጥናት
ጀመረ። በዚህ ወቅት ነበር በጌታችን መድሓኒታችን ፍቅር ልቡ የተነካው። ቅዱስ ቃሉ |”ሁሉን ፈትኑ መልካሙንም ያዙ” እንደሚለው እውነተኛው ሃይማኖት በጸሎትና በጥናት በመፈለግ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፣ፕሮቴስታን
(ብዙ) ፣ የእስልምናና የይሖዋ ምስክሮች (Jehovah Witness) የእምነት ድርጅቶች በሚገባ በማጥናትና በመረዳት የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እውነተኛው መንገድ መሆኑ ደረሰበት። በመቀጠል ስለ ኢትዮጵያና
ኢትዮጵያዊነት ይበልጥ ማወቅና መረዳት በመጀመሩ ከእውነተኛው ማንነቱ በጣም ርቆ እንደነበር ተገነዘበ። በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት
ላይ በጠላትነት የሚንቀሳቀሱ ውስጣዊና ውጫዊው ሃይሎችን በግልጽ ስራቸውን መገንዘብ ጀመረ። እነዚህ የጨለማው ገዢ ኃይሎች በሚችለው
አቅሙ ለመዋጋትና እውነቱ በተለያዩ መንገዶች ለመግለፅ ራሱን ቃል በማስገባት እየሰራ ይገኛል። በሚገርም ሁኔታ ችግር የሆነበት ግን
ወላጆቼቹ ያደገበት ማህበረሰብ ውስጣዊ የኢትዮጵያ ጠላት የሆነው የጨለማው ገዢ አገልጋይ የሆነው የህወሓት ቡድን ደጋፊዎችና ካድሬዎች
በመሆናቸው የሚደርስበት ስድብና ማንጓጠጥ ነበር። መነሻ ምክንያቱ ነገሮች የሚረዱበት መንገድ ስጋዊና ደማዊ ስሜት መሰረት ያደረገ
ስለሆነ ነው። ይህ ሁሉ ቢሆንም የእግዚአብሔር ቃል በቀጥተኛ መንገድ የምትተረጉሞው ቅዱስ ኪዳን ተዋሕዶ ሃይማኖት ከነበረበት የሱስ
ወጥመድ ነጻ እንዲወጣ በር ሆነዋለች።
ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት - በተጨማሪም ስለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት
ይበልጥ ማወቅና መረዳት ሲጀምር ሀገረ ኢትዮጵያ ሀገረ እግዚአብሔር የነገሮች ሁሉ መጀመርያና መጨረሻ መሆንዋ ለመረዳት ጊዜ አልፈጀበትም።
ኢትዮጵያ የእግዚአብሔር ጥበብ መሰረት በማድረግ የዓለም ስልጣኔ ጠንሳሽ መሆንዋ በመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በማረጋገጡ ከእውነተኛው ማንነቴ
በጣም ርቄ እንደነበር ተገነዘበ። ለኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትም ከፍተኛ ፍቅርና አክብሮ አደረበት ኢትዮጵያዊነት የመጀመርያው የእግዚአብሔር
ልጅነት ነውና። በዚህ ምክንያትም የስይጣን አምላኪዎቹ (ኢሉሚናቲ) ኢትዮጵያ ዋነኛዋ የጥፋታቸው ዕቅድ ለመሆንዋ ለመገንዘብ አልከብደዉም።
በዚህ ምክንያትም የኢሉሚናቲ ጸርና የኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ጠበቃ በመሆን በተለያዩ መንገዶች ይሰራል። በኢትዮጵያ አውታር የህዋ
ሰሌዳው ሲለጥፋቸው የነበሩት ጽሑፎቹ በ2003 ዓመተ ምሕረት በመሰብሰብ በመጽሐፍ መልክ በማደራጀት ሰላቢ እጆች በሚል ርዕስ ለማሳተም
አዘጋጅቷል። በተጨማሪም ለወደፊት መጽሕፍቶች ለማዘጋጀት ይሰራል።
አሁን - ከማንኛው ተጨማሪ አላስፈላጊ የተጽዕኖ ኃይል
ነጻ ለመሆን ከየትኛዉም ድርጅትና ማህበራት አባልነት ነጻ የሆነና በተሰጠው ነጻ ፍቃድ እውነት የሚፈልግ የሰው ልጅ በጠቅላላ ኢትዮጵያዊ
መሆኑ የሚያምን በዚህ ምክንያትም የዘር ልዩነት ሳያደርግ የሰው ልጅ እኩልነት ጽኑ እምነቱ ነው። ቀዳሚትዋና ዘላለማዊት የአዳምና
ሄዋን ቀጥተኛዋ ቅዱስ ኪዳን ተዋሕዶ ሃይማኖቱ ነች። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ
ተዋሕዶ ቤተክርስትያን ስርም ይገኛል።