·
ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
ከ 7000 አመታት በላይ ትክክለኛው አምልኮተ እግዚአብሔር የምትፈጽመው ሃገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ከእግዚአብሔር በመመረጥዋና የእግዚአብሔር ጥበቦች መገኛና ማስፈጸምያ በመሆንዋ በተለያዩ ጊዜያት ይህንን የሚያውቁ ባዕዳውያን ሃይሎች ወደ ሃገራችን በመምጣትና በርቀትም ጥበብዋን ለመዝረፍና ጥንታዊው ኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ ሃይማኖትዋን ለመበረዝ የተለያዩ የሰይጣን አምላኪዎች የሆኑ የምስጥር ማህበራት ጥረት አድርገዋል።በእግዚአብሔር ጥበቃ እስከ አሁን ብት ዘልቅም አውሬው(666) ግን ተቃውሞውና ሴራው ለማስፈጸም እስከ መጨረሻ እንደሚጥር የታወቀ ነው።
የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ የፓርላማው አፈ ጉባኤ አባዱላ ገመዳ በሁለት የደብብ
ባፕቲስት ፓስተሮች በፓርላማ መንበራቸው ላይ እንደተሰየሙ ጸሎት ሲያደርግላቸው።
ባለፉት 41 አመታት ሃገራችን ኢትዮጵያ አብዮተኞች ነን በሚሉና እግዚአብሔር በማያስቅድሙ መሪዎች ስትመራ ኖራለች።ሚያዝያ 3,2008 ዓ/ም በ የደቡብ ባፕቲስት ስብሰባ(Southern Baptist
Convention) መካነ፡ድር የተለጠፈው ዜናም ይህንን የሚያጠናክር ነው።
የድቡብ ባፕቲስት ስብሰባ አባላት ከርዕሰ ብሔር ሙላትይ ጋር ሲወያዩ
ዜናው በሃገረው ውስጥ መገናኛ ብዙሃን መዘገቡ እርግጠኛ ባልሆንም መረጃው እንደሚገልጸው የደቡብ ባፕቲስት ስብሰብ(የመናፍቅ እምነት ነው) ሊቀ መንበር ሮኔ ፍሎይድ ና አባላቱ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ከተለያዩ የመንግስት ባለስልጣናት
ከ ርዕሰ ብሔር ሙላቱ ተሾመ
ከውጭ ጉዳይ ሚንስተር አቶ ቴዎድሮስ አድሃኖም
ከፓርላማው አፈ ጉባዔ አባዱላ ገመዳ
በአሜሪካ ከኢትዮጵያ አምባሳደር ግርማ ብሩ
እንዲሁም ከአየር መንገድ ኃላፊዎች
መነጋገራቸውና የ50,000 አብያተ ክርስትያናት የማስገንባት ዕቅድ እንዳላቸውና ባለስልጣናቱ ይህንን እንዲሳካ እንደሚያግዝዋቸው ገልጸዋ።በተጨማሪም ወደ ኢትዮጵያ የመጡት በኢትዮጵያ አየር መንገድ የነጻ ትኬት ግብዣ መሆኑ ነው።ጉዘው የተዘጋጀዉም በአሜሪካ ከኢትዮጵያ አምባሳደር ግርማ ብሩ የልጅነት የትምህርት ቤት ጓደኛ ከነበሩት አቶ ኃይለየሱስ አስተባባሪነትና ፍቃድ በመጠየቅ ነው።አቶ ኃይለየሱስ
እንዲህ በማለትም ገልጸዋል።
"በ 3000 የታሪክ አመታት ውስጥ አንድ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ የሃገሪቱ መሪ ሲሆን ለመጀመርያ ጊዜ ነው።ይህ ደግሞ ወንጌልን ለመስበክ ትልቅ አጋጣሚ ይፈጥራል።ይህንን ዕድል መጠቀም ደግሞ የኛ ብቃት ነው።"
የደቡብ ባፕቲስት ስብሰባ አባላት የሆኑት ፓስተሮች የ 2008 ዓ/ም የጥምቀት በዓል የተገኙ ሲሆን በመካነ፡ድራቸው በለጠፉት ምስል
ፓስተሮቹ ተቃቅፈው ሲጸልዩ ይታያል።ከዚህ አልፈዉም ለምስሉ የጻፉት መግለጫ እንዲህ ይላል “የኦርቶዶክስ ክርስትና የጥምቀት በዓል በአዲስ አበባ። ወደ 5 መቶ ሺህ ኢትዮጵያውያን ተካፍለውበታል
ይህንን የኢየሱስን ጥምቀት ለማሰብ፤ ነገር ግን በተሳሳተ የነገረ መለኮት ትምህርት የተዘፈቀ … ” ነው።
ይህ
ኢትዮጵያና ኦርቶዶክሳዊ ሃይማኖትን ለመለወጥና ለማጥፋት የሚደረግ ሴራ ተግባራዊ ለማድረግ እንቅልፍ እንደማይወስዳቸው ያዉም የሃገራችን
መሪዎች ድጋፍ ተጨምሮበት እውን ለማድረግ መጣራቸው ግልጽ ነው።እኛም ማንነታችንን ለማጥፋትና የምዕራባውያንን ባዕዳዊ እምነትን ለመጫን
የሚያደርጉት ጥረት መቃወም እና ማንነታችን መጠበቅ ይገባናል።
መጋቢት 4,2008 ዓ/ም