እውነት ልምረጥ
በሂወት ጎዳና
እውነት ውሸት ሞልቷልና
እውነት ልምረጥ ኑሮየ እንዲቀና።
11/08/200EC
ፈጣሪና ሰው
ፈጣሪ ሰው ፈጥሮ ሰው ሆነ
ሰው አለምን ወዶ እንደወጣ ቀረ።
11/08/2008ECአንተ ኢ-አማኝ
ቃላት መደርደር
ኣይሆንም ቁምነገር
እውነት በሓሰት ላይቀየር
መመራመርማ ፈቅዷል ፈጣሪ
ሁሌ ያስተጋባል የእውነት ጥሪ
ማለት ግን ኣይደለም ተመራመር ካድ
አትሳሳት ውጣ ከጥልቁ ጉድጓድ
አሁን ፈረንጅ መጥቶ ቢዘላብድ
የወሰደው ነው ከኛው ማዕድ
አባቶች ተፈላስፈው አልቀሩም
አውርሰውናል በውብ ቀለም
ለምንስ ተሰጠህ ያድንቅ አእምሮ
እንድትመራመር ነው ያሁኑና የድሮ
ትርጉም አታዛባ የመመራመር
ሳይነስ አይደለም የጉዞው መስመር
ፈጣሪ ሳይኖር አንተ ማን ፈጣረህ?
አረ ይሄ ውሽት ማነው የነገረህ
አረ መልስልኝ በፈጠረህ?
ሳይነስስ ምን አለህ?
ምርምርህ መልስ ካልሰጠህ
መጽሓፍ ቅዱስ አንብብ ገልጠህ
መሆንህ ይደንቃል የቋንቋ ፋላስፋ
ፍልስፍና የጥበብ ፍቅር ነው ዕይታንህ አስፋ
ፈጣሪ የለም ስላልክ የተፈላሰፍክ መስሎሃል
ፈሪሃ እግዚአብሔር ግን ሩቅ ያደርሰሃል።
አትሞኝ ንቃ ተመልከት ተፈጥሮ
በእግዛብሔር ጥበብ ሲታይ ተሰባጥሮ
አንዱ ለአንድ ይሆነዋል መዝግያ ጉሮሮ
አይንህ አላይ አለ እንጂ በሳይነስ ተተክቶ
የእግዚአብሔር ስራስ ይናገራል አፍ አውጥቶ።
(ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ)
08/03/2008EC
(ለአንድ ኢ-አማኝ (athiest) የፌስቡክ ጓደኛየ የተጻፈ)
ሰው
እኔ ሰው ይገርመኛል
ጥሩን ትቶ መጥፎ ይመኛል
ራሱን ሳያውቅ ሌላን ይዳኛል።
ጥቅምት 1, 2006EC
(ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ)
ነቃሁ
ነቃሁ ከእንቅልፌ ብርሃኑን አይቼ
ያለፈውን ሁሉ በነበር ዘግቼ
አሁን ገና ታየኝ የመፈጠሬ ሚስጥር
ዋናውን ትቼ ለማይረባው ስጥር
መኖርን ትቼ በውሸት ስባዝን
ሁሉም ለካ ለበጎ ነው በጊዘው ሲሆን
አሁንማ ቆርጫለው በቃሉ ልድን ።
ማየት ከፈለክ ብርሃኑ ግልፅ ነው
የማይረባውን ትተህ ልብህን ለበጎ ክፈተው
መጋቢት 4/2005 EC
(ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ)
ኑሮ በዘዴ
በመኖር ሁሌ አለ ፈተና
ጥሩውን መጥፎውም ለበጎ ነውና
ስለዚ አትጨነቅ ኑር በስርአቱ
ፈጣሪህን አስታውስ እሱ ነው የመኖር ስሌቱ።
መጋቢት 4/2005 EC
( ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ)
የይሁዳ ኣንበሳ
መጣ እያገሳ
ጠላትን ድል ሊነሳ።
(ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ)