EAR

አዲስ ነገር

Sunday, 24 April 2016

የሃገረ አሜሪካ ሰይጣናዊ ዲሞክራሲ

ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ





እርስዎ ሃገረ አሜሪካ  የአለማችን የዲሞክራሲ ቁንጮ ናት ብለው ያስቡ ይሆናል።ደግሞ እንዲህ ብለው ቢያስቡ አይፈረድቦትም ምክንያቱም ይህ ጉዳይ ሁሌ አእምሮአችን እስከሚደኖቁር በመገናኛ ብዙሃን፣በፖለቲካና በተለያዩ ሰዎች በተደጋጋሚ ሲነገር የምንሰምው ነገር ነው።በተለይ የሃገረ አሜሪካ መገናኛ ብዙሃን የአለማችን ህዝብ ጭንቅላት በተቆጣጠሩበት በአሁኑ ጊዜ።

ሃገረ አሜሪካ የተመሰረተችው ከሃገረ እንግሊዝ በመጡ የፍሪማሶንሪ ፡የመጀመሪያዎቹ የሰይጣን አምልኮ የሚፈጽሙ የምስጥር ማህበር አባላት ነበር።እነዚህ ሰዎች የመጀመሪያ የምድረ፡አሜሪካ ነዋሪዎችን(native) በጦር መሣርያ የበላይነት በመቆጣጠር የአሁንዋ ሃገረ አሜሪካ መመሥረት ችለዋል።የመጀመርያው ርዕሰ ብሔር(President) ጆርጅ ዋሺንግተን የፍሪማሶንሪ አባል ነበር።በዚህ ምክንያትም ነው ሃገረ አሜሪካ ከሃገረ እንግሊዝ በተደጋጋሚ በተለያዩ አለማችን ጉዳዮች አጋር ሆነው የምናያቸው የምንሰማቸው።የመጀመሪያ የምድሩ ባለቤትና ነዋሪዎች  የአሜሪካን መንግሥት በመቃወም እስከ አሁን ድረስ ጦርነት ላይ ናቸው።ሆኖም እነዚህ ነገዶች በአሜሪካ የጦር ሓይል ግድያና የበላይነት ቁጥራችው እየቀነሰ ነው።

አለማችን እኛ በማናውቃቸውና ስማቸው እንኳን ሰምተነው በማናውቃቸው ጥቂት ነገዶች(ኢሉሚናቲ) ትመራለች።እነዚህ ጥቂት ግን አብዛኛውን የአለማችን ሃብት በብልጣታቸውና ስይጣናዊ ዘዴ ተቆጣጥረውታል።ወዳጄ እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቅ ዎት፧ አለማችን ሃብታም(ቱጃር) ሰው ማነው፧ በእርግጠኝነት መልስዎ ቢል ጌትስ የሚል ይሆናል።ግድ የለም ወዳጄ ይህ እነዚህ ጥቂት ሰዎች (ኢሉሚናቲማንነታቸውና ሰይጣናዊ ዕቅዳቸው እንዳይታወቅባቸው የመገናኛ ብዙሃናቸው በመጠቀም የሚያደርጉት እውነት የመደበቅ ሴራ ነው እንጂ የአለማችን አብዛኛው ሃብት በቀጥታም በተዘዋዋሪም በትሪልዮን በሚቆጠር መጠን በነዚህ ጥቂት ሰዎች ቁጥጥር ስር ነው።ታድያ ይህ ሃብታቸው አለማችንን በተዘዋዋሪ በመቆጣጠር በፍላጎታቸው አቅጣጫ እንዲመርዋት የሚያደርጋቸው።

ሃገረ አሜሪካ በየአራት አመቱ የምታደርገው የርዕሰ ብሔር ምርጫም የነዚህ ጥቂት ሰዎች ማስፈጸምያና የውሸት ዲሞክራሲና ምርጫ የሚነገርበት የማታለያ መንገድ ነው።ወዳጄ ስለ ዲሞክራሲና ምርጫ በየቀኑ የሚደሰኩርልን መገናኛ ብዙሃኖች የነዚህ ጥቂት ስዎች ንብረቶችና ሃብቶች መሆናቸው ያስሙርበት።በዚህ መሠረትም እነዚህ ጥቂት ሰዎች ከጀርባ በመሆን በሃገረ አሜሪካና አለማችን ላይ ያላቸውን ሰይጣናዊ ዕቅድች ሊያስፈጽንምላቸው የሚችል የፖለቲካ ስው በቅድሚያ በመምረጥ ያዘጋጃሉ።በሃገረ አሜሪካ ዲሞክራት እና ሪፐብሊካን የሚባሉ ሁለት የፖለቲካ ድርጅቶች ወይም ፓርቲዎች ብቻ እንዳሉ ያውቃሉ ብየ አስባለው።የነዚህ ድርጅቶች አንቀሳቃሽ ሞቶሮችም እነዚህ የጀርባ ጥቂት ሰዎች (ኢሉሚናቲ) ናቸው።ለይሙስላ የህዝብን ትኩረት ለመሳብና ሓሳብ ለመስረቅ በቴሌቪዥን መስኮት ፓርላማ ውስጥ በመከራከርና በመጣላት የምናያቸው እንዳትሸወድ በጋራለ አንድ አላማ የቆሙና ከፓርላማ ውጭ ስለ ሴራቸው ሻይ እየጠጡ የሚያወሩ ናቸው።የ ህዝብ ሓይለ ህሊና ለመስረቅ ግን በሁለት ጎራ ተከፋፍለው ዲሞክራትና ሪፐብሊካን የሚል የስም ሽፋን ይጠቀማሉ።ከላይ እንድተገለጸው የርዕሰ ብሔር ምርጫም ለይምሱላ የሚደረግ እንጂ መጀመርያዉኑ በነዚህ ሰዎች ተመርጦ የተጨረሰ ነው።ሆኖም የህዝቡ መንፈሰ ለመስለብና ውዥንብርና የመገናኛ ብዙሃንን በመጠቀምና ከፍተኛ የገንዘብ ስፖንሰር በማድረግ(የአለማችን የሃብት ቁንጮ መሆናቸው አትርሳ) ስለመረጡት ሰው በጎውን በማውራት በህዝብ ጭንቅላት ላይ በበጎ እንዲቀረጽ በማድረግ የገጽታ ግንባታ አስቀድመው ይሰራሉ።

ይህ ነገር ልብ  ብለዉት ያውቃሉ ወዳጄ፧ ዲሞክራሲያዊት ናት በሚልዋት ሃገር ሁለት የፖለቲካ ድርጅቶች ብቻ በከፍተኛ ሁኔታ የሚሳተፉ ሲሆን በሃገራችን ኢትዮጵያ ግን ከአስር በላይ የፖለቲካ ድርጅቶች በትንሹ ያሉ ይመስለኛል።የፖለቲካ ድርጅት ብዛት ዲምክራሲ ህልውና ባያረጋግጥም ዲሞክራሲ በምድር ላይ ኖሮ ባያውቅም።

የርዕሰ ብሔርነት ስልጣኑን በያዝነው አመት የሚለቀው ባራክ ኦባማ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ በሕግ ማጽደቁስ ለምን ይሆን፧ ወይስ ዲሞክራሲ ማለት ሰይጣንን ማገልገል ነው፧ የሚገርመው ባራክ ኦባማ የመገናኛ ብዙሃን በፈጠሩለት የውሸት ጥሩ ስብዕናና የንግግር ችሎታው ማለትም ጥሩ ቃላት አቀላጥፎ በመናገር በመዋሸት ያለው ችሎታ ተጠቅሞ የኢሉሚናቲዎች ማስፈጸምያ በሆነው የተባበሩት መንግስታትን ለመምራት ዕቅድ እንዳለው ተናግሯል።ኦባማ ሃገሩ ላይ ያጸደቀው የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ አለማችንን ላይም ተግባራዊ ለማድረግ ፈልጎ ይሆን እንዴ፧ ጊዜ የሚፈታው ጉዳይ ነው።ኦባማ ራሱም ግብረሰዶማዊ መሆኑ ይታወቃል።

በያዝነው አመት የሚካሄደው የሃገረ አሜሪካ የርዕሰ ብሔር ምርጫም እንደሚታየውና እንደሚሰማው ዶናልድ ትራምፕ ቀጣዩ ርዕሰ ብሔር እንደሚሆኑ ከዚህ ቀደም የነበሩት አካሄዶች በማስታወስና የሚታየው የመገናኛ ብዙሃኖች ዘገባዎች መገንዘብ በቂ ነው።ቀድሞውኑ እንደተጨረሰ ግልጽ ነው። የተለያዩ ሴራዎች ቀድሞ የሚተነብየው የሲምፕሶን ተከታታይ የካርቶን ተንቀሳቃሽ ምስል ዶናልድ ትራምፕ እንደሚያሸንፉ በ 2000 እ.ጎ.አ በተሰራጨው የፊልሙ ክፍል ገልፆል።
ሲምፕሶን ተከታታይ ፊልም ዶናልድ ትራምፕ እንደሚያሸንፉ 2000 እጎአ የተነበየበት ምስል

ወዳጄ ጽሑፉ አስደነገጠህ እንዴ፧ ምን አግብቶት ነው ይህ ሁሉ የሚቀባጥረው አልክ እንዴ፧ ደህና እግዚአብሔር ዕድሜው ከሰጠን ሁሉም እናያዋለው።ሰላም።

  ሚያዝያ 16, 2008 ዓ/ም