EAR

አዲስ ነገር

Friday, 25 December 2015

ኢትዮጵያና ኢሉሚናቲ፡ስንደቅ አላማ


ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ
ታላቁ መጽሐፍ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን በኖህ ዘመን የጥፋት ውሃ ባበቃ ጊዜ እግዚአብሔር ለኖህ ዘርህን ሁለተኛ  በጥፋት ውሃ አላጠፋም ብሎ ቃልኪዳን በገባለት ወቅት የገለጸለት ቀስቴን ደመና ላይ እሰካለው በማለት የቀስተ ደመና ምልክት ሰማይ ላይ በማሳየት ነበር።ይህ ታላቅ የምህረት ቃልኪዳን በመቀበልም ቅድስት ሃገር ኢትዮጵያም ከጥንት ጀምሮ ይህንን የቀስተ ደመና ቀለማትን(አረንጓዴ፣ብጫ እና ቀይ) በመውሰድ የሰንደቅ አላማችን መለያ በማድረግ ከእግዚአብሔር ጋር ያላትን ጥንታዊ ግንኝነት አጣናክራበታለች።ይህንን ከእግዚአብሔር ጋር ያላትን ጥንታዊ ግንኝነት የሚጠብቁ የተለያዩ ነገስታት መንፈሳዊነትን በማስቀደም ህዝባቸውንና አገራቸውን ከእግዚአብሔር ጋር በመማከር እግዚአብሔርን በማስቀደም ያስተዳድርዋት ነበር። 

የኢትዮጵያው 225ኛውና የመጨረሻው ንጉስ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በአብዮት ከንግስናችው እስከ ተወገዱበት ድረስ ኢትዮጵያ በመንፈሳዊያንና እግዚአብሔርን አስቀድመው በሚመሩ ነገስታት ትመራ የነበረች ቢሆንም ከአብዮት በሃላ የመጡ መሪዎች(ድህረ፡ነገስታት) ግን መንፈሳዊነትን በመርሳት ስጋዊ በሆነ ፍልስፍናዊ አመራር በመጠቀም ለማስተዳደር በመሞከራቸው የሚስጥር ማህበራትን(ILLUMINATI)ድብቅ አጀንዳዎች ማስፈጸምያና መንገድ ጠራጊዎች ሆነዋል።በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ አስተዳደር የነበረው የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ መሃል ላይ የነበረው የይሁዳ አንበሳ ምስል ነበር።ይህ የይሁዳ አንበሳ ምስል ዘይባዊ( Metaphor)ትርጉሙ ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን ይወክላል።በግልፅ እንደምንረዳው ከምንም በፊት ነገስታቶችን ፈጣሪን በማስቀደም አገራቸውንና ህዝባቸውን ያስተዳድሩ እንደነበረ ነው።በአሁኑ ወቅት ያለው የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ግን መሃል ላይ ባለ አምስት ነጥብ ኮከብ(Pentagram) ይገኝበታል።ይህ ኮከብ በሚስጥር ማህበራት አስተምህሮ አምስቱም ጫፎች የየራሳቸው ፍቺ አላቸው የመጀመርያውና ላይኛው ጫፍ መንፈሳዊው አካል ሲወክል የተቀሩት አራት ጫፎች ደግሞ እሳት፣ምድር፣አየር እና ውሃን ይወክላል።በሚስጥር ማህበራት ህግ(ቀኖና) ሁሉም ሰው ኮከብ ነው ማለትም እየንዳንዱ ሰው የራሱ ፈጣሪ ነው(You are your own GOD የሚለውን የክህደትና የድፍረት ትምህርት ነው።ሆኖም እያንዳንዱ ሰው የራሱ ፈጣሪ ሳይሆን ከሰው በላይ የሆነ ሰውንና አለማትን የሚታየውንና የማይታየውን የፈጠር ከሃሊ ኩሉ የሆነ የመጀመርያውና የመጨረሻ (Alpha and Omega) አንድ ፈጣሪ እግዚአብሔር ነው።