ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
(የጉዞ ማስታወሻ)
በትናንትናው ዕለት (ጥቅምት 9/2007) በትግራይ ውስጥ ከሚገኙት ድንቅ የእግዚአብሔር
ጥበብ ካረፈባቸው ገዳማት ውስጥ እንደ እግዚአብሐር ፍቃድ 3ቱም ጎበኝን። እነዚህ ገዳማት ከመቀለ ውቅሮን አልፈህ አዲግራት ሳትደርስ
የሚገኙ ሲሆን ድንቅ ተአምራት፣ሰነ-ህንፃዊ ጥበብ(Architectural Design)፣አቀማመጥና ፈውስ ያለባቸው ናቸው።ሰወስቱም
ገዳማት(አብያተ ክርስትያናት) ከድንጋይ ተፈልፍለይ የተሰሩ ናቸው።ቅድሚያ የሚገኝው መድሃኔ አለም ዓዲ ቆሾ ገዳም ሲሆን ድንቅ የሆነ
ተአምራት ያያንበት ነው። መጋቢት 27(ጌታ የተሰቀለበት ቀን) ሲደርስ ከየገዳሙ አንደኛው አምድ(pillar) ላይ ዉሃ፣ውተትና ማር ይፈልቃሉ። እነዚህ ፫ ነገሮች ደግሞ
ጌታችን በተሰቀለበት ጊዜ ጎኑ በጦር ሲዎጉት ከጎኑ የፈሰሱት ነገር ናቸው።ድንቅ ዕፁብ ነገር አይገርምም? እውነትም አቢሲንያ ሃገረ
እግዚአብሔር።
ቀጥለን የጎበኝነው ገዳም ጴጥሮስ ወጳውሎስ ይሰኛል።ይህ ገዳም ከመድሃኔ አለም ዓዲ
ቆሾ ገዳም በቅርብ ርቀት የሚገኝ ሲሆን ወደ ገዳሙ ለመዝለቅ የግድ መሰላል መጠቀም ግድ ይላል።ይህ ገዳም በ ሃፀይ ገብረ መስቀል
ጊዜ የተመሰረተ ሲሆን በመጨረሻው ሰማዕት ሮማዊው ጴጥሮስ ስም ይጠራል።
ገዳሙ ውስጥም የ አባቶች ቅርተ አካል(አፅም) በግልፅ ይታያል።ከላይ እንደተገለፀው ወደ ገዳሙ ለመዝለቅ ትንሽ ፈታኝ ሁኔታ ስለ
አለና ከዚህ በፊት አንዲት እናት ወድቀው ስለ ሞቱ የአካባቢው ህዝብ ወደ ገዳሙ ለመሳለም መፍራት ስለ ጀመረ ቤተ ክርስትያኑ ወደ
ታች ወርዳል። ታች ያለው ቤተ ክርስትያንም ሓለቃ ሓለፎም በሚባሉ ያከባቢው ነዋሪ ከ አለት ተፈልፍሎ የተሰራ ነው። ቤተ ክርስትያኑ
ፈልፍለው የሰሩባት መሳርያም እዛው በቅርስ መልክ ተቀምጣ ትገኛለች።
መጨረሻ ላይ የጎበኝነው ሚካኤል ምልሃይ ዘንጊ ገዳም ነው።ይህ ገዳም በ 4ኛው ክፍለ
ዘመን በ አቡነ አብርሃም የተመሰረተ ነው።በገዳሙ ውስጥ ያሉት ምስሎችና ቅርፆች የሚመስጡና በጣም የሚማሩኩ ናቸው። በጣራው ላይ
በክብ ቅርፅ የተቀረፀው የ ጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ ያሳለፈው መከረና ስቃይ በሚገባ ተገልፆበታል ታላቅ ምስጋና ለቅዱሳን አባቶቻችን ይሁንና።በ ገዳሙ በ አንደኛው ጎን ላይም
በሚገርም ሁኔታ ሚስጥረ ስላሴ የሚገልፅ ምስል ይገኛል።
በ አጠቃላይ ሲታይ ኢትዮጵያ ሓገራችን መንበረ እግዚአብሔር መሆንዋ በሚገባ ተገንዚቤአለሁ።
በሕይዎቴ ትክክለኛ ደስታ ያገኝሁባት ቀንም ይህቺ ቀን ነች። እናንተም ገዳሞቹን እንድትጎበኛቸው እጋብዛቹአለሁ።
እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር።