አንድ ሰው የሚፅፈው ነገር በሰዎች ዘንድ በጎ ተጽዕኖ ከሌለው የሚጽፈው ነገር ትርጉም የለዉም ወይም አሉታዊ ተጽዕኖ አለው ማለት ነው።ታሪክን ለትውልድ መፃፍና ማሳወቅ አዲሱ ትውልድ ካለፍው ነገር በጎውን በመውሰድ እንዲጠቀምበት መጥፎዉም በማወቅ እንዳይደገም ከተቻለም እንዲያስተካክለው እንዲያግዘው መሆን አለበት።ይህ በ አትቶ አታክልቲ
ሓጎስ የተፃፈው አይንተሓማመ የሚል ርዕስ የተሰጠው የትግርኛ መፅሓፍ ግን በሚገርም መልኩ የዘር ግንድን መሰረት በማድረግ አንድን ወገን(ፀሃፊው ሸዋዊ የሚሉት) ለመውቀስና የተዘጋጀ ነው።በመፅሓፉ መግብያ ላይ እንደተገለፀው መፅሓፉ የተፃፈው ፀሓፊው እንደሚሉት ሸዋዊያን ያበላሹትንና ያጣመሙትን ታሪክ ለማስተካከል እንደሆነ ይገልፃሉ።በዚህ ምክንያትም የመፅሓፉ ርዕስ "አይንታሓማመ" ወደ
አማርኛ ሃሜት ይቅር ወይም አንወቃቀስ የሚል ትርጉም አለው።ፅሓፊው ሲቀጥሉ ሸዋውያን የታሪክ ጸሓፊዎች የትግራይ ተወላጅ የሆኑትን ሃጸይ የውሃንስን ጀግንነት በመተውና በማጣመም ጀግንነት የሸዋውያን ነገስታት ብቻ እንዲሆን
አድርገዋል የሚል ውንጀላ ነው።ሆኖም አቶ አታክልቲ ስ ህተት ነው ያሉትን ታሪክ ከማስተካከል አልፈው(ታሪክ ማስተካከል ባይቻልም) በየሸዋ ነገስታት ላይ ያላቸውን የማይጠቅምና ትውልዱን ሊመርዝ የሚችል ጥላቻቸው ከ አንድ ፀሓፊ ነኝ ከሚል ሰው በማይጠበቅ መልኩ ገልጸዋል።ይህንን የጥላቻ መንፈስም የቀጣይን ትውልድ መንገድ በተዳፈነ እሳት ላይ እንዲቀመጥ ያደርገዋል።ታሪክን በዘር ከፋፍለህ መጻፍም ከሰብ አዊነት መውጣትና የልጆች አእምሮ በመርዝ መበከል መሆኑን ሊታወቅ ይገባል።አቶ አታክልቲ ሓጎስ የዘር መቁጠር በሽታቸው በሌላ መንገድም ገልጸውታል።የኢትዮጵያ ንጉሥ የነበሩትን ሃጸይ ቴዎድሮስን ትግራዋይ ናቸው በማለት።እኚህ ንጉሥ ኢትዮጵያዊ የሚለውን ማንነት ዝቅ በማድረግ ትግራዋይ ናቸው ወደሚል ከፋይ ማንነት ማውረድስ አንድምታው ምን ይሆን? እኛ የሃጸይ ቴዎድሮስ ታሪክ የምንፈልገው እንደ ኢትዮጵያዊ እንጂ ወደ ዝቅተኛ ደረጃ በወረደ ማንነት አይደለም።የዚህ አስተሳሰብ(ዘረኝነት)ዋነኛው የችግሩ መነሻም ስጋዊ የሆነ የጥላቻ አስተሳሰብ እና ለመጪው ትውልድ ካለማስብ ነው።ጸሓፊው በሃጸይ ምኒሊክ ላይ ያላቸው ጥላቻ
በግልፅ ይነበባል።ሆኖም ጥላቻን በመስበክ ሳይሆን ትውልዱን የምናስተምረው በጎውን በማስተማር ነው።እኔ ለማውቃቸው ሰዎች ሆነ ለልጆቼ
ይህንን ኣስተምራቸዋለው።ሃጸይ ምኒሊክ ሃገራችን ኢትዮጵያ ለመድፈር ለመጣው የጣልያን ሰራዊት ንጽህት የኦርቶዶክስ እምነትን ጋሻ
በማድረግ በዕለት ጊዮርጊስ በአድዋ የጊዮርጊስ ቤተ ክርስትያን በማስቀደስና ጸሎት ወደ ፈጣርያቸው በማድረስ ታቦት ጊዮርጊስን በመያዝ
በጊዜው ዘመናዊ የጦር መሳርያዎች የታጠቀውን የጣልያን ሰራዊት በእግዚአብሔር ሃይል በማሸነፍ ማንነታችንና ሃይማኖታችን በባዕዳውያን
ሳይበረዝ እንዲደርሱን አድርገዋል።ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትም ከኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ውጪ ማሰብና ማየት አይቻልም።ሆኖም ይህንን ሃይማኖት ሽፋን በማድረግም በየፖለቲካ መነፅር ማየት የሚፈልጉ ግለሰቦች አይታጡም።ቅድሱ መጽሓፍም የሚነግረን አንድ ሰው ለሁለት ጌቶች መገዛት አይችልምና የፖለቲካ መነጸራቹን በማውለቅ ለማየት ሞክሩ እንላለን።ኢትዮጵያዊነት ስጋዊው የምድር ካርታ ሳይሆን መሎኮታዊው የክርስቶስ ቅዱስ መንፈስ ነው።የሰው ዘር(አዳም) መገኛም ኢትዮጵያ ነች።ማለትም የሰው ልጅ ኢትዮጵያዊ ነው።ቅዱሱ መፅሓፍም "ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች" (መዝሙር
፷፰፡፴፩) እንጂ ትግራይ፣አማራ፣ኦሮሞ ወይም ሌላ ብሔር አላለም።
ኢትዮጵያዊነት ይቅደም ታላቅ ክብር ነውና።ሰላም።