·
ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
ዶክተር አቡሽ አያሌውን ገና ተማሪ ሳለው በሚያሳትማቸው ሜዲካል ጋዜጣና መጽሔት ነበር የማውቀው።በጊዜውም በጣም ተወዳጅና ተነባቢ ነበሩ።ተማሪ ሆኜ የነበረኝን የሳይነስና ሕክምና ዕውቀት ላይም ከፍተኛ አስተዋጽ ኦ ነበራቸው።ከጊዜያት በሃላ ግን የዶክተር አቡሽ ጽሑፎች በደምብ ማጤን ስጀምር ከመጽሓፍ ቅዱስ ጋር የሚጋጩና የምዕራባውያን የክህደት አስተምህሮ የሚያበረታቱ ሆነው ነው ያገኝህዋቸው።ዘ ማይንድ የሚሉ ተከታታይ መጽሕፍትና አልፋና ኦሜጋ ሁለት ቅጽ መጻሕፍቶች ጭራሽ 666 (የ አውሬው ቁጥር) ቅዱስ ቁጥር ብሎ ለመጥራት የደፈረ ነበር።በተጨማሪው እግዚአብሔርን የሚገኝበት የ አልበርት አንስተይን ቀመር የሚገልጽ ነበር። 2007 ዓመተ ምሕረት ላይ በምዕራባውያን ሴራ አፍሪካ ላይ የተሰራጨውን የኢቦላ በሽታ ሃገራችን ኢትዮጵያ ላይ ቢከሰት ለመከላከል በሚል ያሳተመው መጽሓፍ ብቸኛው መከላከልያ መንገድ መሆኑ ሲሰብክ ነበር።የበሽታ መከላከልያ ግን እግዚአብሔርን በጸሎት ማነጋገር ብቻ ነው።
አሁን ደግሞ በፋና FM 98.1 ላይ በጀመረው የሬድዮ መርሃ ግብር ዘመኑ የቢዝነስ ነው በማለት የውሸት ስብከቱን ጀምሯል።