EAR

አዲስ ነገር

Tuesday, 26 September 2017

‹‹ ባርያና ዲያስፖራ ››




ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ

ባርያና ዲያስፖራ ከወዳጄ በስጦታ እንዳነበው የተሰጠኝ መጽሓፍ ነው።መጽሓፉ ለየተ ያሚያደርገው ጸሓፊው በተግባር ያጋጠመው የስደት ተሞክሮ ያካፈለበት በመሆኑ ነው።አንድ መጽሓፍ በተግባር በተፈተኑ ነገሮች ተዋቅሮ ሲቀርብ ከምናባዊ የሆኑ መጻሕፍት በላይ በኔ በኩል ለማንበብ የምመርጣቸው ናቸው።ምክንያቱም ጸሓፊው ከስሜትና ወገንተኝነት ነጻ ሆኖ እውነተኛው መረጃና ሓሳብ የማቅረብ ዕድሉ ከፍተኛ በመሆኑ ነው።

ጸሓፊው ራሱን የገለጸበት መንገድ ደግሞ እጅግ ትኩረቴን በመሳብ ነበር መጽሓፉን በአጭር ግዜ ውስጥ አንብቤ ቀምነገሩን ለመጨበጥ የሞኮርኩት።በመጽሓፉ የተገለጸው የጸሓፊው ስም "ነጻነት ናፋቂ ዩድ" ይላል።ይህም ከመጽሓፉ አንዳች የነጻነት ጮራ እንድትናፍቅ ያደርገሃል።ብዙ ጊዜው ባርነት ላይ ያለ ሰው ባርነቱ እንዳይገነዘብና እንዳያስታውስ አድርገህ ስትገዛው ራሱን ነጻ አድርጎ ሊያስብ ይችላል።ከጊዜያት በኋላ ባርነት ውስጥ እንዳለ ቢገነዘብም ነጻነት የሚያገኝበት መንገድ አለማወቅ ደግሞ ሊያስጨንቀው ይችላል።

ነጻነት ናፋቂው ዩድ እንደሚያስረዳን ዲያስፖራ እያልን የምንጠራው ከኢትዮጵያ ውጪ ለአመታት ቆይቶ የሚመጣ ወይም ደግሞ በውስጭ አገር የሚኖር ሰው በቀጥተኛ አገላለጽ ባርያ ማለት ነው ይለናል።ባርያ የሚለው ቃል  ደግሞ ለዲያስፖራው ወንድም እና እህቶቻችን በመጠቀም ትክክለኛው ማንነታቸው መንገድር ህተት እንዳልሆነ እንዲያዉም ባርያ የሚለው ቃል መጠቀም ወንድም እና እህቶቻችን አባቶቻችን ነጻነታችንን ጠብቀው ያቆዩልን ዛሬ በራሳቸው ፍቃድ ባርነት የሚናፍቁበት በመሆኑ በደምብ ይገልጻቸዋል።

አባቶቻችን ለዘመናት ያቆይልን ነጻነት ዛሬ ምዕራባውያን በረቀቀ ዘዴ እየነጠቁን ነው።ሌሎች አፍሪካ ሃገራት ለዘመናት የማቀቁብት ባርነት ወላጆቻቸው እንዴት እንዳንገሸገሻቸው ስለሚያውቀ ዘመናዊው ባርነት (ዲያስፖራነት) ይጠየፉታል ይጠሉታል።እኛ ኢትዮጵያውያን ግን ባርነት ስለማናውቅ ይህንን ባርነት አሁን በገዛ ፍቃዳችን እየፈለግነው ነው።ለዘመናት አፍሪካውያን ጉልበት የተመሰረተው የምዕራባውያን ስልጣኔና ሰነ ቁጠባ አሁን ደግሞ በኢትዮጵያውያን ወንድምና እህቶቻችን በረቀቀ ዘዴ እየተፈጸመ ነው።ባርያ ማለት ፤ ጉልበቱን ዕውቀቱን ችሎታውን ጊዜውን (ዕድሜውን) ለሌላ አገርና ወገኑ ላልሆነ ህዝብ የሚሰዋ ፤ የሌሎች አገልጋይ ማለት ነው።በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያውያን የውጭ ሃገራት ሰነ ቁጠባ ለመደገፍ ጉልበታቸው ለረከሰ ስራ በማሰማራት ድጋፍ እየሰጡ ነው።ይህም አሰራርም በምዕራባውያብ በረቀቀ ዘዴ ድጋፍ ይደረግለታል።ዲቪ እያሉ የሚሰጡን ዕድል ለኛ በማዘን ሳይሆን ሰነ ቁጠባቸው የሚደግፍላቸው ርካሽ ጉልበት ለማግኝት ሲሉ ብቻ የሚያደርጉት ብቻ ነው።

ጸሓፊው ዲያስፖራነት የሚያኮራና የሚያስመካ ሳይሆን የሚያሳፍርና የሚያሸማቅቅ መሆኑ በግልጽ ሊያስረዳን ይሞክራል።ኢትዮጵያውያን በውጭ ሃገራት ያሚኖሩት ኑሮም እንደሚዎራው ሳይሆ በጣም አሳዛኝ መሆኑና የሚደረጉ አስከሚ ድርጊቶችም በመጽሓፉ ስለ አብራራው መጽሓፉን መመልከት ይበልጥ ግንዛቤው ይጨምርልናል።

ቅድስት ሃገር ኢትዮጵያ 7510 ዓመታት ነጻነትዋ ጠብቃ የኖሮች ምድር ነች።ይህንን ለማስቀየር ግን ምዕራባውያን የጨለማው ገዢ አገልጋዮች ግን መላው አለም አባታቸው ዲያብሎስ ለማስገዛት በሚያደርጉት የሞት ሽረት ትግል ኢትዮጵያዊ በከፍተኛ ሁኔታ የሚፈትኑበት ወቅት ነው።ይህም ከነፍስና ስጋ ተዋህዶ የተሰራው የሰው ልጅ በተለይ ኢትዮጵያዊ ለስጋዊ ትርፍ ሲባል ነፍስን እንዳያጠፋት  ሴራው በመመከት ቅድስነትዋ ለመንጥቅ እንቅልፍ ያጡት ምዕራባውያን ማሳፈርና ኢትዮጵያዊነቱን ማስከበር አለበት እላለው።

ማክሰኞ መስከረም 16, 2010 ዓመተ ምሕረት

No comments: