EAR

አዲስ ነገር

Sunday, 19 November 2017

ወደ ብርሃን አውጥታቹ አጋልጡት እንጂ ፍሬቢስ ከሆነ ከጨለማ ስራ ጋር አትተባበሩ። ---ኤፌሶን5:11


ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ



2001 ዓመተ ምሕረት ላይ በተከፈተቺው ኢትዮጵያ አውታር የህዋ ሰሌዳየ ስለ ኢሉሚናቲ በመጻፍና መለጠፍ ከጀመርኩበት ጊዜ ከነበረው ሁኔታ አንጻር አሁን ብዙ ሰው ስለ ኢሉሚናቲ ሴራዎች በከፊልም ቢሆን ግንዛቤው እያደገ ነው።አንዳንድ ከለመዱት እስር ቤት ነጻ መውጣት ሞት የሚመስላቸው ሰዎች ግን እውነታው መቀበል ትተው የምዕራባውያን አምልኮ እያስቸገራቸው እውነታው የሚጽፍ ሰው ስህተት ቢኖርበት እንኳን ከማስረዳት ይልቅ የስድብ ናዳ ሲያዘንቡበት ይገኛሉ።እነዚ ሰዎች ያልገባቸው በነርሱ ስድብ የሚቀየር ነገር አለመኖሩ ነው።ይልቁንስ ራሳቸው ለእውነታው በማስገዛት ነጻ የሚወጡበት የእግዚአብሔር መንገድ መፈለግ ነው።

2004 ዓመተ ምሕረት ሟልበወቅቱ የሃገረ አሜሪካ የርዕሰ ስልጣን ባለቤት ባራክ ኦባማ ግብረሰዶማዊ በመሆናቸው "የባራክ ኦባማ ግብረሰዶማዊ ማንነት" በሚል ርዕስ ኢትዮጵያ አውታር የህዋ ሰሌዳ በለጠፍኩት ጽሑፍ ምክንያት ጽሑፉ የተሟላ ማስረጃ የቀረበበት ቢሆንም ማስረጃው ከማረጋገጥ ብዙ ሰዎች የባራክ ኦባማ ተቆርቋሪ በመሆን ለስድብና አንተ ማነህ ፧ የሚል የንቀት ስላቃቸው አዘነቡብኝ።

ይህ የማደርገው ራሴን ጻዲቅ በማድረግ የሌላ ሰው ኃጥያት በማጋለጥ ራሴን ለማግነን ሳይሆን ቅዱስ ቃሉ እንደሚለው "ወደ ብርሃን አውጥታቹ አጋልጡት እንጂ ፍሬቢስ ከሆነ ከጨለማ ስራ ጋር አትተባበሩ።"  --ኤፌሶን ፭፥፩፩ በሚል መንገድ ነው።በአለማችን የስልጣን ቁንጮነት የተቀመጡት ሰዎች የጨለማው ገዢ አገልጋዮች መሆናቸው በማስረዳት ሌላ ሰው ከነዚህ አካላት የሴራ ድራማ ራሱን እንዲከላከል ነው።

በቅርቡ ይበአሁኑ ወቅት የሃገረ አሜሪካ ርዕሰ ስልጣን ባለቤት ዶናልድ ትራምፕ የኢሊሙናቲ ፈረስ መሆናቸው "የሃገረአሜሪካ ሰይጣናዊ ዲሞክራሲ" በሚል ርዕስ የለጠፍኩት ጽሑፍ በመቃወም የስድብ ናዳ ያወረደብኝ አሳዛኝ ግለሰብ አለ።የሚገርመው ግን አንባቢው ጽሑፉ ዶናልድ ትራምፕ ከመመረጣቸው በፊት ትራምፕ አስቀድሞ አሜሪካን ለመምራት በጌቶቻቸው የተመረጡ መሆናቸው ጽሑፉ መጠቆሙ ልብ አላለም ወይም አንብቦም የምዕራባውያን አምልኮው እውነታው እንዳይመለከት አድርጎታል።

አንባቢው ያቀረበው መከራከርያ ነጥብም ውሃ የማይቋጥር ነው።ትራምፕ ስልጣን በያዙበት ማግስት ግብረሰዶማዊነት ለማጥፋት እሰራለው ብለው ቃል ገብተዋል የሚል ነው።አንባቢው ልብ ማለት ያለበት ግን የአለም ህዝብ የማደናገርያ ዘዴ  እንጂ በእውነት መሬት ላይ ወርዶ የሚሰራበት አለመሆኑ ነው።ግብረሰዶማዊነት ማስፋፋት ዋነኛው የኢሉሚናቲ ዕቅድ ነው።ትራምፕም በኢሉሚናቲዎች ወደ ስልጣን እስከ ወጡ ድረስ ከእነሱ ፍቃድ ውጪ ሊሄድ አይችልም

ትራምፕ በበዓለ ስሜታቸው ጊዜ በምስጥር ማህበረሰቦች የሚተዳደረው የማልታ ባለሟሎች በተሰኝ የፍሪማሶኖች የአምልኮ ቦታ ጸሎት ተደርጎላቸው ነበር ስልጣናቸው የተረከቡት።በዚህ ልጥፍ ያለው ብርሃናዊ ምስል (photo) በደምብ ተመልከት ተቃዋሚ በመምሰል ለስልጣን ስትፎካከረው የነበረቺው ሂላሪ ክሊንተንና ስርዓቱ በጸሎት ያስፈጸሙት የምስጥር ማህበረሰብ በሆኑት የማልታ ባለሟሎች ቄስ ጢሞትዮስ ዶላን ከሰነ ስርዓቱ በኃላ የተነሱት ብርሃናዊ ምስል ነው።ሰው የሚመዘነው በሚናገረው ነገር ሳይሆን በተግባሩ ነው።

‹‹እነርሱ የማያምኑበት ምክንያት የዚህ አለም አምላክ የሆነው ሰይጣን ልቦናቸው ስላሳወረው ነው ፤ በእግዚአብሔር መልክ ስለ ተገለጠው ስለ ክርስቶስ ክብር ከተነገረው መልካም ዜና የሚመጣላቸው ብርሃን እንዳያዩ ያደረጋቸው እርሱ ነው››
 ---፪ቆሮንቶስ ፬፥፬

እሁድ ኅዳር 10,2010 ዓመተ ምሕረት



No comments: