ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
ይህ ጽሑፍ ከተጻፈ የቀየ ቢሆንም በወቅታዊ ሁኔታ መሰረት በማድረግ ድጋሚ ለጠፍኩት
ቀልድ የእውነት ነጸብራቅ ነው። የሃገረ አሜሪካ ኮሜድያን የፖለቲከኞች ውሸት በኮሜዲ ስራቸው በማጋለጥ ከጋዜጠኞች በላይ ተጽዕኖ በመፍጠር ይታወቃሉ። በዚህ ምክንያትም የሴራ ሰለባዎች ናቸው።የቻርሊ ቻፕሊን የታላቁ አምባገነን ንግግር(The Great Dictator Speech) የኮሜዲ ፊልም ለተመለከተም ኮሜዲ ምን ያህል እውነትን እንደሚያንጸባርቅ መረዳት ይችላል። የሰው ልጅ አንዱ ገዢ አንዱ ደግሞ ተገዢ ለማድረግ በሚያደርገው ጥረት ሰላሙና ነጻነቱ በፖለቲከኞች እንደተነጠቀ ይነግረናል። ቻፕሊን ማሳቅ ብቻ ሳይሆን ትልቅና አርቆ የሚያስብ ሰው እንደነበር ከፊልሙ መረዳት ይቻላል።
ለመጀመርያ ጊዜ ተናግሮ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ቁምነገር ያስተላለፈ ታሪካዊ ንግግር። መሪና ተመሪ ከመሆን ሰብአዊነትን እንድናስቀድም ይሰብከናል። ስልጣን ሳይሆን ሰዎች ልዩ ፍጥረታት መሆናቸውን ተገንዝበን ማገልገልና ማገዝ እንዳለብንም አበክሮ ይናገራል። የእግዚአብሔር መንግስትም በየ አንዳንዱ ሰው ውስጥ እንጂ በተወሰኑ የስልጣን ባለቤቶች የታጠረ እንዳልሆነ ይገልጻል። ባጠቃላይ የሰው ልጅ ነጻነት በጥቂት ሰዎች ምክንያት ሊገደብ እንደማይገባ ይነግረናል።የ አለም መሪዎችና ህዝቦች ይህንን መልዕክት በሚገባ ተረድተው ፍቅርን በማስቀደም ነገሮች ለማድረግ ቢሞክሩ በእውነት አለማችን የስቃይና የጭንቅ ቦታ ከመሆን ልትድን ትችላለች።
____________________________________________________________________________________________________________________________________
" አዝናለሁ፣ ንጉሠ ነገሥት ለመሆን አልፈልግም። ይህ የኔ ጉዳይ አይደለም። ማንንም መገዛትም ሆነ ማሸነፍ አልፈልግም። ሁሉም ሰው መርዳት አለብኝ ፡ ከተቻለ ፡ አይሁዳዊ፣ አሕዛብ ፡ ጥቁር ሰው ፡ ነጭ። ሁላችንም እርስ በእርስ መረዳዳት አለብን። የሰው ልጆች እንደዚያ ዓይነት ናቸው። እያንዳንዳችን በደስታ ውስጥ ለመኖር እንፈልጋለን፡ የእርስበርስን ጣር ማየት ሆነ እርሰበርስ መጠላላት አንፈልግም። በዚህ ዓለም ውስጥ ለሁሉም ሰው ክፍት ቦታ አለ፣ መልካሚቱ ምድርም ሀብታምና ለሰው ዘር ሁሉ በቂ ነገር አላት። የህይወት መንገድ ነጻ እና ውብ ነው። ግን መንገዱ አጥተነዋል። ስግብግብነት የሰው ልጅ ነፍስን በክሎታል። ዓለምን በጥላቻ በመያዝ፣ በመውደቅ፣ በመጥፋትና በደም መፋሰስ ውስጥ እንድንገባ አድርገውናል። የስልጣኔ ፍጥነት ጨምረናል ነገር ግን ራሳችንን ዘግተናል። ማሺኖች ሰርተናል ግን ፍላጎታችን ጨምሯል። በዕውቀታችን ተማምነናል፤ ጥበባችን አስቸጋሪና ደግነት የጎደለው ሆኗል። ብዙ እናስባለን ግን ስሜታችን ጥቂት ወይም የዛለ ነው። ከማሽኖች በላይ ሰው ያስፈልገናል። ብልህነት ብቻ ሳይሆን ደግነት እና መረጋጋት ያስፈልገናል። እነዚህ ባህሪያት ባይኖሩ ህይወት ጠበኝነት ያሸንፋታል፤ እናም ሁሉም ነገሮች ይጠፋሉ።
አውሮፕላን እና ሬዲዮ እርስ በርስ አቀራርቦናል። እነዚህ ፈጠራዎች በሰው ልጅ ዘንድ አንድነትና ወንድማማችነት እንዲኖር ይሰራሉ። አሁንም እንኳ ድምጼ በዓለም ላይ በሚሊዮን በሚቆጠሩ ህዝቦች ዘንድ ይሰማል፤ በሚልዮን የሚቆጠሩ ወንዶችና ሴቶች እንዲሁም ህጻናት የሰው ልጅ በፈጠረው መጥፎ ስርዓት ምክንያት ይሰቃያሉ፣ ይገደላሉ ይታሰራሉ።
መስማት ለሚችሉ ሰዎች፣ እላለሁ ፡ ተስፋ አትቁረጥ። አሁን በእኛ ላይ ያለው አሳዛኝ ስግብግብነት እንጂ የሰዎች ጥላቻ ያልፋል፣ እና አምባገነኖች ይሞታሉ፣ እናም ከሕዝቡ የወሰደዉ ኃይል ወደ ህዝብ ይመለሳል። እናም ሰዎች እስኪሞቱ ድረስ ነፃነት ፈጽሞ አይጠፋም።
ውታደሮች ራሳችሁን በባርነት በማሰር ምን ማድረግ እንዳለባቹ የሚነግርዋችሁ፣ ምን ማሰብ እንዳለባቹ የሚነግርዋችሁ፣ ስሜታቹ ምን መሆን እንዳለበት የሚያዝዋቹ፣ እንደ ከብቶች ምግብ በመስጠት የሚፈልጉትን እንድትፈጽሙ ለሚያዝዋቹ አምባገነን አለቆቻችሁ ራሳችሁን አሳልፋቹ አትስጡ ምክንያቱም እናንተ ሰዎች እንጂ ማሽን አይደላችሁም። ራሳችሁን ኢተፈጥራዊ እንደሆኑ ማሽኖች ለሚያዝዋቹ ሰዎች አሳልፋቹ አትስጡ። ማሽኖች አይደላችሁም፦ ከብቶች አይደላችሁም፦ ሰዎች ናችሁ። እናንተ በልባችሁ ውስጥ የሰውን ፍቅር አለ፤ ወታደሮች፦ ለባርነት አትዋጉ፦ ለነፃነት ተዋጉ።
በ ፲፯ ኛው ምዕራፍ በሉቃስ ወንጌል ላይ የእግዚአብሔር መንግሥት በሰው ውስጥ አለ ተብሎ ተጽፎአል፤ ይህም በአንድ ሰው ወይም በአንድ ቡድን ላይ ሳይሆን በመላው የሰው ዘር ውስጥና በአንተ ላይ አለ። ሰዎች ማሽን የመስራት ክህሎት አላቸው ፤ እንዲሁም ደስታን የመፍጠር ችሎታ አላችው። እናንተ ሰዎች ህይወትን ቆንጆና ነጻነት ያላት ማድረግ ትችላላቹ።
ከዚያም ፡ በዴሞክራሲ ስም ፡ ይህን ኃይል እንጠቀም ፡ ሁላችንም በአንድነት እንኑር። ወደፊት ወጣቱን ብሩህ ተስፋ የሚያይበትና ያረጁ ሰዎችን ደህንነት እንዲሰማቸው የሚያደርግ መሰረት እንጣል። ባለስልጣኖች ይዋሻሉ ያንን የተስፋ ቃል አያሟሉም። ፈጽሞ በተግባር ማሳየት አልቻሉም።
አምባገነኖች እራሳቸውን ነጻ ያደርጋሉ ነገር ግን ሕዝቡን ያዳዳሉ፦ አሁን የገባነውን ቃል ለመፈጸም እንዋጋ፦ ዓለምን ነፃ ለማውጣትና የዓለማትን መሰናክሎች ለማስወገድ ማለትም ጥላቻን ለማስወገድ መዋጋት እንፈልጋለን። የሳይንስ እና የትምህርት ዕድገት ወደ ሁሉም ሰው ደስታ የሚያመራውን የዓለምን አስተሳሰብ፣ ዓለምን እንዋጋ። ወታደሮች፦ በዴሞክራሲ ስም፣ ሁላችንም አንድነት እናድርግ፦"
No comments:
Post a Comment