EAR

አዲስ ነገር

Thursday, 15 March 2018

የዶክተር ወዳጄነህ ምስክርነትና ኢኩመኒዝም !



ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ



ትላንት በዓለም አቀፍ የትስስር መድረክ (Internet)  ላይ አንድ የተንቀሳቃሽ ምስል አስፈንጣሪ ወደ መጽሐፈ ገጽ መጋቢ አድራሻየ መጣ፤ ተንቀሳቃሽ ምስሉ በተሰጠው ርዕስ ትኩረቴ ስለሳበው አስፈንጣሪው በመጫን መመልከትና ማድመጥ ጀመርኩኝ። ተንቀሳቃሽ ምስሉ በ‹‹ኤክሶዶስ›› የመስኮተ ትዕይንት አዘጋጇ ቤቴልሄም ታፈሰ አቅራቢነት የፕሮቴስታንት እምነት ፓስተሩ ዶክተር ወዳጄነህ ማህረነ ጋር የተደረገ ቃለመጠይቅ ወይም ውይይት ነበር። ውይይቱ ከጅምሩ አንስቶ ቀልብን የሚስብና አስገራሚም ነበር። ምክንያቱም ከአንድ የፕሮቴስታንት ፓስተር የማይጠበቅ ነበር፤ ይህ እንዲሆን ያደረገዉም በጥላቻና በአለማወቅ አብዛኛው የፕሮቴስታንት እምነት አራማጅ ዘንድ እምነቱ የሚመሠረተው በቀጥተኛዋና የመጀመርያዋ ተዋህዶ ሃይማኖት ጥላቻ በመግለጽ ነው። ፕሮቴስታንት የምዕራባውያን ሰይጣናዊ እምነት በመሆኑ የሃገራችን አማኞችም ድርጊቶች ሆኑ አምልኮዎች ተመሳሳይ ናቸው።

‹‹ሁሉን ነገር ፈትኑ መልካም የሆነውን ያዙ።›› [፩ኛ ተስሎንቄ ፭፡፳፩]

እምነት ያዉም እውነተኛው እምነት የምንደርስበት ሰዎች በነገሩን ብቻ ሳይሆን ነገሮች በተገቢና በተለያዩ አቅጣቻዎች በማጥናት ይሆናል። እውነት የምንፈልግ ከሆነም የልባችን መሻት በመመልከት እግዚአብሔር ወደ እውነተኛው መንገድ ያደርሰናል። ይህም እኔ በግሌ ከኢ- አማኝነት ወደ ተዋህዶ እምነት ለመግባት ያስቻለኝ መንገድ ነው። ሆኖም በአብዛኛው የማውቃቸው የፕሮቴስታን እምነት ተከታዮች ግን ይህንን አላስታወልኩም። ፓስተር ወዳጄነህ ያደረገው ግን እውነትን መመርመር ነበር። ፈጣሪም እውነት እንድንመረምር ይፈቅዳል በግድ እንድናምን አይፈልግምና። የፕሮቴስታን እምነት አማኞች ይህንን መንገድ ከጥላቻና ከጭፍን ዕውቀት ወጥታቹ ብታደርጉት ብርሃኑ ይገለጥላቹሃል። የፓስተር ወዳጄነህ ምስክርነት የሚከተለው ነበር
ኦርቶዶክሰ  ኢየሱስን  አታውቅም  ማለት ስህተት  ነው፤ ቅድስት ድንግል ማርያም  በህቱም  ድንግልና ቅድመና ድህረ ውልደት  ድንግልናዋ  አልተለወጠም፤ ቅድስት  ድንግል  ማርያም  ቅደስናዋንና  ለእኔም  እናቴ መሆኗን  አምናለሁ  እቀበላለሁ፤ ኦርቶዶክሶች  እሮብና  አርብ  ሲጾሙ ኢየሱስን  እያሰቡ ነው፤ ከኦርቶዶክሶች ዘጠኝ  በአሎች  ስምንቱ  ኢየሱስን  የሚያስቡ ናቸው፤ አብይ  ጾም  ኢየሱስ  ክርስቶስ  ስለጾመው  ነው የሚጾሙት፤ መላእከትን  በጣም እውደቸዋለሁ  አከብራቸዋለሁ፤ መላእክት  እኔ እልካለሁ ለሚሉ ፓስተሮችም  መላእክት ለሰው በፍጹም  አይላኩም የጎረምሶች ድፍረት….”

በተጨማሪም የመርሐ ግብሩ አቅራቢ ቤቴልሔም አብዲሳ፤ እውነት የምትፈልግ መሆንዋ ከጥያቄዎችዋ መረዳት ይቻላል። በዚህ ምክንያትም ወደ እውነት እየቀረበች ነው። የቤቴልሔም ምስክርነትም አስደናቂ ነበር ፦
 አሁን  ላይ፤ በፊት  እንኳ  እንደዚያ  አልነበርኩም፤ አሁን  እድሜዬም  መጨመር  ሲመጣ፤ በጌታ  ቤት መቆየት  ሲመጣ  የወንጌላውያን  አማኞች  ኢትዮጵያ  ውስጥ  ያሉት  ሌላውን  አላውቅም፤ ይህን  ኃይማኖት ሲመሰረቱ የኦርቶዶክስ  ቤተክርስቲያንን  እየሰደቡ  ነው  የመጡት፤ እየረገሙ  ነው  የመጡት፤ ሃይማኖት እንዲጠላ  እስከዛሬም  ድረስ  የተደረገው  በዚህ ስድብ  ምክንያት ነው፤ ምክንያቱም  ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን  በአብ  በወልድ  በመንፈስ   ቅዱስ ስም  ኦርቶዶክሶች  ያምናሉ፤ ምንም  ክህደት  የለውም  ስለ ሥላሴ  እንደውም  በተለየ  ሁኔታ  አይደለም  እንደውም  በቆንጆ  ሁኔታ የ ሚያብራራ  የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን  ቀኖና  ይመስለኛል፡፡ እና  ቅዱሳኖችን  እየረገመ፤ እያጣጣለ፤ እየሰደበ፤ ማርያምን  እንደዛ እያደረገ  ነው  የመጣው፡፡
.
የኔን  አሁን  ለምሳሌ ልንገርህ፤ እኔም  ያው  ከእነሱ  ውስጥ  አይደል  የተገኘሁት፤ ልክ  ጌታን  እንደተቀበልኩ፤ ሃይማኖቱ  ውሰጥ  አልነበርኩም  መጀመሪያውኑ  በእርግጥ፤ የኦርቶዶክስ  እምነት ተከታይ ነኝ  ልልህ  አልችልም፤ ቤተሰቦቼ  ናቸው  ተከታይ  የነበሩት፤ እኔ  ወጣትነት  ጊዜዬን  ስጨፍር  ምናምን ነው ያሳለፍኩት፤ ጌታን  እንዳገኘሁ፤ ጀመርኩ  እሱን  ነው  የጀመርኩት፡፡
.
ቤቴ  ውስጥ  የጀመርኩት  እሱን ነው፤ እእእ  ወደዛ  ማርያም  የምትሉት  ምናምን  ማለት  ጀመርኩ፤ እእእ ቅዱሳንን  ማንጓጠጥ፤ በታቦት  በሚያንቡት  ሁኔታ መሳለቅ  ጀመርኩ፤ ቤተሰቦቼም  መደንገጥ ጀመሩ፤ የሚጠላ  ሃይማኖት  ነው መጀመሪያውኑ፤ መደንገጥ  ጀመሩ፤ እየሳቀቁ  መጡ፤ በጣም  ነው የምናገረው፤ ከዚያ  ደግሞ  ወዲያውኑ  ጌታን  ተቀበሉ፤ አልፈልግም  ይለኛል  አባቴ፤ አልፈልግም፤ ትሞታለህ  ሲኦል ትገባለህ፤ ልግባ  እንደዚህ  ከምሆን፤ እንደ አንቺ  ከምሆን  ልግባ፤ በኋላ  ደግሞ  ቀጠልኩበት  በዛው፤ ማታም ቡናም  ሲፈላም፤ የማልተው  ጉዳይ  የእነሱን  ነገር  እምነት  መስደብ  ነበር፤ ስለዚህ  ከቤት  አውጥተው ጣሉኝ  ማለት ነው፡፡ አሁን  እኔ ስለ ጌታ  ብዬ  ነው የተሰደድኩት  ብዬ  ለረዥም  ጊዜ  አስብ ነበር፤ አሁን  ነው  ምላሴ  ያመጣብኝ  ነገር  እንደሆነ  የሚገባኝ እና፤ እየሰደበ  እረገመ  እያጣጣለ  ነው የመጣው…… ”


የፓስተር ወዳጄነህ ምስክርነት ብዙ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ሊያስደነግጥ እንደምችል ምንም ጥርጥር የለውም፤ ምክንያቱም የሃገራችን የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች እንደወረደ የምዕራባውያን እምነት ስለሚቀበሉ እውነቱን መርምሮ የሚመጣ ሰው ለመቀበል ይከብዳቸዋል።

ሆኖም ፓስተር ወዳጄነህ ምስክርነት ፍርሽ የሚያደርግ ንግግር ትኩረት ሊደረግበት ይገባል። ይህም እኔ ኦርቶዶክስ አይደለሁም፣ ፕሮቴስታንት አይደለሁም፣ ካቶሊክ አይደለሁም ‹‹የኢኩመኒዝም›› እምነት ተከታይ ነኝ የሚል አዳናጋሪ ቃል ነው።

‹‹ኢኩመኒዝም›› ምንድን ነው ?

‹‹ኢኩመኒዝም›› ፓስተር ወዳጄነህ እንደገለጸው ሳይሆን፤ የዓለም ሰው የፈጠራቸውና በእየሱስ ክርስቶስ ደም በተመሰረተቺው ቀጥተኛዋ የተዋህዶ ሃይማኖት አንድ በማድረግ በመበረዝ እንድትጠፋ በዓለም ቁንጮ የሰይጣን አምላኪዎች ኢሉሚናቲ የተያዘ ሰይጣናዊ ዕቅድ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። መቼም ቢሆን ብርሃን ከጨለማ ጋር አንድ ሊሆን አይችልም። ሃይማኖት አንድ ነች እሷም ቀጥተኛዋ ተዋህዶ።

ኢኩመኒዝም ለማስፈጸው የተመሰረተው የኢሉሚናቲዎች ቅርንጫፍ የሆነው የዓለም ቤተክርስትያናት ህብረት የዚህ ዕቅድ አስፈጻሚ ነው። በለፉት ዓመታት በተዋህዶ ቤተ መቅደስ የተፈጸሙት አስነዋሪ ተግባራት የዚህ ውጤቶች ናቸውና ጥንቃቄ ያስፈልጋል።


ሓሙስ  መጋቢት ፡2010 ዓመተ ምሕረት

No comments: