EAR

አዲስ ነገር

Friday, 6 April 2018

የክርስቶስ ትንሣኤ እና ኢስተር



ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ


በጌታችንና መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ከተፈጸሙት ክህደቶች፣ ኢትዮጵያዊው መልኩ በመቀየር ፈረንጅ ወይም ነጭ መልክ እንዲኖረው አድርገው ማቅረባቸው፣ መስከረም የነበረው ልደቱ ወደ ታኅሣሥ ፳፰/፳፱ መቀየሩ፣ ፈጣሪነቱና ፈራጅነቱ ለመሻር "አማላጅ"  በሚል ተልካሻ ምክንያት ፍጡር አድርገው የሚያቀርቡት አካላት መኖራቸው የተወሰኑ ናቸው።

በተቃራኒው ኢትዮጵያዊው የሆነው እየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤው በተገቢ መንገድ የሚያከብሩት ኢትዮጵያውያን (ተዋህዶ) ናቸው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ የተነሣበትን የመታሰቢያ ዕለት እኛ ኢትዮጵያውያን በጥልቅ መንፈሳዊ የደስታ ስሜት እናከብራታለን። ይህም ያለምክንያት አይደለም ይህችው ዕለት ፈጣሪ ሰው ኾኖ ወደዚህ ዓለም የመጣበትን ዓላማ ከግብ አድርሶ የፈጸመባት ማለትም የሰው ልጆችን የዘር ጠላቶች ደምስሶ ለእኛ ዘለዓለማዊ ድልን ማለትም የሰው ልጆችን የዘር ጠላቶች ደምስሶ ለእኛ ዘለዓለማዊ ድልን ያቀዳጀባት፡ ይዅም ከዲያብሎስ የአገዛዝ ባርነት አውጥቶ በእግዚአብሔር ነጻ ልጅነት የኃጢአትን ቀንበር አስወግዶ ለንስሓ ጽድቅ የሞትን ፍዳ አጥፍቶ ለዘለዓለም ሕይወት ጸጋ እንድንበቃ ያደረገባት ቀን በመኾኗ ነው።

ይህንን በዓል በምዕራባውያን ዘንድ "ኢስተር" እየተባለ የሚከበር ቢሆንም ኢትዮጵያውያን ከምናከብረው የትንሣኤ በዓል በፍጹም አንድ ዓይነት መነሻ ትርጉም የለዉም። እኛ ኢትዮጵያውያን "መልካም የትንሣኤ በዓል!" ከማለት "ሃፒ ኢስተር-Happy Easter" ማለታችን ማቆም አለብን። ምክንያቱም ኢስተር እውነተኛው የክርስቶስ ትንሣኤ በዓል አይወክልም።

የምዕራባውያን "የኢስተር በዓል" ቀጥታ ከጥንታዊው የአሲርያንና ባቢሊሎናውያን "የፅንሰትና ወሲብ" አምላክ(ጣዖት) "ኢሽተር - Ishter" የሚገናኝ ነው። ከጊዜያት በኃላ ይህ "የኢሽተር በዓል" በሮማው ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ዘመነ ንግሥና ክርስትያናዊ መልክ እንድይዝ በማድረግ የክርስቶስ ትንሣኤ የሚገልጽ እንዲመስል ተደርጎ በይፋ ታወጀ፣ በዚህ ምክንያትም ይህ አረማዊ በዓል "የክርስቶስ ትንሣኤ" እንዲመስል ተደረገ። እኛ ኢትዮጵያውያን ለዓለም ሁሉ መሠረት የሆነ ስርዓት አለንና እውነተኛውን የክርስቶስ ትንሣኤ "ሃፒ ኢስተር - Happy Easter " በሚል የመልካም ምኞች መግለጫ ልንበርዘው አይገባም።

 ኢትዮጵያዊነት ታላቅ ክብር ነው !

ቅዳሜ መጋቢት 29, 2010  ዓመተ ምሕረት

No comments: