EAR

አዲስ ነገር

Wednesday, 23 May 2018

ነገረ ፡ እኅተ ማርያም !





ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ

ብዙ ሰዎች፡ ለምን የእኅተ ማርያም መልዕክቶች እንደምጋራቸው ይጠይቁኛል፤ እኔም መልስ ለመስጠት እሞክራለው። ስለ መንፈሳዊ ነገሮች ማጥናት ስጀምር ወደ ዓመታት ገደማ ይሆነኛል። በዚህ ጊዜ ተዋህዶ ሃይማኖት ብቸኛዋ የሰው ልጅ መዳኛ መሆንዋ አምኜ ራሴን በተዋህዶ መንገድ ለመጓዝ ሁሌ ጥረት ላይ ነኝ።

ቅድሱ መጽሐፍመንፈስን መርም” በሚለው መሰረት፡ የእኅተ ማርያም መልዕክቶችም በራሴ መንገድ በመመርመር፡ እውነተኛ መሆናቸው መረዳት ችያለው። ለዓመታት ስለ ሰላቢ እጆች (ኢሉሚናቲ) ሴራዎች በማጠናበት ጊዜ የደረስኩባቸው እውነታዎች በድረ ገጾቼ ስለጥፋቸው የነበሩ እውነቶችና በኢትዮጵያ ላይ እየሰሩት ስላሉ ሴራዎች የእኅተ ማርያም መልዕክቶች ላይ በመስማቴ እረፍተ ያገኝሁበት እና ይበልጥ ሴራቸው ለማጋለጥ ስለረዳኝ ነው።

የኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተክርስትያን አስመሳይ የአውሬው-666 አገልጋዮችና ጳጳሳት፣ ዲያቆናት፣ መምህራን ተሞልታ የፖለቲካ ምሽግ ሆና ምዕመን ግራ ተጋብቶ አባትና እናቱ እንደሞቱበት ህጻን ሲንከራተት ሲታይ እኅተ ማርያም እውነተኛው የተዋህዶ ስርዓት በመግለጥዋ ደስታ ይሰማኛል። በተለይ በክፉ መንፈስ የተያዙ አገልጋይ ነን በማለት፥ ከኛ በላይ አዋቂ የለም በማለት የመምህር ግርማን ወንድሙ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ሲቃወሙ የነበሩ ሰዎች ላይ በመቃዎምዋ በመገሰጽዋና የመምህር ግርማ አገልግሎት የመንፈስ ቅዱስ መሆኑ መግለጽዋ በሚገባ እንዳምናት አድርጎኛል። አውሬው አገልጋይ የሆነውና ኢትዮጵያን ለማጥፋት በፖለቲካ መንገድ የመጣው የኅወሃት መንግሥት መቃወምዋ ተጨማሪ የድጋፍ ማስረጃ ሆኖልኛል።

እስቲ የተወሰኑ የእኅተ ማርያም መልዕክቶች በማንሳት እንመልከት፦

“ወሊድ መከላከያ የምትጠቀሙ ከሆነ 666 ዘንዶውን/አውሬውን ለመከተል በፈቃዳችሁ መርጣችኋል ማለት ነው።”

ስለዚ ጉዳይ፡ በተደጋጋሚ በኢትዮጵያ አውታር”ናሰላቢ እጆች” ድረ ገጾቼ በስፋት የጻፍኩበት ጉዳይ ነበር።
ይህ የእህታችን ሌላ ታላቅ ትምህርት ነው። የተቀበለችው መረጃ ለአገራችን እጅግ በጣም ጠቃሚ ከሆኑት መረጃዎች መካከል አንዱ ነው። ይህን መረጃ ዓብያተክርስትያናቱ በየዕለቱ ስራችን ብለው በሰበካዎቻቸው ወቅት ደግመው ደጋግመው ሊናገሩልት ይገባል።
እህቶች እባካችሁ የወሊድ መከላከያውን በጭራሽ አትጠቀሙ፤ ለማስወረድማ የምታስቡት ጉዳይ አይደልምብለው በየቀኑ መናገር ይኖርባቸዋል። ግማሽ ደቂቃ እንኳን የማትወስድ አንዲት ዓረፍተ ነገር ናት።

ከ666ቱ አውሬ ጋር የተመሳጠሩት መገናኛ ብዙሃን ለባዕዳውያኑ የወሊድ መከላከያና ህጻናት ገዳይ ድርጅቶች ማስታወቂያ ይሠራሉ እንጂ ለእህቶቻችን ማስጠንቀቂያ ሊሰጡ ፈቃደኞች አይደሉም።

7500 አመታት በላይ ትክክለኛውን አምልኮተ እግዚአብሔር የምትፈጽመው ሃገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ ከእግዚአብሔር በመመረጥዋና የእግዚአብሔር ጥበቦች መገኛና ማስፈጸምያ በመሆንዋ በተለያዩ ጊዜያት ይህንን የሚያውቁ ባዕዳውያን ሃይሎች ወደ ሃገራችን በመምጣትና በርቀትም ጥበብዋን ለመዝረፍና ጥንታዊው ኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ ሃይማኖትዋን ለመበረዝ የተለያዩ የሰይጣን አምላኪዎች የሆኑ የምስጥር ማህበራት ጥረት አድርገዋል። በእግዚአብሔር ጥበቃ እስከ አሁን ብት ዘልቅም አውሬው(666) ግን ተቃውሞውና ሴራው ለማስፈጸም እስከ መጨረሻ እንደሚጥር የታወቀ ነው።

ከዚህ ጋር በተያያዘ የምስጥር ማኅበራት ሴራ አስፈጻሚ የሆነው የዓለም ጤና ድርጅት ፕሬዝዳንት ኢትዮጵያዊው ቴዎድሮስ አድሃኖም እንደሚሆን አስታውቄ ነበር። የህዝባችንን ቁጥር በጦርነት፣ በርሃብ፣ በበሽታ፣ በኤድስ ሊቀንሱት አልቻሉም፤ ስለዚህ አሁን የመጨረሻው ጦርነት ላይ ገብተዋል፤ በዚህም ሁለት ወፍ በአንድ ድንጋይ ለመምታት ቆርተው ተነስተዋል፤ ይህም፦ ቁጥሩን መቀነስ እንዲሁም የሚወለዱትን በአውሬው መንፈስ ቁጥጥር ማስገባት። በዚህ ምክንያት የእኅተ ማርያም መልዕክት እውነት መሆኑ እቀበላለው።

“ኢትዮጵያ ለሌሎች ትዕዛዝ ትሰጣለች እንጂ ከነጮች ትዕዛዝ አትቀበልም።”

መልዕክቱ ምንም እንከን አይወጣለትም፤ % ትክክል ነው። አገር ቤትም ሆነ ውጭ ያሉት ፖለቲከኞች ሁሉ በእግዚአብሔር ሥርዓት ውስጥ ቢሆኑ ኖሮ ማንንም ምንንም ባልፈሩና የነኞችና አረቦች ባርያ ባልሆኑ ነበር። ባንዲራውንስ አስገድደዋቸው አይደል፦፧

በተለይ ፀረክርስቶሷ ታሪካዊ ጠላታችን ቱርክ ባገራችን ላይ አሁንም እየፈጸመች ያለችው ወንጀል ደም እንባ የሚያስለቅስ ነው፣ አባቶቻችንና እናቶቻችንን ከመቃብር የሚያስነሳ ነው። ከአረቦች ጋር ሆና ውሃውን፣ ጤፉን፣ ዱቄቱን፣ ከብቱን፣ ዘይቱንና ስኳሩን እየመረዘች ነው። ምዕራባውያኑ በኪኒን፣ መርፌና ቴክኖሎጂው፣ እስማኤላውያኑ ደግሞ በሕዝብ መሃል ሰርገው ገብተው በምግባችን፣ መጠጣችን እና ልብሳችን ላይ ዘምተዋል።

በተጨማሪ ቱርክ የጦር ሠራዊቷን በሶማሊያ እና ሱዳን በማከማቸት ላይ ትገኛለች፤ ግብጽን እና ሳዑዲ አረቢያን እንደቀድሞው ለመቆጣጠር ስለምታልም፤ ዋናው ትኩረቷ አባይና ጣና ሃይቅ ላይ ነው። በጣና ሃይቅ የታየው አረም በቱርኮች የተዘራ ነው ቢሉን አይድነቀን፤ ወደ አዲስ አበባ የሚበረው የቱርክ አየር መንገድም ልክ በጣና ሃይቅ ሰማይ በኩል ነው በየቀኑ የሚያልፈው። በሰሜን ሶርያ ባለፈው አርብ ብዙ ወታደሮች የሞቱባት ቱርክ በኩርዶች ላይ የኬሚካል ቦምቦችን ተጠቅማ እንደነበር ተለጿል፤ የኔቶ አባል በመሆኗ ምዕራባውያኑ ጸጥ ብለዋል። ልፍስፍሱና ጉረኛው የቱርክ ህዝብ፡ በቅርቡ ከሰማይ እሳት ይወርድበታል፦

ቤተመንግስት ውስጥ የገባው አንዱ ዘንዶም ከጣልያን ወረራና ወረራው ካስከተለው የአፄ ኃይለ ሥላሴ የእንግሊዝ አገር የስደት ኑሮ ጋር የተያያዘ ነው።

ደጋግሜ የምለው ነው፤ ኢትዮጵያ የሁሉም ኢትዮጵያውያን አገር ናት፤ እግዚአብሔር በሰጠን አገር ሌላ ሕዝብ ወይም የውጭ ኃይል ዕጣዋን የመወሰን መብት የለውም። አሁን ያለው በቋንቋ ላይ የተመሠረት የክልል ሲስተም መቀየር ይኖርበታል፤ ሬፈረንደም በፍጥነት ተካሄዶ የቀድሞዎቹ ክፍለ ሃገራት መመለስ አለባቸው።


“ቡና፣ ጫት፣ ሺሻ፣ ሰንደል፣ ጥንቁልና፣ ቀይ መጋረጃ፣ የኢሬቻ በዓል፤ ሁሉም ከሰይጣን ናቸው።”

እኅተ ማርያም፡ እውነተኞቹ አባቶች፡ መናገርና ማስተላለፍ የነበረባቸው መልዕክት፡ እግዚአብሔር ከፋሽኑ ዓለም አውጥቶ እንድታስተላልፍ ስላደረገ አመሰግነዋለው። እግዚአብሔር ሰው አይንቅም፤ ታማኝ አገልጋይ ይፈልጋል እንጂ።

እኛ ክርስቲያኖች የብሔራዊ ስሜት ሳይገድበን የክርስቶስ ከሆኑ ወንደሞቻችንና እህቶቻችን ጋር እንድናብር እንታዘዛለን።

መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ፡ “ይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና” ይለናል።

ኮራጁ ዲያብሎስ ፀረ–ክርስቶሱም የራሱ የሆኑትን ሁሉ ለዓላማው በመላው ዓለም በጋራ ሰብስቧቸዋል፦

ለምሳሌ ኮሙኒዝም “የዓለም ወዛደሮች ሁሉ ተባበሩ” በሚል መርሆ አመጸኞቹን ግራኞች ያስተባብራል፣ እስልምና ለ “ኡማችን/እናታችን” በሚል መርሆ በመላው ዓለም ያሉትን ግራኝ ሙስሊሞች ሁሉ ያስተባብራል፣ ዓለማዊነት/ሴኩላሪዝም ደግሞ ‘ኢ–ዓማናይ‘ የሆኑትን ግራኝ ልጆቹን በመለው ዓለም ያስተባብራል። ዓለማውያኑ ምዕራባውያን ሙስሊሞችን አምልኳቸውን ወደ አገሮቻቸው ሲያስገቡ፣ ሙስሊሞቹ ደግሞ ወደ አገሮቻቸው የምዕራባውያኑን አምልኮና የገባያ ማዕከላት ያስገባሉ፤ ዓብያተ ክርስትያናትን ግን ይከለክላሉ።

እነዚህ ሦስት ቡድኖች የተለያየ የሚመስል መንገድ ቢከተሉም ግን የሁሉም መንፈስ አንድ ዓይነት ነው፤ ሁሉም የፀረ–ክርስቶሱን ልብስ ለብሰዋልና። ምንም እንኳን ተልዕኳቸው ዓለም አቀፋዊ ባሕርይ የያዘ መስሎ ቢታይም፤ እግረ መንገዳቸውን ግን “ብሔራዊ” ማንነታቸውን በመላው ዓለም ለማሰራጨት ነው የተነሱት፦ ኮሙኒዝም እና ሴኩላሪዝም የምዕራባውያኑን ባሕል፣ ቋንቋና አምልኮት፤ እስልምና ደግሞ የአረቡን ባሕል፣ ቋንቋና አምልኮት ለማስፋፋት ይታገላሉ።

በአገራችን የሚታዩት ፀረ–ኢትዮጵያዊነትና ፀረ–ተዋሕዶ ዘመቻዎች የእነዚህ ሦስት ቡድኖች ወኪሎች መሆናቸው በግልጽ የሚታይ ነው። አኩሪውን ክርስቲያናዊው ኢትዮጵያዊ ማንነታችንን ለማጥፋት በክህደት ወሃ የተጠመቁት ወገኖቻችን ለዓለም አቀፋዊው የሉሲፈራዊ ሥርዓት እራሳቸውን አሳልፈው መስጠታቸው በጣም የሚያሳዝን ነው። ያውም ለጊዚያዊ ጥቅም ሲሉ፦

የአረቡ፣ የህንዱ፣ የሱዳኑ፣ የሶማሌውና የቻይናው መጉረፍ፣ ጎረቤት አገሮች እየፈራረሱ ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ መደረጉ፣ እንዲሁም የጠንቋዩ፣ የቃልቻው፣ የዕጹ፣ የሺሻው፣ የቡናው ወዘተ ባህል መስፋፋት በኢትዮጲያዊነት ላይ የተጠነሰሰ ሤራ መኖሩን ይጠቁመናል። ኢትዮጵያዊነት = ክርስትና፦
እህቶቻችንን ወደ አረብ አገር በመላክ በጋኔን እንዲሞሉና ወደ ኢትዮጵያም ተመልሰው ቡናውን ለሰዎች በየቦታው እንዲያጠጡ ይደረጋሉ፣ ሰይጣናዊውን የኢሬቻ በዓል ብሔራዊ በዓል ለማድረግ ይሞከራል፣ (መስቀልን ለምተካት … በመስቀል ክብረ በዓል ማግስት) ፣ የተዋሕዶ ወጣቶችን በእናት ቤተክርስቲያናቸው መንፈሳዊ መዝሙሮችን እንዳይዘምሩ ሲተናኮሏቸው፤ የራያ ጨፋሪዎች ግን በየቤተክርስቲያኑ ሰተት ብለው እንዲገቡና ባሕላቸውን እንዲያስተዋውቁ ይታዘዛሉ።

ይህን ከባድ የፈተና ጊዜ የመወጣቱ ኃላፊነት ያለብን እኛ እያንዳንዳችን ነን፤ በግላችን፡ ከታች ወደላይ ማድረግ የሚገባንን ሁሉ ማድረግ ከቻልን የጠላቶቻችንና ተባባሪዎቻቸው ሤራ ብዙም ሊያሳስበን አይገባም።
እስኪ ለጊዜው ከቡናው፣ በተለይ ደግሞ በጣም አደገኛ ከሆኑት ሺሻና ጫት እንቆጠብ፣ (እንደ አዲስ አበባ ከፍተኛማ በሆኑ ቦታዎች ጫትና ሺሻ የጤና ጠንቅ ናቸው)። እስኪ በእምነት ከማይመስሉን ጋር መደበላለቁን እናቁም። እነዚህን በእጃችን ያሉትን ቀላል ነገሮች እያንዳንዳችን ማድረግ ካልቻልን ሌላውን መውቀስና መኮነን መብት ሊኖረን አይገባም።


ኅሙስ ግንቦት 16, 2010 ዓ.ም.

2 comments:

Unknown said...
This comment has been removed by the author.
Unknown said...

እምነትህ ለራስህ ነው ። የሷን ቃል ማመንህን ለሰው መስበክና እንዲያምኑ አታድርግ እውነትን እግዚአብሔር ይገልፃል ። እምነትህን በትህግስት ጠብቅ ። ከቃል ባለፈ ደግሞ እኔ የምመክርህ በአካል ቤቷ ተገኝተክ መርምር ። በቃል ማር የሚያዘንቡ ታህምራትን የሚያደርጉ እንደሚመጡስ አላነበብክም ? ልባቸው እሾህ ሆና አፋቸው ለስላሳ ቃልን የሚዘራም እንደሚመጡ አልተነገረህም ?