EAR

አዲስ ነገር

Monday, 11 June 2018

እግር ኳስና አዕምሮ ቁጥጥር !


ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ

የእግር ኳስ ዓለም ዋንጫ ፡ ሊጀመር ጥቂት ቀናት ቀርቶታል። በአሁኑ ጊዜ ፡ እግር ኳስ ፡ ለኢትዮጵያውያን ፡ ማንነታችን እያስረሳን ይገኛል። ፳፬ ሰዓት ፡ የምዕራባውያን ፡ እግር ኳስ ፡ የሚመግቡን መገናኛ ብዙሃንና ጋዜጠኞች ፡ እንደ አሸን በበዙበት ፡ ስለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊ ማንነት ፡ ደፍሮ ለመናገርና ለማስተማር የሚሞክሩት መርሐ ግብሮች ግን ጥቂትና ዘላቂት የሌላቸው ናቸው። የምዕራባውያን እግር ኳስ የሚደሰኩርልን አካላት ፡ በተለይ የወጣቱ አዕምሮ በመቆጣጠር ፡ እግር ኳስ ፡ ከመዝናኛነት አልፎ ትልቁ የህይወታችን ክፍል በማድረግ  ፡ ትኩረት ልንሰጥበት የሚገባን ጉዳዮች ፡ ያለ በቂ ትኩረት እንድናልፋቸውና ምዕራባውያን ላዘጋጁልን የባርነት ወጥመድ ፡ተገዢ እንድንሆን እያደረገ ይገኛል።


በአውሮፓና ደቡብ አሜሪካ ውስጥ ፡ የእግር ኳስ ፡ ጨዋታዎች በኢሉሚናቲ ቁጥጥር ሥር ከወደቁ ፡ አንድ ክፍለ ዘመን ገደማ ሆኖታል። ከሣምንት ወይም ቀናት በመንግሥት ሥራ የባርነት ሥርዓት ውስጥ ፡ ለቆዩ ሰራተኞች (ባርያዎች) ፮ኛው ወይም ፯ኛው ቀናቸው እግርኳስ እንዲመለከቱ በተለያዩ መንገዶች ተጽዕኖ በማድረግ ስለ ሚደግፉት ቡድን መረጃ በብዛት እንዲያገኙና በጨዋታው ውስጥ ዳኛው ስለወስናቸው ውሳኔዎችና ሌላ ተያያዠ ጉዳዮች በማንሳት ፡ ቀጣይ ወይም የሥራ ቀናት ስለነዚ ነገሮች እንዲያወሩና እንዲያስቡ በማድረግ ፡ ሰራተኛው ወይም በጠቅላላ የዓለም ህዝብ ፡ ለህይወቱ ወሳኝ ስለሆኑ ነገሮች እንዳያስብ ፡ ዘላለም በባርነት እንዲኖር ሊያደርጉት ችለዋል።

በቢልዮን የሚቆጠር ህዝብ  ፡ ሴረኞች ባሴሩት ጦርነት ያለ ኃጥያቱ  ፡  በተለይ ህጻናት ጭንቅ ውስጥ ባሉበትና እንዲሁም ብዙ የዓለማችን ህዝብ ፡ ዕለታዊው የምግብ ፍላጎቱ ሟሟላት ሳይችል   በረሀብ በሚሞትበት ዓለም በቢልዮን የሚቆጠር ገንዘብ በማውጣት   የእግርኳስ ድግስ በማዘጋጀት ፡ የዓለም ህዝብ ማደንዘዝ  ፡  ሰይጣናዊ ሥራ እንጂ ሌላ ምንም ሊሆን አይችልም።

ሰኞ ሰኔ 4, 2010  ዓ.ም

No comments: