ከ
፭ ዓመት በፊት፡ ከነበረኝ “የማሪዋናና ትንባሆ” የማጨስ እንዲሁም “ጫት” የመቃም ሱስ፡ሙሉ በሙሉ፡
“በቅዱስ፡ሚካኤል” አምላክ፡ ፍቃድ ነጻ የወጣሁበት ነበር። እግዚአብሔር፡ ሰውን የፈጠረው ፍፁም ነፃነትን ሰጥቶ
ነው።ነገር ግን፡ ሰው ነፃነቱን አላግባብ በመጠቀሙ፡ የኃጢአት ባሪያ ሆነ።ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፡ በመስቀል ዋጋ
ከፍሎ ደግሞ፡ ነፃነትን ሰጠን። “በነፃነት ልንኖር ክርስቶስ ነፃ አወጣን” [ገላ.፭፥፩]። ዛሬ ላይ ደግሞ፡
ለኃጢአት፣ ለሥጋ ፈቃድ፣ለኑፋቄ፣ ለባዕድአምልኮ፣ ለዘረኝነት እና ለ ክህደት እንዳንገዛ፡ በነፃነት እንኖር ዘንድ፡
አምላካችን ይጠራናል። “ወንድሞቼ ሆይ ፥ እናንተ ስለ ነፃነት ተጠርታችኋል፤” [ገላ. ፭፥፲፫]
ከነበሩኝ ሱሶች ተላቂቄ እንድጸና ካደረጉኝ ነገሮች፡ መምህር ግርማ ወንድሙ፡ በየሳምንቱ በራድዮ አቢሲንያ ሲያስተምሩት የነበረ፡ ነፍስ የሚዘራ ድንቅ ትምህርት ነበር። ይህ የሚያውቆው በስቃይ ያለ ሰው ብቻ ነው። አዋቂ ነኝ፡ ከኔ በላይ የሚያውቅ የለም፡ የሚል መምህር እውነቱ ሊደርስበት አይችልም። መምህር ግርማን፡ የሚቃወሙ አማኝ ነን የሚሉ ሰዎች ሳይ በጣም አዝናለው። ፈጣሪ፡ ከትዕቢታቹ አላቆ እውነቱ ይግለጥላቹ።

No comments:
Post a Comment