EAR

አዲስ ነገር

Saturday, 27 October 2018

የላሊበላ ቅርሶች ለምን ማውደም ተፈለገ፧




ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ

"እጅግ በጣም አስደናቂና ከፍተኛ የጥበብ ችሎታ የሚታይበት ዕፁብ ድንቅ ሥራ በመሆኑ ያየሁትንና የተሰማኝን ሁሉ ነገር ብጽፍ የሚያምነኝ ስለማይኖር በእግር ተጉዘው ሄደው በአይናቸው ለሚያዩት ትቼዋለሁ" ላሊበላን ለመጀመሪያ ጊዜ የጎበኘ አውሮፓዊ ቄስ ፍራንሲስኮ አልባሬዝ የተናገረው፡፡

የላሊበላ ቅርሶች ለምን ማውደም ተፈለገ፧ ምዕራባውያን ጥንተ ጠላቶቻችን ሀገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን በመቆጣጠር እግዚአብሔራዊ የሆኑ መንፈሳዊ ሃብቶችዋ በመውሰድ በጠቅላላው የሰው ልጅ ላይ መቀዳጀት ለሚፈልጉት የበላይነት ደረጃ ለመጠቀም ይፈልጋሉ። ይህ ካልሆነ በኢትዮጵያ ያሉ ድንቅ መንፈሳዊ ሃይል ያላቸው ሃብቶችና ጥበበች ማጥፋት ሌላው አማራጫቸው ነው።

የላሊበላ አብያተ ክርስትያናት በቅዱስ ላሊበላ አነሳሽነት በቅዱሳን መላዕክት ተረዳኢነት የተሰሩ ትንግርታዊ፣ ለዓለም ህዝብና ለተመራማሪዎች እንቆቅልሽ ሆነው ለዘመናት ዘልቀዋል። ይህንን ጥበብ የማይዋጥላቸው የምስጥር ማህበረሰብ አባላት በተለያዩ ዘመናት ለመስረቅና ለማጥፋት ወደ ኢትዮጵያ ዘልቀው ገብተዋል።
 
የቅዱስ ላሊበላ አብያተ ክርስትያናት አሁን የተጋረጠበት የመውደም አደጋም በተለያዩ ጊዜያት የተፈጸመበት ሴራ ውጤት ሊሆን ይችላል። አብያተ ክርስትያናቱ ለመታደግ መንግስሥት እያሳየው ያለው ቸልተኝነት ደግሞ ሌላው እንቆቅልሽ ነው።
እነዚህ የጨለማ ገዢዎች ባስቀመጥዋቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን  በተግባር ግን ኢትዮጵያዊነታቸው የካዱ የዘመኑ የባዕዳን ሃይላት አገልጋዮች ተጨማሪ ጉዳት ሆነዋል።
 
ምዕራባውያን በጋቱን የፌደራሊዝም ስርዓት በተፈጠረው የዘረኝነት በሽታ ምክንያት ኢትዮጵያዊ አንድ በመሆነ እነዚህ ውድ ሃብቶቹ እንዳይታደግ ተጨማሪ ችግር ሆነበታል።

No comments: