EAR

አዲስ ነገር

Sunday, 1 November 2020

Facebook ከ ፲፫ ዓመታት በላይ የተጠቀምኩበት አካውንት ዘጋብኝ


✍ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ

የዓለም ህዝብ ለመሰለልና ለመቆጣጠር የተመሰረተው ፌስቡክ (መጽሐፈ ገጽ) ፣ አዲስ የዓለም ሥርዓት ለመመስረት የሚያግዝ በሰላቢ እጂች (illuminati) የሚተዳደር የሕዋ ሰሌዳ ሥርዓት ነው። ይህንን ትልቅ እውነት በመረዳት ከ፲፫ ዓመታት በላይ ስጠቀምበት ብርሃናዊ ምስሌንና ትክክለኛው ስሜ ባለመጠቀም የሰላቢ እጆችን ሴራ በማጋለጥ ኢትዮጵያውያንን በማንቃት ነበር። 

ፌስቡክ በተደጋጋሚ ሰላቢ እጆችን የሚያጋልጥ በተለይ ስለክትባት ጎጂነት የሚያጋልጥ ልጥፎች ስለጥፍ ያለማስጠንቀቅ በተደጋጋሚ አንስቶብኛል። በተመሳሳይ “በእውነተኛ ስምክ እየተጠቀምክ እንዳልሆነ መረጃ (ሪፖርት) ደርሶኛል ስለዚ በጥቂት ቀናት ውስጥ ወደ እውነተኛ ስምክ ካልቀየርክ አካውንትህ ይዘጋል!” የሚል መልዕክት ቢልክልኝም ባለመቀየሬ አሁን አካውንቴ ሙሉ በሙሉ ዘግቶታል። እዚህ ጋር ልብ ሊባል የሚገባል ለፌስቡክ  ሪፖርት ያደረገው በ አካል ሰው የሚያውቀኝ መሆኑ ነው። ይህ የክፋታችን ደረጃ የሚያሳይ ነው።

በተመሳሳይ የፌስቡክ እህት ድርጅት የሆነው ኢንስታግራም የኢትዮጵያ አውታር የኢንስታግራም ገጽ ሙሉ በሙሉ  ዘግቶታል። ይህ ሁሉ የሚጠቁመን እውነት መግለጥ ለሰላቢ እጆች ትልቅ የህመም ስሜት የሚፈጥርና የአዕምሮ ቁጥጥር የሚቃወም ማነኛዉም አካል  ማፈን ፈጣን መሆናቸው ነው። ቢሆንም በሌሎች አማራጮች እንደምቀጥል አሳውቃአለሁ።

ጥቅምት ፳፫፡ ፳፻፲፫ ዓ/ም


No comments: