❖ በደንብ እናስተውል፤ ለዘመናት፡ በትግራይ የሚገኙት ገዳማትና ዓብያተክርስቲያናት፤ አክሱም ጽዮን፣ ደብረ አባይ፣ ደብረ ዳሞ ወዘተ ሁሉም በጽዮን ማርያም መቀነት አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ቀለማት ያሸበረቁ ገዳማት ናቸው። ታዲያ ይህን መለኮታዊ ፀጋ ከትግራይ ሕዝብ ለመንጠቅና ተዋሕዶ ክርስቲያን ሕዝቤንም ከአምላኩና ከጽዮን እናቱ ጋር ለማጣላት ብሎም ሉሲፈርን ለማንገስ፤'ሰለጠንን' ባዮቹ “ኢ-አማንያኑ” የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ህወሓቶች፣ ሻዕቢያ፣ አሕዛብ የዋቄዮ-አላህ ልጆች፣ ከሃዲ መናፍቃን ሁሉ የዘር ማጥፋት ጦርነቱን በሕብረት ተናብበው በመክፈት እነዚህን አብያተ ክርስቲያናትንና ገዳማትን በተቀናጀ መልክ ነበር ወዲያው ያጠቋቸው። ብዙም ሳይቆዩ የሉሲፈርን ሰንደቅ ሰቀሉ፣ ክቡሩን የጽዮንን/የንጉሠ ነገሥት አፄ ዮሐንስን ሰንደቅ በሉሲፈር ሰንደቅ ተኩት።
ለመሆኑ ጨርቁ የት ነው የሚመረተው? ከየት እያመጡት ነው? ምናለ ለተራበው ወገኔ እንጀራ ቢጋግሩለት?
ከተራበው ሕዝቤ በሰረቁት ስንዴ የፋፉትና ከዓረብ በመጣ ውስኪ በመሳከር ላይ ያሉት ወንጀለኞቹ እነ ጌታቸው ረዳ ከልባቸው ተጸጽተው ለንሰሐ ወደ ገዳም በመግባት ፈንታ በለመዱት ዲያብሎሳዊ መንገድ ሉሲፈርን ለማንገስ ሲሉ “መንበረ ሰላም” የተሰኘውን ቡድን ካባ መልበስ መርጠዋል። ይህ ደግሞ እጅግ በጣም ከባድ ኃጢዓትና ከሁሉም የከፋ ወንጀል ነው።
No comments:
Post a Comment