EAR

አዲስ ነገር

Monday, 28 December 2015

ጨለማና ብርሃን

ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ


የህይወት ጉዞ ውጣ ውረድ የመኖር ጣዕም ነው።ሁሌም በመኖር ደስታና ሃዘን መፈራረቅ የመኖር ትርጉም በሚገባ እንድንረዳና ህይወት በተገቢ መንገድ ለመምራት አስተማሪዎቻችን ናቸው።ጨለማን ሳታውቅ ብርሃንን ማወቅ አይቻልም።ምክንያቱም ሁሉም ነገር ንፅፅር ነውና።የጨለማን ማንነት ካወቅን የጨለማ ተፃራሪ የሆነ ነገር ብርሃን ወሆኑን ማወቅ አያስቸግረንም።በህይወት መንገድም ጨለማንና ብርሃንን ማየት ትክክለኛውን መንገድ ለመምረጥና ለመጓዝ የሚያስችለን የተፈጥሮ ሕግ ነው።ፈጣሪ ሁሉም ነገር የሚሰራው በምክንያት መሆኑን መረዳት ይገባናል።