EAR

አዲስ ነገር

Sunday, 20 December 2015

ፖለቲካ የውሸት ሰበካ።

ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ


የሰው ልጅ ነጻ ፍጡር ነው። በዚህ ምክንያትም ምድራችን ከተፈጠረችበት ጊዜ ጀምሮ ነጻነቱን ለመንጠቅ የተለያዩ ዘዴዎች ተዘይዶበታል።ከዘዴዎቹ መካከልም አንዱ ፖለቲካ ነው።እንድያዉም የምድራችን የመጀመርያ ፖለቲከኛ ዲያብሎስ ይመስለኛል።ዲያብሎስ አዳምንንና ሄዋንን የውሸት ምኞት በመፍጠር ሰመያዊ ክብራቸውን እንዲያጡ ምክንያት ሆኗቸዋል።የዘመኑ ፖለቲኮኞችም እኔ አውቅልሃለው በሚል መንፈስ የሰው ልጅን በማይጨበጥ ተስፋ በመክተት ከመንፈሳዊነት እና አምልኮተ እግዚአብሔር በመለየት ስጋዊውን ፍላጎቱን እንኳን ሳያሟሉለት ተስፋ ቢስ አድርጎውታል።ፖለቲካ ተራ የሞተ ሰውን ንኳ ህያው ብሎ የሚጠራ(ህያው እግዚአብሔር ብቻ ነው) ነው።በጣም የሚገርመኝ የተለያዩ ሰዎች የተለያዩ ፖለቲካዊ ሃሳቦችና አማራጮች ናቸው ብለው በተለያዩ አጋጣሚዎች (በተለይ በዚሁ የማህበረሰብ ትስስር ድረ ገፆች) ያቀርባሉ እነዚህ ሰዎች ፖለቲካ የሰው ልጅ ብቸኛው ችግር ፈቺ የሚመስላቸውና የነሱ ሓሳብ ተግባራዊ ካልሆነ ደግሞ ችግር እንደሚያስከትል ሲገልፁ በጣም ይደንቃል።ሆኖም እነዚህ ተራ ሰዎች ያልገባቸው ነገር ፖለቲካ በሰው ልጅ ታሪክ ላይ ምናባዊ የማይጨበጥ ነገር እንደሆነ ብቻ ነው። ባንፃሩ የፖለቲካ ውጤቶች ጥላቻ፣ዘረኝነትና ጦርነት የመሳሰሉት ናቸው።

ነፃነት ለሰው ልጅ።