EAR

አዲስ ነገር

Monday, 28 December 2015

ኢትዮጵያና ኢሉሚናቲ፡ በኢህአደግ/ህወሓትአርማ ላይ ያለው ችቦ




ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ

ፈጣሪ የስው ልጅን ሲፈጥረው ክብሩ እንዲገልጥበትና ምድርንና መላው ሃብቶችዋን እንዲገዛ ነበር። ሆኖም በሰነ ፍጥረት ታሪክ ውስጥ የብርሃን መልአክ የነበረው ሉሲፈርና (Lucifer) የተፈጠረበት ዋና አላማ እንደሌሎቹ መላእክት ሁሉ እግዚ አብሔርን እንዲያከብር ነበር።ሆኖም በትዕቢት የእግዚአብሔርን ክብርና ስልጣን ለመያዝ ፈለገ።በዚህ ፍላጎቱም የብርሃን መል አክነቱንና ክብሩን በመተው ከሱጋርም መላእክቶችን በማስከተል ከፍተኛ ስልጣናቸውን ትተዋል።ይህ ሉሲፈርም ዋነኛ የሃጥያት ጠንሳሽ ሆነ።በክፉ ሃሳቡም የመጀመርያዎቹ የሰው ፍጡሮቹ አዳምና ሄዋንን በእግዚአብሄር የተከለከለውን ፍሬ እንዲበሉና ከበሉ በሃላም ዓይናቸው እንደሚከፈትና ክፉውም ደጉም መለየት እንደሚችሉ ብርሃኑም እንደሚገለጥላቸው በመስበክና በማታለል የሃጥያት ቀማሾች አደረጋቸው።የሃጥያት መስራቹ ሉሲፈር(ስይጣን) ክብሩን እንጂ ክፉ ስልጣኑን  አልተነጠቀምና የሚስጥር ማህበራት በመጠቀም ደባውን ይፈፅማል።ሉሲፈር የሚለው ቃል ቀጥተኛ ትርጉሙም ብርሃን አመንጪና ሰጪ(Light bearer)ማለት ሲሆን ሆኖም ብርሃኑ የተነጠቀ ሲሆን ሰዎችን በማታለል ግን ጨለማን ያወርሳል።የሰይጣን ጭፍሮች የሚስጥር ማህበራትም የሊሲፈርን ብርሃን(የእግዚአብሔርን መንገድ ማወቅ) ሰጪነት መነጠቁ ስለማይዋጥላቸው ጨለማነቱ ብርሃን ነው ብለው በመስበክ ሰውን ወደ ጨለማ መንገዳቸው ያስገባሉ።የሚስጥር ማህበራት ስይጣናዊ የሆነና የሰው ልጅን በደብሳሳው የሚያታልል ሚስጥራዊ የሆነ አስተምሮና አላማቸውን የሚገልፅ ምልክትም አላቸው።ከነዚህ ውስጥም የችቦ ምልክት ሲሆን ይህም ከላይ እንደተገለፀው የሊሲፈርን ብርሃን ሰጪነትን ለመግለፅ የሚጠቀሙበት ነው።ሊሲፈር የብርሃን መልአክነቱን መነጠቁን አይዋጥላቸውምና።ይህ የችቦ ምስልም ሃገረ አመሪካ የነፃነት ምስል በማለት የምትጠቀምበት ሲሆን።በኢህአደግ/ህወሓት መለያ ኣርማ(logo) ላይም ይገኛል።ኢህአደግስ መጪው ጊዜ ከኢህአደግ ጋር ብሩህ ነው ብሎ መስበኩ ሰውን ፈጣሪውን ከማመን ርቆ ኢህአደግ እንዲያመልክ ነው።ሆኖም መጪው ጊዜ ብሩህ ሊሆን የሚችለው ከእግዚአብሔር  ጋር ብቻ ነው።ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር።