ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
አንድ በአል የሚከበርበትን ምክንያትና አስፈላጊነት ሊኖረው ግድ ነው።ሆኖም የምናከብረውን በአል የምናከብርበትን ምክንያትና አስፈላጊነት ሳናውቅና ዝም ብለን ለደስታና ጭፈራ ማክበር አላዋቂነት ነው።አይሁዳውያን ከ 1933-45
የናዚ ስርዓት
በነገሰበት ወቅት የ አዶልፍ ሂትለር የልደት ቀን April 20 በድግስ፣በመጠጣት፣ስጦታዎችን በመቀያየርና በተለያዩ ባዕድ በሆኑ ድርግቶች በመከወን ያከብሩት ነበር።ሆኖም አይሁዳውያን ለአመታት በዘለቀው
በአዶልፍ ሂትለር መሪነት ብዙ ለአእምሮ የሚከብዱና የሚሰቀጥጡ ግፎችና መከራዎች ይደርስባቸው ነበር።እኛስ የገና በአል እንዴት ነው
የምናከብረው?
በአሁኑ ጊዜም በሉላዊነትና ስልጣኔ በሚሉ ሽፋኖች የገናን በዓል አከባበር በምዕራባውያን ባዕድ አከባበር እየተበረዘ ነው።ለምሳሌ የገና ዛፍና የገና አባት የመሳሰሉ ነገሮች የባዕድ አምልኮ መገለጫ ናቸው።የኢትዮጵያውያን አከባበርም አይደሉም።ስለዚ ባህላችንና አከባበራችን በጦርነት ባርያ ልያረጉን ያልቻሉትን አሁን ግን ጭንቅላታችንን ባርያ እያረጉት ካሉት የምዕራባውያን ባዕድ አስተሳሰቦችና እምነቶች ራሳችንን ነጻ ልናወጣ ይገባል።