EAR

አዲስ ነገር

Wednesday, 27 January 2016

መቋሚያ - ሱስ የምንከላከለውና የሚድን በሽታ ነው።

    ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ

    

የሰው ልጅ በምድር ሲኖር የሚያልፋቸው በጎም መጥፎም  መንገዶች አሉት። እነዚህ መንገዶችም የሂዎቱ አቅጣጫና ማረፍያ የሚወስኑ ናችው። በተለያየ አጋጣሚም የሚያጋጥሙን ነገሮች በጥንቃቄ ካለፋቸው አስተማሪዎችና መንገድን የሚያቀኑ ሊሆኑ ይችላሉ። አንድ ነገር ያለ ምክንያት አይፈጠርም የሚል እምነት አለኝ። በተለያዩ ምክንያቶችና አጋጣሚዎች አንድ ሰው የነገሮች ጥገኛ ወይም ሱሰኛ ሊሆን ይችላል። ለጉዳት የሚዳርጉ ነገሮች ላይ ሱሰኛ ከሆነም ቆይቶም ቢሆን ማንኛዉም በሱስ ላይ ያለ ሰው ከሱስ ለመውጣት እንደሚፈልግ እርግጥ ነው። በዚህ አጋጣሚ የምገልጸው እኔ ራሴ በተለያዩ ሱሶች ውስጥ ስለ አለፍኩኝ የሱሰኛ ጭንቀቱ ምን እንደሆነ ይገባኛል። አብዛኛው ሰዉም ሱሰኛው ከሱሱ እንዲላቀቅ እንጂ እንዴት መላቀቅ እንዳለበት አይነግረዉም ወይም አይጠቁመዉም። በኔው እምነት ሳይነሳዊ የሆኑ መንገዶች ከሱስ ለመውጣት አማራጭ ቢሆንም አምልኮተ ፈጣሪ ግን አስተማማኝ ከሱስ ማምለጫ መንገድ ነው።

በአሁኑ ጊዜ በሀገራችን እየታየ ያለው የማሪዋናና የሌሎች ሱሶች ተጠቃሚ ወጣት ቁጥር ከፍተኛ ነው። ለዚህ ምክንያት ከሚሆኑት መካከልም ሉላዊነት ያመጣው የመገናኛ ብዙሃንና ታዋቂ ሰዎች የሚባሉ ባህሪ ባለመምረጥ ሙሉ በሙሉ ማለትም ጎጂውንና ጠቃሚውን ባለመለየት መኮረጅ ነው።

ከአንድ ወር በፊት ከብዙ ጊዜ በሃላ አንድ የቀድሞ ጓደኛየ መንገድ ላይ አገኝሁት። ልጁ በጣም ተቀየረብኝ ምክንያቱም ከዚህ በፊት ሳውቀው ቀጫጫና ሱሰኛ ነበር። አሁን ግን ሰውነቱ ሞላ ፡ ፊቱም ቀላ ብሏል። እሱም የኔ ለውጥ ገርሞታል አፍጥጦ ያየኛል። “ካልቸኮልክ ሻይ እየጠጣን እንውራ!” አለኝ። እኔም ፍቃደኝነቴን በመግለጽ አንድ ቦታ ላይ ተቀመጥን። ወሬ ተጀመረ “በጣም ተቀይረሃል ምንድነው ሚስጥሩ በማለት ጠየቀኝ”። እኔም አዎ የነበሩኝን ሱሶች ተውካቸው በማለት መለስኩለት። በተራየም እኔ ተመሳሳይ ጥያቄ ጠየኩት። እየሳቀ ሁለት ወር ሙሉ ሱስ ለመተው ማገገምያ ውስጥ እንደቆየና አሁን ከማገገምያ ከወጣ ስድስት ወር እንደሞላው አጫወተኝ። ጥያቄየ በመቀጠል የት ነው ማገገምያው? አልኩት። መቐለ ዩኒቨርሲቲ በመሰረተው “መቋሚያ” የሚባል ድርጅት እንደሆነ ነገረኝ። ሲቀጥልም ድርጅቱ ሁለት ወር በማገገምያ ውስጥ በማስቆየት የተለያዩ ከሱስ ሊያርቁ የሚችሉ ትምህርቶችና ድጋፎች በማድረግ ያስወጣቸዋል። በመቀጠልም በድርጅቱ ያገገሙ ልጆች በመሰባሰብ በተመላላሽነት የተለያዩ ትምሕርቶች በማስተማር እርስ በርስ እንዲወያዩ በማድረግ (ቋሚ የሆነ መርሐ ግብር አላቸው) የበለጠ ለውጥ ለማምጣት ይሰራሉ። ልጆቹ በመርሐ ግብርም ወደ ተለያዩ ትምሕርት ቤቶች በመሄድ ስለ ሱሰኝነት ግንዛቤና ትምህርት ለወጣት ተማሪዎች ይሰጣሉ። ‹‹ሱስ በሽታ ነው።›› መሪ ቃላቸው ነው። ይህ ሁሉ ሲነግረኝ በጣም ደስ አለኝ ፡ በልጁ ያየሁት አካላዊና አእምራዊ ለውጥም አስደነቀኝ። ከርሱ ጋርም ወደ መሰብሰብያ ቦታቸው እንድሄድ ጋበዘኝ። ግብዣው ተቀብያ አብረን ሄድን።መሰብሰብያ ቦታው ላይ ስደርስ አብዛኞቹ ልጆች የማውቃቸው ነበሩ። ሰላምታ ከሰጠህዋቸው በኃላም ለውይይት ተቀመጥን። የውይይቱ መሪና አስተማሪም ተዋወቀኝ። እኔም ከዚህ በፊት ሱሰኛ እንደነበኩኝ አሁን ግን ከሱ ነጻ እንደሆንኩኝ ስገልጽለት ደስ በሚል ፈገግታ ታጅቦ “ዎው በጣም ጥሩ!” አለ። አስራ ሥስት ዓመት ሙሉ ሱስ ውስጥ እንደነበረም ነገረኝ። ውይይቱ በጣም ደስ በሚል መንፈስ ተጠናቀቀ። የልጆቹ ራሳቸው ተለውጠው ሌላው ሰው ለመቀየር ያላቸው መንፈስም አስደነቀኝ። እኔም የመቋምያ ድርጅትን እውነትም መቋምያ አልኩኝ።መቋምያ በጸሎት ሰነ ስርዓት ምእመናን በመቆም ብዛት እንዳይደክማቸው ለድጋፍ የሚጠቀሙባት በትር ነች።

ታድያ ውይይቱ በሚደረግበት ወቅት ግን ብዙ ነገርች ትኩረቴን ስቦታል። አወያዩ ፍጹም ጭዋና ሰነ ስርዓተኛ ነበር። መንፈሳዊ የሆኑ ትምህርቶች ሲሰጥም ፕሮቴስታንታዊ ይዘት ያላቸው ነበሩ። ይህ ሁኔታ ነበር ትኩረቴን የሳበው ታድያ አስተማሪው ከሱስ የተላቀቁት ጓደኞቼን በሃይማኖት ረገድ ተጽዕኖ ሊያደርግባቸው ይችላል። በተጨማሪም አብዛኛዎቹ ልጆች በሱስ ዓለም የነበሩ በመሆናቸው ስለ ሃይማኖት ብዙ ዕውቀትም ያላቸው አይመስለኝም። በዚም ምክንያትም ተጽዕኖ መፍጠሩ አይቀርም ብየ አስባለው። ከውይይቱ በሃላ ስለ አስተማሪው መረጃ ለማግኝት በመሞከሬ እውነትም እንደጠረጠርኩት ፕሮቴስታንት መሆኑ አረጋገጥኩኝ። ውስጤም የመቋሚያ ወጣቶችን ከሱስ የማላቀቅ በጎ አላማ በአወንታዊ መልኩ ብመለከተዉም ከጀርባ ግን ሃይማኖታዊ አላማ እንዳይኖርው እሰጋለው።

ሰላም
18/05/2008