ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
ከቅርብ ጊዚያት ጀምሮ በቤተ ክህነት ዙርያ የሚታዩ ነገሮች የምዕመንን መንፈሳዊ ሃይልን የሚያደክሙና እርሰ በርስ በጠላትነት እንዲተያይ የሚያደርጙ ነገሮች እያየን እየሰማን ነው።የኔ ዋነኛው ትኩረት ግን የ አጥማቂው መምህር ግርማ ወንድሙ ጉዳይን ይመለከታል።
የሰው ልጅ ወይም ምእመን የመንፈስ አሰራርን ባለማወቁና ስጋዊ በሆነ መንገድ ኑሮው በመግፋቱ ለተለያዩ ችግሮች በመጋለጥ አስከፊ ሕይወት መኖር ተለማምዶታል።ለዚህ ምክንያቱም የተለያዩ ጠንቋዮችና ደብተራዎች በቤተ ክርስትያንና በተለያዩ ቦታዎች መሽገውየክፉ መንፈስ ህልውናና ጥቃት ለማያውቀው አብዛኛው ሰው የመኖር ፈተናና ጠላት ሆነው ሕይወቱ ሲያመሳቁሉት ኖሮዋል።
ይህ እንዳይሆንም የሃይማኖት መምህራንና አስተዳዳሪዎች የቤተ ክርስትያን በጎችን መጠበቅ ይገባቸው ነበር።ሆኖም ይህንን ማድረግ ባይችሉም ይህንን ማድረግ የሚችሉትን እንደነ መምህር ግርማ ወንድሙ አይነት ጸጋው የበዛላቸው አባቶችን መደገፍ ሲገባ በተቃራኒው ራስዋ ቤተ ክርስትያን በሚገርም መልኩ ከ አህዛብ ባልተለየ እንድያዉም በበለጠ የተለያዩ ሰንካላ ምክንያቶች በመፍጠር የመምህርግርማ ወንድሙ ሰውን የማዳንና አምልኮተ እግዚአብሔርን በመፈጸም በጎውን መንገድ እንድንከተል የሚያደርገው ድንቅ ትምህርታቸው እንዳይፈጽሙ ምዕመን የእርኩሳን መናፍስት መጫወቻ እንዲሆን ሰይጣን በዘየደው ዘዴና ሓሰተኛ ውንጀላ ለወራት እስር ቤት እንዲወረወሩ ቢደረግም የእግዚአብሔር የሥራው መንገድ ብዙ ነውና እስር ቤትም ውስጥ ሆነው ብዙ የበረከት ሥራዎች እንደሰሩ ራሳቸው ከእስር ከወጡ በሃላ በራድዮ አቢሲንያ በሰጡት ትምህርት አድምጠናል።

መምህር ግርማ ወንድሙ ውስብስብና በፍልስፍናና ሳይነስ ልንደርስበት የማንችለውን የመናፍስት ውግያ ምንም ሳይሰስቱ በማስተማርና በመፈወስ የብዙ ኦርቶዶክሳዊና የሌላ ሃይማኖት ተከታይ ሰው ሂወት እንዲቃናና የእግዚአብሔርን መንገድ የተከተለ እንዲሆን ያደረጉ ናቸው።ለዚህም እኔ ራሴ ቀንደኛ ምስክር ነኝ።በዚህም ምክንያትም ሰይጣን የሰውን ልጅ መዳንና የእግዚአብሔርን መንገድ እንዲከተል አይፈልግምና ይህንን የመምህር ግርማን የማዳን ሥራን ለማቆው በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ መንገዶችና ምክንያቶች በመፍጠር ይቃወማል።መምህር ግርማ ከእስር ከተለቀቁ በሃላም ቢሆን ፍቃድ ተሰጥቷችው የማዳን ሥራቸው ቢጀምሩም አሁን ደግሞ ከፓትርያርክ አቡነ ማትያስ በተጻፈ ደብዳቤ ሥራቸው እንዲያቆሙ መደረጉ ሰምቻለው።
ይህ ዜና የሰማሁት በየሳምንቱ ቅዳሜ በራድዮ አቢሲንያ የሚተውላለፈውንና የብዙ ሰዎች ሕይወት በቀየረው የመምህር ግርማ ወንድሙ ክፍል 116A ትምህርት ለማድመጥ ዛሬበዩቱብ መካነ ድር ለማድመጥ ሲከፍት የመርሃ ግብሩ አዘጋጅ አያልቅበት ተሾመ በሚያሳዝን መልኩ ሲገልጸው ነው።መምህር ግርማ ወንድሙ ከአሁን በሃላ በማንኛውም የሃገር ውስጣና የውጭ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ስም ምንም ቃል ትንፍሽ ማለት እንደማይችሉና ደብዳቤው የስም ማጥፋት ጽሑፎች የበዙበት እንደሆነና ራድየው ላይ ለማንበብም እንደሚከብድ ገልፆል።
ቅድስት ሃገራችን ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘመናት ኦርቶዶክሳዊ ተዋህዶ ሃይማኖትን ጠብቀው ያቆዩላት ብዙ አባቶች አልፈዋል አሁንም አሉ።በቀዳማዊ ንጉሥ ሃይለስላሴ ዘመንም ከግብፅ ሲሾምላት የነበረው ፓትሪያርክ ቀርቶ ራስዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ራስዋና የራስዋ ሰው (ፓትሪያርክ) መሾም ከጀመረች ጊዜ ጀምሮ የ አሁኑ ፓትሪያርክ ስድስተኛው ናቸው።አቡነ ማትያስ የፕትርክና ስልጣንን ከያዙ ሦስተኛ አመታቸው ላይ ይገኛሉ።
እኚህ አባት በእውነት ኦርቶዶክሳዊና የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ጠባቂ መሆናቸው እጠራጠራለው።አካሄዳቸዉም ፖለቲካዊ መንገድ ይመስላል።የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያንን መናፍቃን (ተሃድሶዎች ነን የሚሉ) ለመውረርና ለመቆጣጠር በሚንደረደሩበት ወቅትማህበረ ቅዱሳንን ለመቃወም ተንደረደሩ።ባለፈው የካቲት ወር ላይ በካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ባደረጉት ጉብኝትም ለፖፕ ፍራንሲስ(ኢሊሙናቲ) ከካቶሊክ ጋር ያለን ልዩነት ጠባብ ነው በማለት ተናግረዋል።ሆኖም ካቶሊክና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን በምንም መንገድ የማይገናኙ ሁለት የተለያዩ መንገዶች ናቸው።የቀድመው የካቶሊክ ፖፕ ፒዮስ ባርከው በላኩት የጦር መሳርያ ብዙ የኢትዮጵያ ልጆች በ አገራቸው በፋሺስት ጣልያን መገደላቸው እንዴት ይዘነጋል ?
የሁሉም ነገር መልስ ባለቤት እግዚአብሔር ነውና ለሁላችን በጎ ሕሊና ለመሪዎቻችን መንጋውን ከመበታተን የሚያድን መንፈስ ይላክልን።