ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
የሰው ልጅ ከጥንት ጀምሮ የተለያዩ የመገናኛ መንገዶች እየተጠቀመ አሁን የምንጠቀምባቸው የተለያዩ የመገናኛ መንገዶች ላይ ደርሷል።ከነዚህ መካከልም ቴሌቪዥን አንዱ ነው።በሃገራችን ኢትዮጵያም ከቅርብ ጊዜያት ጀምሮ የተለያዩ የግልና የመንግስት ጣብያዎች እየተበራከቱ መጥተዋል።ቴሌቪዥን ሁሉንም የመረጃ ማስተላለፍያ መንገዶች ማለትም ምስል፣ድምጽና እንቅስቃሴ የሚጠቀም በመሆኑ በሰዎች ጭንቅላት ላይ ተጽዕኖ ለመፍጠር አቅም ይሰጠዋል።ትምህርት ማህበረሰብን በመቅረፅ ደረጃ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ይታወቃል።መገናኛ ብዙሃንም ሃይለኛና ያብዛኛው
ህዝብ የትምህርት መሳርያ ናቸው።ሰላቢ እጆችም (ኢሊሙናቲ) ይህንን ተጽዕኖ የመፍጠር አቅም በመጠቀም የ አለም ህዝብን ጭንቅላት
ለመቆጣጠር ይጠቀሙበታል።ማለትም ድብቅ አጀንዳቸውን ያዘሉ መልዕክቶች በመመሳሰልና በመሸፋፈን በሚያሰራጭዋቸው መርሃ ግብሮች እንዲያስተላልፉ
ይረዳቸዋል።የሳተላይት ቴክኖሎጂ ከመስፋፋቱም ተጨምሮ ትውልዱ በተለይ ህጻናት የምዕራባውያን ባህልና አስተሳሰብ ተገዢ እያደረገ ነው።ይህም ትክክለኛው ኢትዮጵያዊ ማንነት የሚያጠፋና የውጭ ሓይሎች ባርያ የሚያደርግ ይሆናል።
የቃና ቴሌቪዥን መሪ ቃል ‹‹ውስጤ ነው›› የሚል ቃል ነው።ይህ ቃል በጥልቀት ሲመረመር ባዕዳዊ የሆነ ምልከታ የያዘ ነው።ውስጤ ነው ለሚለው ቃል ማን ነው? ወይም
ምንድነው? የሚል ጥያቄ መጠየቅ ተገቢ ይሆናል።