ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
የፌስቡክ መካነ ድር በቅርቡ አንድ ሰው በለጠፈው ነገር ጓደኞቹ የሚሰጡት ምላሽ ለማወቅ የሚያግዙ የስሜት መግለጫ ቁልፎች በ ላይክ (like) ቁልፍ ላይ መጨመሩ ይታወቃል።እነዚህ ቁልፎች መገረም፣ማፍቀር፣መሳቅ፣ ማዘን የሚገልጹ ናቸው።እውነት ፌስቡክ ይህን ሁሉ ለመጨመር የፈለገው ለተጠቃሚው በማሰብ ይሆን፧
አለማችንን እኛ ባልተገነዘብናቸውና ባላወቅናቸው አካላት ትመራለች።የነዚህ አካላት (ሰላቢ እጆች) ዋነኛ አላማም የአለም ህዝብን አንድ ላይ በማስተሳሰር መግዛትና የነሱ ሰይጣናዊ አንድ የአለም መንግስት አገልጋይና ባርያ ማድረግ ነው።ይህንን ሰይጣናዊ ዕቅድ ለመፈጸም ከሚጠቀሙበት መንገድም ቴክኖሎጂ አንዱ መንገድ ነው።አንድ የአለም መንግስት ለመመስረት የሚረዳቸው ይህ ቴክኖሎጂ ሰዎችን በዘመናዊነትና አዋቂነት በሚል ሰንካላ ሽፋን በማስተሳሰር የሰውን ነጻነትና ስሜት በማጥናት የሚበጃቸው መንገድ እንዲቀይሱ ይረዳቸዋል።የኮምፒተር ቴክኖሎጂም ዋነኛው መሳርያቸው ነው።
የአለም አቀፍ ግንኝነት መረብ (internet) በጥቂት የአለማችን ቁንጮ (ሰላቢ እጆች) ሰዎች ቁጥጥር ስር መሆኑ አንባቢው ማወቅ ይገባዋል።ይህ ማለትም ማነኛውም የኮምፒተር ትስስር ባለበት የሚደረግ ነገር ምስጥሩ ያልተጠበቀና በጥቂቶች ቁጥጥር ስር መሆኑ ግልጽ ይሆናል።አሜሪካዊው ኢድዋርድ ስኖውደን ከቅርብ አመታት በፊት በተለያዩ ጊዚያት እያወጣቸው ያሉት መረጃዎች እንኳን በቂ ማሳመኛ ይሆናሉ።
ወደ ፌስቡክ ስንመለስ አሁን የጨመራቸው ቁልፎች በቀላሉ ፌስቡክ የሚያስደስቱንና የሚሳዝኑን በጠቅላላ የኛ አጠቃላይ ሰነ ፡ልቦናዊ ፍላጎት ለማጥናትና መረጃዎችን በመሰለል ለነዚህ ጥቂት ግን አለም አቀፍዊና ውስብስብ ዕቅድ ላላቸው ቁንጮዎች አሳልፎ ለመስጠት አላማ ያደረገ ማሻሻያ ነው።ሰብዓዊና ተፈጥራዊ የሆነው የሰዎች ግንኝነት ወደ ሰው ሰራሽ (arteficial)ና
ማሽናዊ መቀየር ድብቁ ፍላጎታቸው ነው።ይህም የሰው ልጅ ከሰውነት
በመውጣት ባርያ በማድረግ መግዛት ስለሚፈልጉ ነው።
የፌስቡክ መስራች ማርክ ዙከምበርግ ከወራት በፊት ከቻይናዊትዋ ሚስቱ ለወለዳት ልጁ በጻፈላት ደብዳቤ በግልጽ ለሚቀጥለው ትውልድ በቴክኖሎጂው መንገድ አንድ የአለም ስርዓት (New World Order) መመሥረት እንደሚመኝላት ገልጿል።
