EAR

አዲስ ነገር

Thursday, 15 September 2016

እውነተኛ ኢትዮጵያዊ ፊልሞች


ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ

ዘመኑ የፊልም ኢንዲስትሪ ከፍተኛ ደረጃ የደረሰበት ጊዜ ነው።ፊልም አንድን ማህበረሰብ በመቅረጽ ረገድ የራሱ የሆነ አስተዋጽኦ  አለው።የ አሜሪካ የፊልም መንደር ሆሊውድ አለም አቀፍ የሆነ የፊልም ተጽዕኖ የፈጠረ ነው።አገራችም ውስጥም የዚህ መንደር የፊልም ምርቶች ትውልዱን ኢትዮጵያዊው የሆነውን በመጣል የምዕራባውያን አጠቃላይ የሆነ ተጽዕኖ እንዲያድርበት እያደረገው ነው።የ አገራችን የፊልም ኢንዲስትሪም እድገት ላይ ያለ በመሆኑ ይህንን ተጽዕኖ በመመከት ኢትዮጵያዊ የሆኑ ፊልሞች ለማቅረብና የምዕራባውያን ፊልሞች ተጽዕኖ ማስቀረት አልቻለም።የፊልሞቹ ርዕሰ አሳብ እንዲያዉም ከሴትና ወንድ የፍቅር ግንኝነት ዘለው ማለፍ አልቻሉም።በተደጋጋሚ  እንደሚገለጸው ኢትዮጵያ ብዙ ለፊልም የሚሆኑ አስደናቂ ታሪኮች ያላት ሃገር ነች።ሆኖም ይህ ወደ ተግባር ሲቀየር ብዙ አይታይም።በዚ ጽሑፍ የምናየው ትንሽ ቁጥር ቢኖራቸዉም እውነተኛ የሆነ ኢትዮጵያዊ የሚሰብኩ ፊልሞች ለማየት በመቻሌ አድናቆቴንና በፊልሞቹ የተነሱት ጉዳዮች ለመግለጽ ነው።

.ዩቶጵያ - ይህ ፊልም ከተሰጠው አርዕስት ጀምሮ ትኩረቴን የሳበው ነበር።ፊልሙ ለመመልከት ፍላጎት ያደረብኝም አርዕስቱም በማንበብ ብቻ ነበር።ምክንያቱም ዩቶጵያ የሚለው ቃል ፍጹም የሆነ የደስታ ኑሮ የሚገኝበት ምናባዊ ቦታ መሆኑ ነበር።ይህም ምድራዊ ገነት የሆነችውን ኢትዮጵያ የሚወክል ቃል ነው።ግሪካዊው ባለ ቅኔ ማየት የተሳነው ሆሜር ኢትዮጵያውያንን ዩቶጵያ በሚለው ድርሰቱ እንዲህ ይገልጻቸዋል።
‹‹ ሰዎች ከመላእክት ጋር ይኖሩ ነበር ነገር ግን ሰዎች ሲከፉና ሲረክስ መላእክት ከሰው ጋር መህን አቆሙ …… አሁንም ግን ከመላእክት ጋር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አሉ። ››
ይህ ነበር ኢትዮጵያዊነት ዩቶጵያ ማለት አማልክት ጋር መኖር ሃሳብ ጭንቅ የሌለበት ኑሮ።አምላክን እያመሰገኑ እያገለገሉ መኖር።ይህንን ኑሮ በማጣታችን ነው ኑራችን ክፋት፣ ተንኮል፣ ጭንቅ የሚገለጥበት የሆነው።አባቶቻችን ግን ይህ ኑሮ ህይወታቸው ነበር።ስልጣንያቸው አማልክት ጋር መኖር እግዚአብሔርን ማስደሰት ነበር።

ይህንን እውነታ ለዚህ ትውልድ መንገር ግን እንደ ዕብድ ሊያስቆጥር ይችላል።ምክንያቱም ማንነቱ አባቶቻቹ ክብር ተመልሶ እንዳያይና እንዳይኖርበት ብዙ ሴራዎች ተፈጽሞውበታል አሁንም በተጠናከረ መንገድ እየተሴረበት ነው።ይህንን ሴራ ለማሸነፍ ግን የአባቶቹ መንገድ ማጥናትና መኖር መጀመር አለበት።ጊዜዉም ይህንን እንዲያደርግ ያስገድደዋል።ምክንያቱም ያንን መንገድ ትቶ ሌላ መንገድ በማበጀቱ እየኖረው ያለ ኑሮ መልስ ይሰጠዋል።


የዩቶጵያ ፊልም ደራሲም ይህንን በሚገባ የተገነዘበ መሆኑ ምንም ጥርጥር የለዉም።የፊልም ጥበብን በመጠቀም ይህንን እይታ በትንሽ ጭላንጭልም ቢሆን ሊያሳየን ሞክሯል።ለዚህም ትልቅ ምስጋና አለኝ።በተጨማሪም ፊልም በሚገባ ታስቦበት እንደተሰራ የሚያመለክት ነገር አግኝቻለው።የፊልሙ ፖስተር ላይ ዩቶጵያ የሚለው የፊልሙ አርዕስት ሲጻፍ "" ፊደልን ከሌሎች ፊደላት ተላቅ ብላ ተጽፋ ትታያለች።ደራሲው በእውነት ይህንን ያደረገበት ምክንያት በግልጽ ባይታወቅም ግን ከፊልሙ ይዘትና አርዕስት በመነሳት ግን የታሰበበት ይመስለኛል። ""  ፊደል ከኢትዮጵያውያን ጋር የተቆራኝ ነው።ቶ ከየ ፊደላት የመጨረሻዋ ማለትም ሳብዕ ነች።ይህም በሰው አምሳል የተቀረጸችና ሰብ ማለትም ሙሉ ፍጡር የሚል ትርጉም ያላት ነች።ይቺ ፊደል ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን ከዘመነ ብሉይ ጀምሮ ሲጠቀሙበት የነበረ ፊደል ነው።በዘመነ አዲስ ፈጣሪ ሰው ሆኖ ""  ወደ ምድር እንደሚመጣ የሚተነበየ ነበር።

በአጣቃላይ ዩቶጵያዊ ፊልም ፍጹም ኢትዮጵያዊ የሆነና ይህንን የውሸት አለም ግልጥ አድርጎ በማሳየት ውሸቱን እንድንፋለም የሚጋብዝ ነው።በተለው ማንነቱ ጠፍቶት በምዕራባውያን አምልኮ ለሚሰቃየው ትውልድ እውነታው የሚያሳይ ነው።ይህንን ፊል መመልከት ትርፍ እንጂ ኪሳራ የለዉም።


፪.ረቡኒ - በፊልሙ ካሉት ገጸ ባህርያት አንዱ ጥንታዊው የአስተዳደር  ስርዓት ጀማሪ የሆነው ኢትዮጵያዊው ካህን ዩቶር ነው።
ዩቶር ወይም ራጉኤል ማነው?


፫.ሃገርሽ ሃገሬ -