ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
ይህንን ስጽፍ : ፖለቲከኛ ለመሆን በመፈለግ አይደለም። የሀገራችን ኢትዮጵያ ችግር የታየኝና የመስለኝ መነሻ ወይም ምክንያት ነው ያልኩት ለመግለጽ እንጂ። ፖለቲካ : እውነት አይታየዉም፣ ስለ ቀጣዩ ትውልድ አያስብም። አሳቢ ለመምሰል ግን ይሞክራል : በጠቅላላ እውነት ናት ብሎ ያሰባትን ሌላ ሰው ወይም ህዝብ ላይ በማስረጽ እንዲቀበለው ይጥራል። የሱ ተቃራኒ የሆነ ሓሳብ ያላቸው ስዎች በጠላትነት ይፈርጃል። ተቃራኒ ሓሳቡ ተጽዕኖው ከፍተኛ ሆኖ ከታየዉም የሓሳቡ አመንጪ ሰውን ለማጥፋት እስከሚችለው ድረስ ይደፍራል።ይህ የፖለቲካ የተለመደ አካሄድ ነው። መጨረሻዉም መጠፋፋት ነው።
የትውልድ ታሪክን በማጣመም ለፖለቲካ ለፍጆታ መጠቀምም የተለመደ አካሄድ ሆኗል።በእርግጥ አንድ ማህበረሰብ በሚያካሂደው ማህበራዊ እንቅስቃሴ የሰው ስብስብ እስከ ሆነ ድረስ በጎም መጥፎም ሁኔታዎች አከናውኖ ማለፉ እርግጥ ነው። ታድያ ፖለቲካ ለያዘው ዓለማ ማስፈጸምያ መጥፎ ድርጊቶችን ካለፈው የታሪክ ዶሴ በመጥቀስ ለፖለቲካዊ ዓላማው ማዋል ከጀመረ ነገሮች መጨረሻ ወደሌላቸው ንትርክና የትውልድ የጽልመት ኑሮ መዳረጉ የምናየው እውነታ ነው።
ሀገራችን ኢትዮጵያ ከ42 ዓመታት በፊት ጀምሮ መፍትሔ ወደጠፋበት የታሪክ ውጥንቅጥ የገባች እንደሆነች አምናለው። በዚህ ወቅት የተመሰረተው ገንጣይ የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ድርጅት (ት.ህ.ነ.አ.ድ) የዚህ በሽታ መነሻ ነበር። ድርጅቱ ከተመሰረተ
ከአንድ ዓመት በኋላ ባዘጋጀው የድርጅት ዓላማ የሚገልጽ ጽሑፍም (Manifiesto) የዐምሓራ ብሔር ገዢ መደብ ከገዢነት ማስወገድ
እንደሆነ ይገልጻል። ዐምሓራ የሚባል ብሔር ባይኖርም። ይህ ነበር በዚህ ወቅት ለሚታየው የኢትዮጵያ የዘረኝነት ድባብ መሰረቱ።
የድርጅት አላማ የሚገልጽ ጽሑፍም (Manifiesto) - ሽፋን
በአሁኑ ዘመን ይህንን የዘረኝነት በሽታ በትግራይ ክፍለ ሀገር ወጣት ላይ የዘሩትም የታሪክ ጸሓፊ ነኝ በሚሉት በዘረኝነት የተለከፉት የአንድ የፖለቲካ
ድርጅት አስፈጻሚ የሆኑ መምህር ገብረኪዳን ደስታ ናቸው። መምህር ገብረኪዳን የማውቃቸው የአንደኛ ደረጃ ተማሪ በነበርኩበት ወቅት
"ፅዉፅዋይ" በሚለው የትግርኛ ቋንቋ
የተረት መጽሓፍ ነበር። ከጊዜያት በኋላ ግን አነጋጋሪ በሆኑ የሽዋ ሰዎችን የጥቃት ዓላማ ባደረጉ በዘረኝነት የታጨቁ መጽሕፍቶቻቸው
ይበልጥ እያወቅኳቸው መጣው።
ከድርጅቱ አላማ የሚገልጽ ጽሑፍ አማራ ብሔር በጠላትነት የሚገልጽበት ጽሑፍ
ባሁኑ ወቅት ለሚታየው የወጣቶች ታሪክ አውቀናል የማለት ትዕቢት መነሻው የሆነ ዘረኝነት ህወሓት
ዓላማ ያነገቡ ሽዋን ትኩረታቸው ያደረጉ ዘረኛ የሆኑ የመምህር ገብረኪዳን ደስታ መጻሕፍቶች ናቸው። ታድያ የትግራይ ክፍለ ሀገር
ወጣት ይህንን የዘረኝነት እሽግ ምግብ ከምን እንደተሰራ ለምን እንደተሰራ ሳያጣራ ውሃን በመጨመር ወደ ሆዱ በማግባቱ ምግቡ ተመልሶ
ተውሳክ እየሆነበት ተቸጉሯል። “እምቢታ አንፃር ወረርቲ” የሃጸይ ዩሃንስ ታሪክ ከፍ አድርገው ፤ የሃጸይ ምኒሊክ ታሪክን በሚያንኳስስ
መልኩ በማቅረብ። ሽዋና ትግራይ የሚሉ ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት ያቀዱ የህወሓት ፖለቲካ ለማስቀጠል የሚያስችሉ ጥላቻ ላይ የተመሰረት
የውሸት ታሪክ መጻፍና መናገር መለያቸው ነው።
መምህር ገበረኪዳን ከየሩቅ መስኮተ ትዕይንት(Television) ውጪ በአካል ያየሁዋቸው ባለፈው
ዓመት በመቐለ ከተማ በሚገኝው ራሔል ቤተ ጥበብ በተደረገው ሳምንታዊ የጥበብ ዝግጅት የክብር እንግዳ ሆነው በመጡበት ወቅት ነበር።
በዚህ ወቅት መምህር የሚያደርጉት ንግግር በጉጉት ስጠብቀው ነበር። ጊዚያቸው ደርሶ በጋዜጠኛ ነጋ ዘርኡ ግብዣነት ወደ መድረኩ ወጥተው
የቀረበላቸው ጥያቄዎች መመለስ ሲጀምሩ ከዚህ በፊት በዘረኛው ስብከታቸው የተጠመቁ ወጣቶችና ጋዜጠኞች በደማቅ ጭብጨባ ተቀበልዋቸው።
በዚህ ወቅት አንድ ነገር ገባኝ ለሰው ልጅ እሱ ከማንም በላይ እንደሆነ ከነገርከው አንተ ንጉሥ ለመሆን እንደማይቸግርህ ነበር።
እነዚህ ሰዎች በመጽሓፈ ገጽ መድረክ የሃጸይ ዩሐንስ ኢትዮጵያዊነት
በመርሳት ትግራዋይ መሆናቸው ዘረኛ አስተሳሳባቸው በመርጨት ያልገባው ወጣት ወደ ፈለጉበት አቅጣጫ የሚመሩት ናቸው። በንግግራቸዉም
ሃጸይ ዩሃንስ ብቸኛው ኢትዩጵያዊ ንጉሰ ነገስት እንደሆኑ የተለመደቺው የጅል ስብከታቸው በመስበክ ተሰናበተው ሄዱ። መምህር ገብረኪዳን
ሃጸይ ዩሐንስ ከሞት ቢነሱ አንት “ውሸታም እኔ ሰበብ በማድረግ የሞትኩላትን ኢትዮጵያ ትግራዋይ ነው በማለት አታስቀይምብኝ!” የሚልዋቸው
ይመስለኛል።
በዛው ዓመት (2008) ነሓሴ ወር በድምጺ ወያነ ትግራይ በተዘጋጀው የተማሪዎች ምረቃ ዝግጀት
በተመራቂ ተማሪ ጋባዥነት በተገኝሁበት ወቅት መምህር ገብረኪዳን የክብር እንግዳ ነበሩ። በተለያዩ ዝግጅቶች መምህር የክብር እንግዳ
ሆነው መቅረብ የተለመደ ነው። ይህ የሆነበት ምክንያትም ግልጽ ነው። የመድረኩ መሪ መምህሩን ካደነቀ በኋላ እንዲናገሩ እድል ሰጣቸው።
ንግግራቸው ሸዋን መዝለፍ እንደሚሆን አልተጠራጠርኩም። ታድያ መምህር በንግግራቸው ትግራዎትና ትግራይ ውስጥ የሚገኙ የኦርቶዶክስ
ተዋሕዶ ለምን በአማርኛ ያስቀድሳሉ በማለት ፈጣሪም ትግራዋይ ለማድረግ በሚመስል መልኩ ክሳቸው ትግራዋይን ትተው ሽዋን ደረሰ። መምህር
ገበረኪዳን በንግግራቸው በቤታችን ምግብ ለመመገብ ጸሎት የምናደርገው እንኳን የሸዋ ሰዎች በፈጠሩብን ተጽዕኖ በአማርኛ ቋንቋ ነው
ይላሉ። ተገደን ነው አለማለታቸው ግን ያስመሰግናቸዋል። መምህር ገብረኪዳን ያደረጉት ንግግር በተንቀሳቃሽ ስልኬ የተንቀሳቃሽ ምስል
ወድምጽ መቅረጫ አስቀርቸዋለው። ከታች መመልከት ይቻላል።
በተመሳሳይ ዓመት ማለትም ባለፈው ሳምንት ለመጀመርያ ጊዜ በትግርኛ ቋንቋ የተዘመረ ነው የተባለለት
የኦርቶዶክስ መዝሙር (የኤርትራ የትግርኛ መዝሙር ግን አዳምጣለው) በደብረ ሰላም ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስትያን በየሰራተኞች ጉባኤ
መርሐ-ግብር ላይ ሲመረቅ መምህር ገበረኪዳንና የፖለቲካ መምህር መሓሪ ዩሃንስ የክብር እንግዶች ነበሩ። በዚህ አጋጣሚምም ቤተ ክርስትያን
ከፖለቲከኞች የዘረኝነት ሓሳብ እስረኛ መሆንዋ ታየኝ።በእርግጥ በእግዚአብሔር ቤት ማነኛዉም ሰው መግባትም ሆነ መገልገል የእግዚአብሔር ፍቃድ ነው። ሆኖም ፖለቲካዊ ዓላም
ያላቸው ሰው እንግዳ አድርጎ ማቅረብ ግን ምዕመን ከመንፈሳዊነት ማራቅ ነው የሚሆነው። በትግርኛ ቋንቋ ማስቀደስ ሆነ መዘመር ሽዋዎች
የምትልዋቸው እንዳልከለከልዋቹ እናውቃለን።
ዘረኝነት ይውደም
ኢትዮጵያዊነት ይለምልም።
ሰላም
ጥር 24, 2009 ዓመተ ምሕረት