EAR

አዲስ ነገር

Monday, 9 October 2017

ግዕዝና ምዕራባውያን


ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ

"Then Melchizedek king of Salem brought out bread and wine; he was the priest of God Most High. And he blessed him and said: 'Blessed be Abram of God Most High, possessor of heaven and earth; And blessed be God Most High, who has delivered your enemies into your hand'" (Genesis 14:14, 16 - 18)

አንባቢ ልብ በል ይህ በዘፍጥረት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የሚገኝ ስለ ኢትዮጵያዊው ካህን መልከ ጼዴቅ  በከፊል የሚገልጽ ነው።ምንጩም አስርጊዜ የእግዚአብሔርን ቃል በመሰረዝና በመደለዝ ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት የሚለፉትን ምዕራባውያን የሚጠቀሙበት የኪንግ ጀሚስ ቨርዥን ነው(King James Version) መጽሐፍ ቅዱስ።ታድያ እስቲ የእንግሊዝኛው ቃል ደግማቹ አንብቡት Melchizedek ይላል።ማለትም መልከ ጼዴቅ ይህ ቃል መቼም በእግሊዝኛ ቀጥተኛ ፍቺ ሊኖረው አይችልም።ምክንያቱም የግዕዝ ቃል ነውና።ይህንን ግን መሰረዝና መደለዝ አልቻሉም ይባስ ብለው በመጽሓፋቸው ይዘዉት ይዞራሉ እንጂ። አሁንም ኢትዮጵያ የሚለው ቃል በኩሽ ተክተውታል።ይህም ግዕዝ የመጀመርያው ልሳነ ሰብእ ለመሆኑ አንዱ ማስረጃ ይሆናል።በተጨማሪም የኢትዮጵያ ታሪክና የግዕዝ ቋንቋ ከአክሱማዊ ስልጣኔ ብቻ የሚያይዙት የፖለቲካ ውላጅ ግለሰቦች የኢትዮጵያና የግዕዝ መነሻ አንድና ከአክሱም ስልጣኔ ሺና ከዚያ በላይ አመታት በፊት መሆኑ እንዲረዱት ያደርጋል። ከአይሁዳዊነት ኢትዮጵያዊነት እንደሚቀድም የአግአዝያን እንቅስቃሴ አራማጆች ልብ አድርጉ።

ምዕራባውያን በአሁኑ ጊዜ ግዕዝን ለማጥናትና የብራና መጻሕፍትን ለመዝረፍ መሯሯጣቸውም ለዚ ነው።በ UNESCO እንዲመዘገብልን የምንፈልጋቸው ቅዱሳት ቅርስም እኛው መጀመርያ እንጠቀምባቸው እንዳንባቸው። UNESCOና የአለም አብያተ ክርስትያናት ምክር ቤት (WCC) በአንድ ምድብ የሚሰራ የኢሉሚናቲ ሴራ ማስፈጸምያ በመሆኑ እንጂ ለኛ አስቦ አይመዘግብልንም።ገንዘብ ከመሰብሰባችን በፊት ስለ ነፍሳችን ብለን  ቅዱሳን ቦታዎች ለመዳን እንጠቀምባቸው።በተረፈ UNESCO የሚመዘግባቸው ቅርሶች ምዕራባውያን ሊድንባቸው ሳይሆን ሊያረክስዋቸውና የክህደት ተግባራቸው ሊፈጽምባቸው ወደ ኢትዮጵያ እንዲጎርፉ ለማድረግ  ነው።

 ኢትዮጵያዊነት ታላቅ ክብር ነው።

No comments: