EAR

አዲስ ነገር

Saturday, 14 October 2017

የሰንደቅ ዓላማ ቀንና የይሁዳ አንበሳ


 ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ

ሀገረ እግዚአብሔር ኢትዩጵያን ለማጥፋት የዲያብሎስ እንደራሴ ሆኖ የሚያገለግለው ህወሓት ሰማያዊ የሆነው ሰንደቅ ዓላማዋ ወደ ተለያዩ ክልሎች ቀለማት በመከፋፈል ለማጥፋት እየጣረ ቢሆንም አልተሳካለትም።ዘላለም አይሳካለትም።ባለ አምስት ጫፍ ኮኮብ (Pentagram) ያረፈበት ሰንደቅ ዓላማ በማውለብለብ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በማለት የዲያብሎስ ባለሟል መሆኑ በግልጽ እያስመሰከረ ይገኛል።


ጥንታዊው የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ የእግዚአብሔር ቃልኪዳን ገላጭ ነበር።ይህም
አረንጓዴ ብጫና ቀይ (ኪዳነ ኖህ) ፦ እግዚአብሔር ከኖህና ከሰብዓዊ ፍጡሩ ጋር ያደረገው ቃልኪዳን ዘላለማዊ ምልክቱ በቀስተደመና ገዝፎ ይታያል።ይህም በኢትዮጵያውያን ዘንድ በሰንደቅ ዓላም ተጠብቆ ይገኛል።

የይሁዳ አንበሳ (ኪዳነ ዳዊት) ፦ እግዚአብሔር ከዳዊት ጋር ያደረገው ኪዳን ሲሆን እሱም በመሎኮታዊ ዘውድ ዙፋን ምልክትነት ይታወቃል። የዳዊት ልጅ እየተባለ በተጠራውና ሞዓ አንበሳ ዘእምነገደ ይሁዳ ሥርወ ለዳዊት ማለትም የዳዊት ዘር ሥር ከሆነው ከይሁዳ ነገድ የተወለደ አንበሳ አሸናፊ ተብሎ በራዕይ ዩሓንስ የአዋጅ ቃል የተነገረለት ጌታችን መድሓኒታችን  እየሱስ ክርስቶስ ነው።
የይሁዳ አንበሳ ትውክልት ያለበት የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ምድራዊ የሆኑት ነገሥታት የማይወክል ነው።በእግዚአብሔር ባላቸው እምነትና ጽናት ግን ለዘመናት ሲጠቀሙበት ኖሮዋል።

አስገራሚውና አስደናቂው ነገር በተዋህዶ እምነት ስር እየኖሩ ይህንን አምላካዊና የቃልኪዳን ትውክልት የሆነው ሰንደቅ ዓላማ በመካድና በማጥላላት ዲያብሎስ በብሔር ብሕረሰቦች ሽፋን ራሱን ያገነነበት ባለ አምስት ጫፍ ኮኮብ ያለበት ሰንደቅ አላማ መጠቀማቸውና ማምለካቸው ነው።

ዓርብ  ጥቅምት 3, 2010 ዓመተ ምሕረት




No comments: