EAR

አዲስ ነገር

Friday, 24 November 2017

ሰውና ሥልጣን!


ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ


የዓለም መገናኛ ብዙሃን የሃገረ ዚምባብዌ መሪ ሮበርት ሙጋቤ ከስልጣናቸው መውረዳቸው እየዘገቡ ነው።ይህ ሁኔታም ለምዕራባውያን የደስታ ስሜት እንደሚፈጥር ምንም ጥርጥር የለዉም።የገዢዎች የረቀቀ ብልሃት ጠንክሮ የዜጎችች ፍረሃት ግልጽ ሁኖ የሚታይበት ቦታ አፍሪካ ነው። እንደልባቸውም አምባገነኖች የሚርመሰመሱበት አፍሪካ ነው። ግን ማነው አምባገነን፧ ማነው ጠቅላይ አምባገነን መንግሥት(totalitarian) አስተሳሰብ አራማጅ፧ ማነው ለዲሞክራሲና ሰብአዊ መብቶች መከበር የቆመው ፧ ይህን መረዳት ደግሞ እዚያ አስቸጋሪ ነው።

ለመሆኑ አምባገነኖች እንደሚነግርላቸውማንም የማይደርስባቸው ብሩህ አእምሮ ያላቸው ሰዎች ናቸው፧ወይስ ሳይኮፓትዕብዶች ናቸው ወይስ ልዩ ፍጡር፧ እግዚአብሔር ለቅጣት የላካቸው፧ ወይስ አንዳች ዓይነት ከጨለማ ቤት የተላከብን ዲያቢሎስ የሚጋልባቸው፧ ይህ ካልሆነ ጠቅላይ አምባገነን መንግሥት አስተሳሰብ አራማጆች ታዲያ ምንድን ናቸው፧ እነዚህን ጥያቄዎች አንስተን (በአንድ ቀን ፈጽሞ አብራርተን አንጨርሰውም) ቀስ እያልን እያዘገምን ችግሩን ከበን ጥያቄውን አገላብጠን ለመመለስ፣ ለመፍታት እንሞክራለን

የፖለቲካ ጽንሰ ሓሳቦች ብዙ ይመስላሉ እንጂ ወዳጄ፡ በጣም ጥቂቶችና በጣት የሚቆጠሩ ናቸው። ወደ ሥልጣን የሚወስዱ መንገዶችም ወደዚሁ ወደ ሥልጣን የሚያደርሱና እዚያው ሥልጣን የሚያቆዩ ብልሃትና ዘዴዎች ውስን ናቸው። እነሱም በዚህች ዓለም አንድ ሁለት ተብለው ይቆጠራሉ።

ተወደደም ተጠላም፣ አውቀንም አላወቅንም ምናልባት በቃላት ጨዋታ መታለልም አለ፡ ብዙ ሰው ብዙ አምባገነን  ዝም ብሎ ተቀብሎ በትከሻው ላይ ጭኖ እነሱን በደስታም ወይም በሐዘንም በደንብ የማስተናገድ በሽታም በዓለም ላይ ፡አከባቢአችንን ማየት ይበቃል፡ይታያል። ለምን እነደዚህ ሆነ፧

ትልቁም ትንሹም ጠቅላይ አምባገነን መንግሥት አጋንንት በአፍሪካ ሆነ በሌላ አካባቢ  በሕዝብ ሳይመረጥ፡ ቢያንስ አንድ ቀን ብትሆንም ቤተ፡መንግሥት ገብቶ በሰው ላይ ቀልዶ በሕይወቱ ለትንሽ ደቂቃና ለጥቂት ቀናትአመታቱንማ የሚመኘው ብዙ ነው፡ ተደስቶ መሞት ይፈልጋል። ለምን፧

ይህ ፍላጎት ይህ ምኞት ከየት መጣ የሰው ልጅስ ለምን ይህን ያልማል፧ ሌላ ጥያቄ። ለመሆኑ በአፍሪካ ይህን ማለም ሲቻልና ይህን ማድረግ ሲፈቀድ ሌላውስ ለምን ወይም በምን ምክንያት እንደዚህ ዓይነቱ ቅዠት ይከለከላል፧
ለመሆኑ በምን ዘዴ አድርገው እነሱ ተቆጣጥረው ያዙት፧

ተወደደም ተጠላም፣ አውቀንም አላወቅንም ምናልባት በቃላት ጨዋታ መታለልም አለ፡ ብዙ ሰው ብዙ አምባገነን ዝም ብሎ ተቀብሎ በትከሻው ላይ ጭኖ እነሱን በደስታም ወይም በሐዘንም በደንብ የማስተናገድ በሽታም በዓለም ላይ አከባቢአችንን ማየት ይበቃል፡ይታያል። ለምን እነደዚህ ሆነ

ይህ ደግሞ ምክንያት አለው።
የሰው ልጆች በአንድ በኩል በባሕሪአቸው ደካማ ናቸው። በሌላው ጎኑ የሰው ልጆች መንገዱን የሚያሳያቸው መሪ/መሪዎች ይፈልጋል። አንደኛው ምክንያት ደህና ቀን ይመጣልብሎ በተስፋም ያንቀላፋል። ሆዳም፦“ – ብዙዎቹ እንደሚሉት፡ ብቻ ሳይሆን ምን አገባኝ ልጆቼን ላሳድግበት፣ ለምን የእሳት ራት ልሁንብሎም ሊያስብ ይችላል። አልፎ ተርፎም ሁሉም አንድ ናቸው። ልዩነት በመካከላቸው የለም።ያም አምባገነን ይህም አምባገነን ብሎም እርሙን አውጥቶ ተስፋ ቆርጦም ይሆናል። (አንድ ሰው ደግሞ አይቶ አውጥቶ አውርዶ ይህን ከአለ አይፈረድበትም፦



ሰው ልጅ/ልጆች ጥቁሩም ነጩም ከገባበት ችግር የሚያወጣውን አለቃ ፈልጎ ከአገኘ ይከተለዋል።አንዳንዴ ሌላው ብድግ ብሎ የተከተለውን መሪ ይኼ ሁሉ ሰው አይሳሳትም  ስለዚህ እኔም ብቻዬን ከምቆም ብሎ እራሱን አታሎ እሱም ተነስቶ አብሮ ይጮሃል።ይህን የተገነዘበ አንድ እሳት የላሰ መሪ ደግሞ ጸሐፊዎች በትክክል እንደአሰፈሩት እንደ ከብት አንድ ቀን የሚነዳውን አገልጋይ ተከታታይ ወይም የሚሞትለትን ከመሞት የማይመለሰውን ሎሌ ቀስ በቀስ ሳይታወቅበት በብልሃት ኮትኩቶ አዘጋጅቶ አስታጥቆ ወደ ጦር ሜዳ ይልከዋል።እንዴት፧ በምን ዘዴ፧

የሰው ልጆችን ከገቡበት ችግሮች ጎትቶ የሚያወጣ መሪ ነብይ አንድ ሳይሆን እነሱ ብዙ ናቸው። እንደሚታወቀው የተለያዩ መሪዎች እኔ እሻላለሁ እኔ እብልጣለሁ ብለው ይነሳሉ። እነሱም የሰውን ልጆች አእምሮ አስክረው ለመያዝታሪክ ላይ ብዙ አካባቢዎች እንደምናየውየሰበካ ፉክክርውስጥ ገብተው ይገጥማሉ።

አንዱ ቡድን(ኢትዮጵያን ጥሩ ምሳሌ ናት ) ተነስቶ አንድ ነገር ይላል። ሌለው ቡድን ለየት ያለ ብልሃት ይቀይሳል። ሦስተኛው ሁለቱን ገፍትሮ የራሱን አዲስ አስተሳሰብ ለማስፋፋት ይሞክራል። አራተኛው ዱላ ወይም ጠበንጃ ይዞ ሁሉንም ጭጭ ለማድረግ ይነሳል።አምስተኛው ላስታርቅ ብሎ ቤንዚን አርከፍክፎ እሳቱን በሁሉም አቅጣጫ ይለኩሳል። ስድስተኛው ከጎረቤት ጠላት ከባዕድ ጋር ገጥሞ ሁሉንም ለመውጋት መላ ይመታል። ሰባተኛው ኅብረትና አንድነት ብሎ ከፋፍሎ ተራ በተራ ተቀናቃኞቹን መቶ ኮርቻው ላይ ጉብ የሚልበትን መንገድ ያመቻቻል። ስምነተኛው። ረጋ ብሎ የሚያስብ ሰው ደግሞ ለመሆኑ ትክክለኛው ከእናንተ ሁሉ ማን ነው፧ ብሎ ይጠይቃል።ለመሆኑ ከእነሱ ሁሉ ትክክለኛው ማን ነው፧ ሁሉም፧ ወይስ አንዱ፧ ወይስ የተወሰኑት፧ ወይስ ሌላ ገና ያልተወለደው፧

እዚህ ላይ አንድ ሓቅ ቢጠቀስ በሰው ልጆች ላይ በተለያዩ አካባቢዎችከድንጋይ ዳቦ ዘመንከኦሪት ዘፍጥረት እስከ አሁን ጊዜ ድረስ እስከ 21ኛው ክፍለ ዘመን በአታላይ የፖለቲካ መሪዎች ብልጣ ብልጥነት ብዙ እጅግ ብዙ ተቀልዶበታል።

መቀለድ ብቻ ሳይሆን በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ የዓለም ሕዝቦች፡ አንደኛና ሁለተኛ ዓለም ጦርነት ተመልከት፣ በመደብ ትግል ስም የተለኮሱትን ጥፋቶች መለስ ብለህ እይ፣ በማራኪ ስም የተካሄዱትን አብዮቶች ቁጠር፣ የብሔር ትግል የሚባለውን የሕዝቦች ፍጅት ጨምረህ አብረህ አስተውል በእነዚህ ሁሉ ምክንያቶች ንጹህ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።ታድያ መፍትሔው ምንድነው፧ በፈጠረህ እግዚአብሔር ብቻ ሙሉ እምነት በማድረግ ነገሮች የመጡበት መንገድ በመገንዘብ ነጻነትህን መጠበቅ።ከአለማዊ ፖለቲከኞች የሚገኝው ትርፍ የለም ይህም የታሪክ ሰነዶችና አሁን የምናያቸው ሁኔታዎች ግልጽ አስረጂ ናቸው።

አርብ ኅዳር 15,2010 ዓመተ ምሕረት

No comments: