EAR

አዲስ ነገር

Sunday, 14 January 2018

ቢትኮይንና አውሬው - 666

ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ


ቢትኮይንን እ.ጎ.አ 1988 የተነበየበት የዘኢክኖሚስት መጽሔት ሽፋን

በአሁኑ ወቅት ቢትኮይን ስለሚባል አዲስ የገንዘብ ዝውውር መንገድ በተደጋጋሚ እየሰማን ወይም እያነበብን ነው። ይህ አዲስ ቴክኖሎጂ ምንድነው፧ እንዴትስ ይሰራል፧ በቀጣይ የአለማችን ሁኔታስ የሚፍጥረው ለውጥ ወይም ተጽዕኖ ምንድነው፧

እ.ጎ.አ 1988 የታተመው የዘኢኮኖሚስት መጽሔት የሽፋን ታሪክ ምስል የሚያሳየው ዛሬ በጣም የታወቀው የኤሌክትሮኒክ ምንዛሬ  ቢትኮይን (Bitcoin) ጋር ተመሳሳይ ነው። ስዕሉ ይበልጥ አስገራሚ የሚሆነው ደግሞ ቴክኖሎጂው እውን የሚሆንበት ወይም ተግባር ላይ የሚውለው እ.ጎ.አ 2018 ላይ መሆኑ መጥቀሱ ነው። አሁን የያዝነው ዓመትም እጎአ 2018 ነው። ዘኢኮኖሚስት መጽሔት ቢትኮይንን ከ 20 አመት በፊት ትንቢት የተናገረለት በ አጋጣሚ ወይስ በዕቅድ፧

መጽሔቱ ስለ ቢትኮይን ሲገልጽ ይህ አዲስ አለም አቀፋዊና አዲስ የዓለማችን ገንዘብ እንደሆነ ያብራራል። ቢትኮይን BITCOIN አሁን ባለንበት ሰዓት አብዛኛው የአለም ህዝብ ለመገበያየት የሚጠቀመው ገንዘብን ነው። ቢትኮይን ደግሞ በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ተቀባይነትን እያገኘ የመጣ የክሪፕቶግራፊ ቴክኖሎጂን የሚጠቀም ዲጂታል ገንዘብ ነው ማለት ይቻላል።

ገንዘብ የሰው ልጅን ባርያ ለማድረግ የአለማችን አንድ ከመቶ የሆኑት የኢሉሚናቲ የደም ሓረግ ያላቸው ሰዎች የሚጠቀሙበት መሣርያ መሆኑ ማወቅ ይገባናል። ይህም አብዛኛውን የ አለማችን ተፈጥራዊውና ሰው ሰራሹን ሃብት በነዚህ ጥቂት አካላት ቁጥጥር ስር በማደረግ የሃብት ልዩነቱ በማስፋት የተቀረው ድሃው ህዝብ በቁጥጥራቸው ስር ለማድረግ ይረዳቸዋል። አዲሱ የቢትኮይን ዓይነት ምንዛሪ በእውነት እነዚህን ችግሮች መፍታት ይጀምራል፧

የኢሉሙናቲዎች የመጨረሻው ዕቅድ መላው የሰው ዘር በሚመሰርቱት አንድ የዓለም ስርዓት(One World Order)ለ አውሬው-666 ማስገዛት ነው።

ቢትኮይን እንዴት ይሰራል

ራሱን ሳቶሺናካሞቶ በማለት የሚጠራው፣ ነገር ግን በአካል ማንነቱ በማይታወቅ ግለሰብ  የተመሰረተ ነው ቢትኮይን።  ቢትኮይን ማንም በነጻ የሚጠቀመው “Open Source” ሶፍትዌር አገልግሎት የሚሰጥ ነው።

ቢትኮይን በመጠቀም የሚደረጉ የገንዘብ ዝውውሮች ድብቅ እና ዝውውሩን የሚያካሂዷቸውም ሰዎች ስም አልባ ናቸው። ማለትም ፩ ሰው ለሌላ ሰው ቢትኮይን ማስተላለፍ ቢፈልግ ልክ እንደ ባንክ_አካውንት ቁጥር ያለ የቢትኮይን አድራሻ ተብሎ የሚታወቅ አካውንት ቁጥር አለ፤ ነገር ግን ይህ የቢትኮይን አካውንት ቁጥር በትክክል የማን እንደ ሆነ ከባለቤቱ ውጪ ማንም ስለማያውቅ የሚደረገው ዝውውር ከ፩ የቢትኮይን አካውንት ቁጥር ወደ ሌላ የቢትኮይን አካውንት ቁጥር ብቻ ይሆናል ማለት ነው።ይህም ያለ ምንም ወጪ የአለም አቀፍ የግንኝነት መረብ (internet) በመጠቀም ብቻ በቀላሉ እና ፈጣን በሆነ መልኩ ይሰራል።

ልውውጡና እና ክፍያውም የሚፈጸመው ለዚሁ ተብለው በተዘጋጁ የኮምፒውተር ፕሮግራሞች፣ የስማርት ስልክ መተግበርያዎችና በተበተታተነ የመረጃ መረብ የመረጃ ቋቶች አማካይነት ነው። በክሪፕቶከረንሲ (CryptoCurrency) አሰራር ሁለት ተጠቃሚዎች ፍጹም እርስ በእርስ ሳይተዋወቁ ወይንም የተለምዶ ማዕከላዊ የገንዘብ ተቋማት ፍጹም ጣልቃ ሳይገቡ የሁለቱንም ጥቅም የሚያስጠብቅ የገንዘብ ልውውጥ ወይንም ግብይት ሊያደርጉ ይችላሉ።

ቢትኮይን ከአውሬው ጋር ስላለው ግንኙነት
የአውሬው ምልክት በመጽሐፍ ቅዱስ በየውሃንስ ራዕይ ላይ የተገለጸው ነው። በተለይ በየውሃንሰ ራዕይ ምዕራፍ ፲፫ ቁጥር ፲፯ ላይ እንደተብራራው የአውሬው ምልክት የሌለው ሰው ምንም አይነት ነገር ማግዛት እንደማይችል ነው። የአውሬውም ስም ወይም የስሙ ቍጥር ያለው ምልክት የሌለበት ማንም ሊገዛ ወይም ሊሸጥ እንዳይችል ያደርጋል ሲል ይገልጻል።

ስለዚህ እራስዎን ቢትኮይን ከዚህ ምልክት ጋር እንዴት እንደሚዛመድ እየጠየቁ ይሆናል ፧ በአሁኑ ወቅት ይህንን የቢትኮይን አገልግሎት ለማግኝት የተወሰኑ ሰዎች በቀኝ እጃቸው ላይ የቢትኮይን ቺፕ (microchip) ተተክሎላቸዋል። የየውሃንስ ራዕይ የሚነግረንም ይህንን ነው። አውሬው ሰዎች የራሱ ለማድረግ በግንባራቸውና በቀኝ እጃቸው ምልክት ያደርግባቸዋል። ምልክቱም ማይክሮ ቺፕ ነው።

አንድ የዓለም ገንዘብ

ኢሉሚናቶዎች አንድ የዓለም መንግስሥት በመመስረት የሰው ዘርን ለአውሬው ለማስገዛት በሚያደርጉት ጉዞ አንድ የዓለም ገንዘብ መዘርጋት አንደኛው የማስፈጸምያ መንገድ ነው። ይህም የቢትኮይን አገልግሎት በመጠቀም ሊፈጸም የሚችል ነው።
ኢሉሚናቲዎች በሰው ዘር ለሚፈጽሙት ሴራና ደባ አስቀድመው በተለያዩ መንገዶች ፍንጭ ይሰጣሉ። ይህም በተለያዩ ዘመናት ተስተውሏል። ቢትኮይንም ከ፳ አመት በፊት የተተነበየ እንጂ ዝም ብሎ የተከሰተ አይደለም። ይህም የኢሉሚናቶዎች የሰው ዘርን ለመማረክ የሚያደርጉት ጉዞ የተደራጀና የታቀደ እንደሆነ የሚያመለክት ነው።
የእግዚአብሔር ቅዱስ ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስም የሚነግረን ይህንን ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ የተቀመጠ አንድም ትንቢት ሳይፈጸም የቀረበት ጊዜ የለምና ወደ ፈጣርያችን በመጠጋት መጨረሻችን እንዲያሳምርልን እንለምን።

ሰኞ ጥር7, 2010 ዓመተ ምሕረት


No comments: