በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች የዙስ የሚል ጽሑፍ ያለባቸው ልብሶች ማየት እየተለመደ ነው። የዙስ የአሜሪካዊው ሙዚቀኛና የኢሉሚናቲ ወኪል የሆነው ካኒ ዌስት በ2013 እ.ጎ.አ በሮክፊላ የሙዚቃ አሳታሚ ድርጅት አማከኝነት የለቀቀው የሙዚቃዎች ጥራዝ (Album) ነው።
ይህ የሙዚቃ ጥራዝ ከመናፍስት ምስጢራዊ ማህበረሰቦች ጋር በቀጥታ የተገናኙ መልዕክቶችን እና ተምሳሌቶች የታጨቀ ነው። ካኒ ዌስት የዙስ የሚል ርዕስ መጠቀሙ የተጠናወተው ራስን ከፍ የማድረግ ሰይጣናዊ ባህሪ ነው። ምክንያቱም ራሱን ከሰውነት በመውጣት ከእየሱስ ክርስቶስ ጋር ያወዳደረበት ነውና። ሰውነት ወደ አምላካዊነት የማሳደግ ክፉ ፍላጎት ነው። በክርስቲያኖች ዘንድ በምድር ላይ የእግዚአብሔር አምሳያ እንደሆነ
የሚቆጠረው
ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው።
ካኒ ዌስት በየሙዚቃ ጥራዙ ካካተታቸው ሙዚቃዎች አንዱ "እኔ አምላክ ነኝ" የሚል ርዕስ አለው። ይህንን ጽንሰ፡ሐሳብ ለአድናቂዎቹ ግልጽ ለማድረግ ግን አልቻለም።
እስቲ የግጥሙ ስንኞች እንመርምራቸው።
"ክርስቶስን አናገርኩት
ጌታ ሆይ፥ ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ፧ አለው
እኔም እንዱህ አልኩ በርዶኛል
እነዚያን ሚሊዮኖች ለማቆየት እየሞከሩ ነው
ከሁሉ ከፍ ያለ ሰው አውቃለሁ
እኔ ግን በጣም የቀረበ ነኝ
rሚካሳ ሱ
ካሳ
ያ ነው ኮሳ ኖስትራ
እኔ አምላክ ነኝ
እኔ አምላክ ነኝ
እኔ አምላክ ነኝ "
በዚህ የዘፈኑ ስንኝ ካኒ ዌስት ራሱን ከጌታችንና መድሓኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ጋር ራሱን በተመሳሳይ ደረጃ ማስቀመጡ ነው። እግዚአብሔር ራሱ ይቅር ይበለው። እኛንም ይቅር ይበለን ከማለት ውጪ ምን ይባላል፧
«እጅግ በጣም ከፍ ያለ እኔ ግን በጣም የቀረበ ነኝ» የሚለው ስንኝ በመዝሙረ ዳዊት ያለው የእግዚአብሔር ቃል ሊያመለክተን ይችላል።
"እናንተ አማልክት ናችሁ ፣ ሁላችሁም የልዑል እግዚአብሔር ልጆች ናችሁ።" ----መዝሙር ፹፩፡፮
በባህላዊ ሃይማኖቶች እና ሚስጥራት ልዩነት አለ። የአብርሃም ሃይማኖቶች አንድ አምላክ መኖሩን ይቀበላሉ። የተለያዩ
ሰይጣን የሚያመልኩ የኢሉሚናቲ ቤተ እምነቶች ግን ይህንን የሚክዱ ሲሆኑ በተጨማሪም እውነተኛ ክርስትያኖችን ልያታልል የሚችል ክርስትያናዊ
የሆነ ምልክቶችና ኪነ ጥበባዊ ውጤቶች ይጠቀማሉ። ካኒ ዌስትም ያደረገው ይህንን ነው።
ይህ ምስል የመጀመርያው የየዙስ
የዘፈን ጥራዝ ሽፋን እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ ምስል ነው። በምስሉ የሚታየው የተዛባ የክርስቶስ የፊት ገጽታ ነው። ሆኖም የዘፈን
ጥራዙ ታትሞ በሚሰራጭበት ወቅት ይህንን ምስል ለመጠቀም አልደፈረም። በብዝዎች ዘንድ ተቃውሞ ልያስነሳበት እንደሚችል በማሰብ ሊሆን
ይችላል።
ይህ ብርሃናዊ ምስል የሚያሳየን
ካኒ ዌስት የክርስቶስ ምስል ያለበት ሰንሰለት አንገቱ ላይ አጥልቆ ነው። ትርጉሙም የኢየሱስን ተምሳሌት የማይነካ መለኮታዊ ተምሳሌት
አለመሆኑን እና እርሱ ወደዚያም መድረስ እንደሚችል በትዕቢት ለመግለጽ ነው።
ታድያ ይህንን ሰይጣናዊ የዘፈን ስያሜ የሆነውና የጌታችን መድሓኒታችን እየሱስ ክርስቶስ መሎኮታዊ ኃይል ዝቅ ለማድረግ የሚደፍር YEEZUS የዙስ የሚል ቃል በሚለበሱ ልብሶች አትመው ፋሽን በሚል ሽፋንና ማታለያ እያቀረቡልን ነውና ከመልበስና ከማስተዋወቅ ራሳችንና ሌሎች ሰዎችም መጠበቅ አለብን።
No comments:
Post a Comment