EAR

አዲስ ነገር

Tuesday, 23 January 2018

ነፍሳት የእግዚአብሔር ልጆችን ከፈርዖን ባርነት ነጻ ለማውጣት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ነበራቸው


ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ


መጽሐፈ ቅዱስ አስገራሚና አስደናቂ የሆኑ ታሪኮችን የያዘ ነው። ደጋግመህ በምታነብበት ጊዜው ሁሌ አዲስ ነው። ዛሬ መጽሐፍ ቅዱሴን ሳነብ በጣም ካስገረሙኝ ነገሮች በመቀንጨብ ላንባቢ ማካፈል ወደድኩኝ።

መጽሓፉን በምናነብበት ወቅት  ያልተለመደ ሃይል ስለተጎናጸፉ ሰዎች፣ ምስጥራዊ የሆኑ መሣርያዎች፣ እንግዳ የሆኑ ድርጊቶች፣ ስለ ጠፉ ጥንታዊ ከተሞችና እስከ አሁን ሙሉ ለሙሉ ልንረዳቸው ያልቻልናቸው ትንቢቶች እናገኛለን።

ለዛሬ ትኩረቴ ያደረኩት ግን በመጽሐፍ ቅዱስ የዘጸአት ክፍል በተጠቀሱት አስገራሚ ጸባይና አስተዋጽኦ ስለ ነበራቸው እንስሳትና ነፍሳት ነው። በዘጸአት የተጠቀሱት ነፍሳት ሰዎችን በመግደል ብዙ ተዓምራቶች የሰሩ ናቸው። የእግዚአብሔር ወኪልና መልዕክተኛ የነበረው ሙሴ የግብጻውያን ንጉሥ ፈርዖን እስራኤላውያን ነጻ የማይለቃቸው ከሆነ በግብጻውያን ላይ መአት እንደሚደርስ አስጠንቅቆት ነበር። ፈርዖንም እስራኤላውያን ነጻ ባለመልቀቁ የግብጻውያን ውሃ ወደ ደም ተቀይሮ ነበር።

እንቁራሪቶች - ፈርዖን አሁንም ቢሆን የእግዚአብሔር ትዕዛዝ ባለማክበሩ በሚልዮን የሚቆጠሩ እንቁራሪቶች ወረርሽኝ እንዲከሰት ሆኗል። እንቁራሪቶቹ በግብጽ ምድር ከሁሉም የውሃ ምንጮች ነበር የወጡት።

ቅማል - ፈርዖን የመጀመርያዎቹ ሁለት የእግዚአብሔር ማስጠንቀቅያዎች በመፍራት እስራኤላውያንን ነጻ ሊለቃቸው አልደፈረም። ይህ ተከትሎም እግዚአብሕሄር ሙሴን አለው፥ ‹‹አሮንን በትርህን በእጅህ ዘርጋ፤ የምድሩንም ትቢያ ምታ በለው፤ ቅማልም በግብጽ ሀገር ሁሉ በሰውና በእንስሳ ላይ ይወጣል።››  አሮንም የታዘዘው አደረገ።

ተናካሽ ዝንብ - ለሦስተኛ ጊዜ ፈርዖን የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ መፈጸም አልፈለገም። በግብጽ የደረሱት መአቶች ሊመልሱት አልቻሉም። እግዚአብሔር ሙሴን ወደ ወንዝ ላከው፤ ሙሴም ፈርዖን የእግዚአብሔር ልጆችን እንዲለቃቸው ይህንን የማያደርግ ከሆነ ተናካሽ ዝንቦች እንደሚለቅለት አስጠንቅቆት ነበር።


ማክሰኞ ጥር 15, 2010 ዓመተ ምሕረት

No comments: