EAR

አዲስ ነገር

Wednesday, 24 January 2018

ከፖለቲካና ገንዘብ ውጪ የሆነች ምድር - የዘመኑ ዩቶጵያ


ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ


ስለ ዩቶጵያ ሰምታቹ ወይም አንብባቹ ይሆናል። ዩቶጵያ የሰላም፣ ፍቅር፣ አንድነትና ደስታ ምድር ነበረች። ይቺ ምድር ብዙ ሰዎች ምናባዊ እንደሆነችና በተጨባጭ ያለች እንዳልሆነች ይገልጻሉ። ዩቶጵያ የሚለው ቃል ለመጀመርያ ጊዜ የተጠቀመው ግሪካዊው ባለቅኔ ሆሜር እንደሆነ ይነገራል። ሆሜር ዪቶጵያ ብሎ የገለጻቸው የዚያን ጊዜ ኢትዮጵያውያን ህዝቦች ነበር። ኢትዮጵያዊያንን ሲገልጻቸው ባጭሩ ከአማልክት ጋር የሚኖሩ የተለዩ ሰዎች እንደሆነ አድርጎ ነው።

15ኛው ክፍለ ዘመን ቶማስ ሞር የሚባል የሃገር እንግሊዝ ቄስ ሃገር እንግሊዝን ከዩቶጵያውያን/ኢትዮጵያውያን ልምድ በመውሰድ ኑራቸው መቀየር የሚቹሉበት መጽሐፍ አዘጋጅቶ ነበር። ምክንያቱም የዩቶጵያውያ/ኢትዮጵያውያን ጥንታዊ የኑሮ ሥርዓት ገነት ውስጥ የመኖር ያህል ስሜት የሚሰጥ ነበር። በዩቶጵያውያን የኑሮ ስርዓት ህዝቦች በጋራ በመስራት በጋራ የሚኖርበት ሃብት፣ ገንዘብ ንብረት ለግል ማካማቸት የማይችሉ ሲሆን በጋራ ያመረቱት ምርትና ምግብ በእኩል በመካፋል ያለልዩነት በሰላም በደስታ የሚኖሩበት ነው። በሃገራችንም ለዚህ የኑሮ ስርዓት የሚቀራረብ በአቶ ዙምራ የሚመራ የአውራምባ ማህበረሰብ አለ። ይህ ማህበረሰብ ከዩቶጵያውያን የሚለይበት ነገር ገንዘብ መጠቀሙ ይመስለኛል።

የዩቶጵያውያን የኑሮ ስርዓት በዘመኑ ይኖራል ወይም ይመሰረታል ብሎ ማሰብ ሊከብ ይችላል። ቢሆንም የዘመኑ ዩቶጵያውያን ሊባሉ የሚችሉ ማህበረሰብ ግን አሉ። ሳይነሳዊ ብልወለድ አይደለም፤ በሳይንሳዊ ልብወለድ ፊልሞች የምናያቸው ከምድራችን በሚልዮን ኪሎሜትሮች ርቆ የሚገኝ ቦታ አይደለም። እውነታው ይህ ነው፤ የዚህ ማህበረሰብ አባላት የሚኖሩት የፖለቲካና የገንዘብ ሥርዓት በሌለበት መንገድ ነው። ፖለቲካ፣ ገንዘብና የውሸት ሃይማኖቶች የምድራችን የችግሮች መሰረት እንደሆኑ በግሌ ይሰማኛል።

የማህበርሰቡ አባላት የሚኖሩበት ቦታ አውሮቪለ ይባላል። ህዝቦቹ ከተለያዩ ብሔርና ባህል ካላቸው 50 ሃገራት የመጡ ናቸው። የአውሮቪለ ከተማ እ.ጎ.አ 1968 የተመሰረች ነች። የከተማዋ አባላት የፖለቲካ ሰርዓት ስለሌላቸው ጨቛኝ ተጨቋኝ አካል የለም። በተጨማሪም ገንዘብ ጥቅም ላይ ሰለማይዉል የሃብት ልዩነትም ስለሌለ ጦርነትም ሆነ ጥላቻ ሊኖር አይችልም።

በከተማዋ ድረ-ገጽ የሰፈረው መልዕክትም የሚከተለው ይላል። የአውሮቪለ ከተማ አላማ አለምአቀፋዊትና ከተለያዩ ሃገራት የተውጣጡ ወንድ ሴት ከፖለቲካና ብርሔተኝነት ነጻ በሆነ ሰላማዊና ወዳጅነት በሞላበት ጠቅላላ የሰው ልጅን በአንድነት የሚኖርባት ከተማ ማድረግ ነው።

መጽሐፍ ቅዱሳችን የሚነግረን ገነት ምድር ውስጥ እንደነበረች ነው። እኛስ ይህ አልናፈቀንም፧ መቼም ምኞት አይከለከልም።


ሮብ ጥር 15, 2010 ዓመተ ምሕረት

No comments: