EAR

አዲስ ነገር

Wednesday, 27 June 2018

ኢትዮጵያና አሜሪካ !


ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ፦

ኢትዮጵያ፡ የዘፍጥረት ምድር ነች፤ ይህ ሲባል ሰፊ ትርጉምና አንድምታዊ ድምዳሜ ያለው ነው።  እግዚአብሔር የሰው ልጅን የፈጠረበት የሰው ልጅ በኩር አዳም የእግር አሻራ ያለበት፣ አዳምና ሄዋን ፳፬ ሰዓታት ለፈጣሪያቸው በገነት (ኢትዮጵያ) ውስጥ ሆነው የሚያመሰግኑበት ድንቅ ቦታ ነበር፤ አሁንም በሰው ልጆች ሓጥያት ባይታይም ግን አለ። በዚህ ምክንያት ነው ዲያብሎስና የርሱ አገልጋዮች የምስጥር ማኅበራት የዓለም ህዝብ ለዲያብሎስ ለማስገዛት ዋነኛ ትኩረታቸው  ኢትዮጵያ ገነት አድርገው እየተንወሳቀሱ ያሉት። የታሪክ ማኅደር እንደመዘገቡት ሳይሆን የመጀመርያው የዓለም ጦርነት የተካሄደው በኤዶም ገነት ነበር፤ በሄዋንና እባቡ መካከል የተካሔደው ጦርነት። ይህ ጦርነት እስከ ዓለም ፍጻሜ የሚቀጥል ነው። መዳረሻዉም ገነት የሆነቺው ምድረ ኢትዮጵያ መውጋት ነው።

አሜሪካ፦

አሜሪካ ከ፪ ሞቶ ዓመታት በፊት በ”ነጻ-ግንበኞች (freemason)” የምስጥር ማኅበረሰብ ማለትም ሰይጣን አምላኪዎች የተመሠረተች ሀገር ነች። እውነተኞቹ የምድሪቱ ሰዎች እስከ አሁን ነጻነታቸው ለመቀዳጀት አሜሪካን ይፋለማሉ፤ ሆኖም ብዙ የመገናኛ ብዙሃን ሽፋን አያገኙም። ይህም ሆን ተብሎ የሚፈጸም የክፉዎች ድርጊት ነው። አሜሪካ፡ ዳግማዊት ባቢሎን ብለን መጥራት እንችላለን። ምክንያቱም፡ ጥንታዊትዋ ባቢሎን፡ ብዙ የጣዖት አምልኮት የነገሰባትና ዲያብሎስ ዓለም ለመቆጣጥር ሲጠቀምባት ነበር። አሁንም አሜሪካን እየተጠቀመ ነው።

የኢትዮጵያ የግዛት ወሰን በጣም ሰፊ ምድር ያካልል ነበር። ሆኖም በሴረኞች ምክንያት ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ገጽታ ለመያዝ ተገዳለች። ይህም ከ፲፻፱፮፯ ጀምሮ የማኅጸንዋ ልጆች የሆኑ በምግባራቸው ግን የምዕራባውያን አገልጋይ የሆኑ ሻዕብያና ወልደ  ሻዕብያ ህወሓት አስተዋጻቸው ከፍተኛ ነው። ይህም ለብዙ ሺ ዓመታት ሳትደፈር የኖረቺው ሀገር በቀላሉ በምዕራባውያን  ልትደፈር ችላለች። የምስጥር ማኅበርሰብ ዋነኛ ዓላማም የተዋህዶ ሃይማኖት መሠረትዋ ለሆነው ኢትዮጵያ በመቆጣጥር ለዲያብሎስ ማስገዛት ነው። ይህ ባለፉት ፶ ዓመታት ተሳክቶለታል። አይገርምም፦ ከተዋሕዶ ትግሬ መሪ ሙስሊም ኦሮሞ መሪ የተመረጠበት ግዜ ላይ ደርሰናል፤ ሆይሆይ የሚለውን ሰው ብዛት ስናይ፡ ለስላሳው ፀረ–ክርስቶስ ጨረቃዋን መጎተት ሲጀምር ምን ያህል ተከታይ እንደሚኖረው መገመት አያዳግተንም። የሚፈለገው ይህ ነው፤ አላማውም ያ ነው።

በኢትዮጵያ መሠረት ላይ ጥላቻ እንዲኖረው በማድረግ መሬት መንቀጥቀጥ መፍጠር መቻል፡ ነው አላማው። ዘረኝነት በኢትዮጵያ ለመዝራት ህወሓትን ተጠቅመዋል። በዚህም መልክ በተዋሕዶ ሃይማኖት አማኙ ህዝብ መካከል ልዩነትን ለመፍጠር ሙከራ ተደርጓል። ላለፉት ሺህ ዓመታት ጦርነቱ፣ ረሃቡና በሽታው ሁሉ ይከሰት የነበረው በወሎ ላሊበላ አካባቢ እና በትግራይ ነው። በዱሮ ጊዜ ጣዖት አምላኪዎችን (ራያ) ወደ ሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል አምጥተው አስፈሩ፤ በኋላ ላይ ደግሞ የደርግ መንግስት ትግርኛ ተናጋሪ ክርስቲያኖችን ከትግራይ በማፈናቀል በደቡቡ ኢትዮጵያ ለማስፈርና ትግራይን ከተዋሕዶ ለማጽዳት ሞክሯል። “Problem – Reaction – Solution” ብሎታል፡ ተንኮለኛው ፈላስፋ ሄገል። ልክ በአይሁዶች በኩል የእስራኤልን መሠረት ለመነቅነቅ እንደሚሞክሩት፡ አሁን በአገራችንም በትግሬዎች በኩል የኢትዮጵያን መሠረት ነቅንቀው ለማፍረስ እየታገሉ ነው። ይህ ቁልጭ ብሎ እየታየ ነው። የሄግል ፍልስፍና ዋነኛው የምስጥር ማኅበረሰብ ዲያብሎሳዊ መሣርያ ነው።

ወቅታዊ የኢትዮጵያ ሁኔታ የሚነግረንም ይህ ነው። ህዝባችን  ዐቢይ አሕመድ በመምጣቱ ለውጥ የሚመጣ መስሎት ተስፋ ይዟል። በእርግጥ ላለፉት ፳፯ ዓመታት ያለወንጀላቸው ብሔራቸው ብቻ መሰረት በማድረግ በማሰር ጥፍራቸው በጉጤት በመንቀልና ውሃ የሞላ ሃይላንድ በብልታቸው በማሰር እንዲመክኑ ሲደረጉ የነበሩ ብዙ ዜጎቻችን ነጻ እንዲወጡ ሲደረግ በማየቴ ለዓመታት ህሊናዬ ሲረብሸኝ የነበረ ነገር በመሆኑ አሁን ዕረፍት አግኝቻለው፤ ይህ ያደረገም እግዚአብሔር መሆኑ አምናለው።  ሆኖም የሄግልን ፍልስፍና ማስታወሱ ግድ ነው።
ባለፈው ቅዳሜ ለዐቢይ አሕመድ ድጋፍ በተጠራው ሰልፍ ፈንጅ በማፈንዳት የተከሰተው ነገር ተከትሎ ለማጣራት የሀገር አሜሪካ የምርመራ ድርጅት (FBI) እንዲመረምር መፈቀዱ እጂግ ይገርማል። ዐቢይ አሕመድ የህወሓትን የምዕራባውያን ሴራ አስፈጻሚነት እያስቀጠለ ለመሆኑ ግልጽ ሆኗል። ኤፍ.ቢ.አይ (FBI) እና ሲ.አይ.ኤ (CIA) የዓለምን ህዝብ የሰላም የነሱ ሰይጣናዊ ድርጅቶች እኛ ሀገር ላይ ሰላም ያመጣሉ ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው። ተዋህዶ መሰረትዋ በሆነ ሀገር ድንግል ማርያምን የካደ መሪ ኢትዮጵያን ይበጃል ብሎ ማሰብም የዋህነት ብቻ ነው ሊሆን የሚችለው። 

የአሜሪካ መንግስት በፀረ ሽብርተኝነት ድጋፍ ስም ጌታቸው አሰፋ ለሚመራው የደህንነት መስሪያ ቤት ከፍተኛ የሆነ እርዳታ ታደርግ ነበር። እርዳታው ከሰው ኃይል ስልጠና ጀምሮ እስከ ከፍተኛ የሆነ የስለላ መሳሪያዎችን መለገስን ይጨምራል። በቋሚነት ኢትዮጵያ ውስጥ የሚኖሩ አሜሪካዊያን የስለላ ሰዎች የደህንነት መስሪያ ቤት ውስጥ ላሉ counter terrorism division አባላት መረጃ በማቀበል፥የተገኘውን መረጃ በመተንተን፥ እንዲሁም ዘመናዊ መሳሪያዎችን አጠቃቀም በማሳየት ድጋፍ ያረጉ ነበር። counter terrorism division በዋናነት አላማው ከውጭ ሃገር የሚነሳን እስላማዊ ሽብርተኝነትን መዋጋት ነበር። የእስልምና አሸባሪዎች የምትፈጥራቸውና የምትደግፋቸው ራስዋ አሜሪካ ነች፤ ይህ ነው የአሜሪካ ሴራ!

ነገር ግን ጌታቸው አሰፋ[የድህንነት ቢሮ የቀድሞ አዛዥ] በይፋ ደረጃ ለፀረ ሽብር ቡድን የሚውሉ ድጋፎችን እና የሰው ኃይል ወደ ሃገር ውስጥ ደህንነት ስራ ላይ እንደ አስፈላጊነቱ እየመደበ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን፥ ጋዜጠኞችን፥ የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን ለመሰለል፥ለማስፈራራትና፥ለማፈን ይጠቀምባቸው ነበር።

ዛሬ የህወሓት የማኅበራዊ ትስስር ድረ ገጾች ሰዎች አሜሪካ መርማሪ ልትልክ ነው ሲባል የሚሰጉት ይህንን የረጅም ጊዜ ግንኙነት ስለሚያውቁና በነሱ እምነት ዛሬ አሜሪካ ከህወሓት ጎን አይደለችም ብለው ስለሚያስቡ ነው። አሜሪካ ጓዳችንን በደንብ ታውቃለች ከዚህ በፊት በሷ እርዳታ የኢትዮጵያን ህዝብ እንዴት እንደምናሸብር ስለምታውቅ በቶሎ ጉዳችን ሊገለጥ ነው የሚል ፍርሃት ነው። CIA ኮርማ ጫንቃችን ላይ ካወቅንና ከተረዳን የቆየ ቢሆንም እንዲሁ በግላጭ ያለምንም ሕፍረት ክብራችንን እንሸጣለን ብዬ ግን አልገመትኩም ነበር። "አያ ጅቦ ሳታማሀኝ ብላኝ"


አሜሪካ እንደ ሀገር ከተመሠረተች ጀምሮ ከ200 በላይ ጦርነቶች  አካሂዳለች። በተለያዩ ሀገራት ለሚፈጠሩ ነውጥና ጦርነቶች የ አሜሪካ ቀጥተኛና ተዘዋዋሪ አስተዋጽዖ አለበት።እንኳን የእኛን ባለሥልጣናት ቀርቶ በአገሮቻቸውም ያሉትን ፖለቲከኞችና ባለሥልጣናት የሚመርጡት እነዚህ “ስውር የሆኑት” ሉሲፈራውያን ናቸው። ሳያስቡትና ሳያቅዱት ሾልከው ሥልጣን ላይ በወጡት ፕሬዚደንት ትራምፕ ላይ ምን ዓይነት ጥቃት እየፈጸሙ እንደሆነ እያየን ነው።

ዶናልድ ትራምፕን ሌት ተቀን ሲሰልሏቸው የነበሩትና የተዋረዱት የብሔራዊ ምርመራው ጽሕፈት ቤት (ኤፍ.ቢ.አይ) ወኪሎች ባለፈው ቅዳሜ በአዲስ አበባ የፈነዳውን ቦምብ ጉዳይ ለመመርመር ወደ ኢትዮጵያ ተልከዋል። ምን አገባቸው፧ ሁሉም ንገር በደንብ ተዘጋጅቶ የተቀነባበረ ነው፡ ከበፊቱ የሚለየው በምንድን ነው፧ አዎ፦ አሁን ሁሉም ነገር በጣም ፈጣን ነው፤ ስለዚህ ነገሮችን አገናዝበን በግልጽ ለማየት እንችላለን። ይታየን እስኪ፤ ስልጣኑን ከያዙ ገና ሦስት ወር ያልሞላቸው ዶ፨ር አብይ የድጋፍ ሰልፍ እንዲያዘጋጁ ተነገራቸው። በዚህ ሰልፍ ላይ ቦምብ እንዲፈነዳ ተደረገ፤ ኤፍ ቢ አይ መርማሪዎችን ላከ፣ ያዘጋጇቸውን እና የመረጧቸውንም (ሙስሊም) ሰዎች ቁልፍ በሆኑ የሥልጣን ቦታዎች (ፖሊስ) ላይ እንዲያስቀምጡ ታዘዙ። የ ሄገል ዲያሌክቲክስ፦ (Problem – Reaction – Solution)።

በቀጠናው ኢትዮጵያ ብቻ ነች ክርስቲያን አገር ሁለተኛ ደግሞ ኢትዮጵያን ከቀይ ባህር ድርሻ ማስወጣት ይፈልጋሉ፤ ለዚም ህወሓት ቀንደኛ አስፈጻሚ ነበር ይህን ለምን ፈለጉ ሲባል ደግሞ መልሱ እነሱ የሚጠጡትን ውሃ ከኢትዮጵያ ያገኛሉ፡፡ ስለዚህ የኢትዮጵያን መዳከም ሱዳን፣ ግብጽ፣ ሶሪያ እና መላው አረብ ይፈልገዋል፡፡

እውነተኛው የኢትዮጵያ ትንሳዔ የሚረጋገጠው፡ ፳፬ ሰዓት፡ ወደ ፈጣሪ አንጋጠው ስለ ኢትዮጵያና እንዲሁም ለመላው የሰው ዘር ሓጥያት ምህረት በሚለምኑ ቅዱሳን ነው። እኛም በጸሎት እናግዛቸው፡ ጊዝያዊ በሆነው የፖለቲከኞች ድራማ ስሜታችን ሊሰረቅ አይገባም።

ኢትጵያዊነት  ታላቅ ክብር ነው!


ሰኔ 20, 2010 ዓ.ም.

No comments: