EAR

አዲስ ነገር

Sunday, 1 July 2018

“ዓውደ ነገሥት” መጽሐፍና የዶክተሮች የድጋፍ አስተያየት!






ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ

በቅርቡ፡ መረጃው የተሳሳተ ቢሆንም፡ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፡ የኢትዮጵያ ቤተመጽሐፍት እና ቤተመዛግብት ኤጀንሲ ዋና ዳይረክተር፡ ሆኖ  ተመርጧል የሚል  ዜና ተሰራጭቶ ነበር። ይህንን ተከትሎ ነበር፡ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፡ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ የሆነውን፡ የመምህር ግርማ ወንድሙ፡ የፈውስና የወንጌል አገልግሎት፡ ታዋቂነቱ በመጠቀም፡ በመቃወም የብዙ ጭፍን ተከታዮቹ መንገዱ ወደ መጥፎ ሁኔታ እየወሰደ ያለው።

የመምህር ግርማን ትምህርት ለሚከታተል ሰውዓውደ ነገሥት”* የተሰኝ የጥንቆላ መጽሐፍ የብዙ ሰዎች ህይወት እያመሰቃቀለ እንዳለ ለመረዳት አይከብደዉም። ታድያ ይህ መጽሐፍ፡ በኢትዮጵያ ቤተመጽሐፍት እና ቤተመዛግብት ኤጀንሲ፡ ውስጥ እንደቅርስና ውድሃብት ተቆጥሮ ክብር ተሰጥቶት ይገኛል። የኔ የፌስቡክ መልዕክቴም ይህንን ተከትሎ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፡ ይህንን የጥንቆላ መጽሐፍ እንዲያስወግድ ነበር የጠየኩት። በለጠፍኩት ጽሑፍም የተወሰኑ ሰዎች የራሳቸው አስተያየት የሰጡኝ ሲሆን ከነዚህ ውስጥም በመጽሐፉ ላይ፡ ጥናት አድርገናል የሚሉ ሁለት ዶክተሮች ነበሩ። ሌሎች አስተያየት ሰጪዎች መጽሐፉ የማያውቁት ሲሆን፡ በከፊል ደግሞ፡ በየዋህነት መጽሐፉ ቅርስ በመሆኑ ለምን ይጠፋል እንዲያዉም መንከባከብ አለብን፡ የሚል  አንድምታ ያለው አስተያየት ነበር የሰጡት። እነዚህ ሰዎች ክቡር የሰው ነፍስ ወደ ሲዖል የሚነዳ መጽሐፍ ቅርስ ነው በሚል የማይረባ ምክንያት መደገፋቸው አንደኛ አላዋቂነት ሲሆን ሁለተኛ ደግሞ አሳዛኝ ነው። ዶክተሮቹም ቢሆን ስለ ሰው ነፍስ ግድ አይሰጣቸዉም፡ አስገራሚው ነገር ስለ መጽሐፉ የሚያውቁ መሆናቸው ነው። ታድያ ይህ የዲያብሎስ የጥንቆላ መጽሐፍ ለምን ለመደገፍና ጠበቃ ሆነው ለመቅረብ ፈለጉ፧ የራሴን ምልከታ ላጋራቹ፦

ዶ/ር ማዕረግ ከአውሬው ምልክቶች አንዱ ነው፤ በክርስቲያናዊው የመንፈሳዊ ሕይወታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተጠምቀን የክርስትና ስም፡ ብሎም ቅብዓቅዱሱን ተቀብተን የሊቅነቱ ማዕረግ እንደሚሰጠን፡ በፀረክርስቶሱ ዓለምም እንዲሁ ዶክትሬቱን ለመቀበል የአውሬውን ቅባትበመቀባትእርሱ የፈጠረውን ሥርዓት ለማገልገል ቃል በመግባት ነው፤ ነፍስን በመሸጥ። በተለይ በውጭ አገራት ዶክትሬቱን የተቀበሉ ወገኖች ማዕረጉን ከተቀበሉ በኋላ ለለገሰቻቸው አገር እድሜ ልካቸውን ጠበቃ መቆም ወይም የአገሪቷን ፍላጎቶች የማሟላት ግዴታ አለባቸው። ባጠቃላይ፡ የባዕዳን መጠቀሚያ በመሆን ከሀገራቸው ጥቅሞች በተጻራሪ ይቆማሉ።

ለምሳሌ በእምነት በኩል ፕሮቴስታንቶች አሜሪካና አውሮፓ፣ ካቶሊኮች ለጣልያን፣ ሙስሊሞች ለሳዑዲ አረቢያ ሲሉ ከማንነታቸውና ከገዛ ሀገራቸው ጥቅም በተጻራሪ እንዲንቀሳቀሱ ሲደረጉ፤ በዶክትሬት የተካኑትም ወገኖች፡ ምዕራባውያኑዲሞክራሲ” “ኒዖ ሊበራሊዝም፣ ወይምሊበራል ዲሞክራሲለሚሉት የማታለያ ርዕዮተ ዓለም እንዲታገሉ ይገደዳሉ።

በዶክተሮች ላይ ትኩረት ሰጥቼ መጻፌ በምክንያት ነው። ምክንያቱም የዋሁ ህዝባችን የመንፈሥ ውግያው ሳይረዳተምረዋል ተመራምረዋል” በሚል ምክንያት የነገሩት ሁሉም ነገር ያለጥያቄና አስተያየት የመቀበል ዕድሉ በጣም ሰፊ ስለሆነ ነው።ጌታችን መድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ያስተማረን “ዂሉን ፈትኑ መልካሙንም ያዙ” የሚለው ቅዱስ ቃል  ተግባራዊ ልናደርገው ይገባል። ቅድሱ ከርኩሱ ለመለየት ይጠቅመናል።

*እስራኤላውያን በባቢሎን ምርኮ ጊዜ፡ ከባቢሎናውያን የተማሩትና የወሰዱት የጥንቆላ መጽሐፍ ነው። በምዕራባውያኑ ህዝቦች “ሆሮስኮፕ” በሚል ይታወቃል። ይህ መጽሐፍ የንግሥተ ማክዳ (የሳባውያን ንግሥት)ና የእስራኤሉ ንጉሥ ሰሎሞን ልጅ ቀዳማዊ ምኒሊክ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ አብረውት ከመጡት በእስራኤላውያን የክህነት ሥልጣን ካላቸው ሌዋውያን ጋር ይዞውት ወደ አክሱም ያመጡት ነው።

ዓርብ ሰኔ 22, 2010 ዓ.ም.

No comments: