EAR

አዲስ ነገር

Thursday, 29 November 2018

የትግራይ ህዝብ ሰልፍ ስለወጣ ሊፈረድበት አይገባም !


ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ


የትግራይ ተወላጅ እንደ መሆኔ መጠን ኅወሓትና የትግራይ ህዝብ አንድ ነው ማለት አይቻልም ! ምክንያቱም ኅወሓት የኢትዮጵያ ጠላት ሲሆን ትግራዋይ ግን ለኢትዮጵያ አንድነት አንገቱን የሰጠ የጀግናው ኢትዮጵያዊ ንጉሠ ነገሥት ዮሐንስ ፬ኛ ልጆች ነን።

የዐምሓራም ህዝብ ፣ የኦሮሞም ህዝብ ሌላውም ሁሉ ለወያኔ ሲሰለፍና ለመለስ የሀዘን ልብስ እየለበሰ ሲያስመስል እንደነበር ማስታወሥ ግድ ይለናል፡።

ስለ ፖለቲካ መፃፋ የማይመለከተኝና የምጠየፈው  ቢሆንም የሀገራችን ፖለቲካ በዋናነት ኅወሓት  መከፋፈሉን እና ዘረኝነቱን ዓላማቸው አድርገው በሚንቀሳቅሱት ሰላቢ እጆቾ ምዕራባውያን  ስለባ ስለሆነች አንዳንዴም ይህንን ለመቃወም ኢትዮጵያዊነቴ ስለሚያስገድደኝ እፅፋለው።  

የትግራይ ህዝብ ወያኔዎች ከመላ ሀገሪቱ ተሰባስበው የተጫኑትና በአሁኑ ወቅት ከማንም በላይ በአፈና ያለ ህዝብ ነው ፤ ስለዚህ በዚህ ወቅት ምንም ቢያደርግ ልንፈርድበት አይገባም ከወያኔዎች አላቀን ነጻነት እንስጠውና ያኔ በሚያሳየው አቋም እንመዝነዋለን ፡፡ አባታችን አቡነ አብርሀም የመስቀል በዓል ባህር ዳር ላይ ሲከበር " ህዝብ አይሳሳትም " ብለው ነበር ፡፡ አሁንም የትግራይ ህዝብ አይሳሳትም ሌባም ቢሆን ተደብቆ ይሰርቃል እንጅ በአደባባይ ስለ ሌብነት መልካምነት አይሰብክም ፡፡ ስለዚህ አይደለም በኢትዮጵያ በመላው ዓለም የተወገዙ ተግባሮችን የትግራይ ህዝብ ደገፈ ማለት ችግር አለ ማለት ነው ፡፡ ምክንያቱም ቢያንስ ሰው ናቸውና፤ ሰው ደግሞ በምንም መልኩ ሙሉ በሙሉ እንዲህ ህሊና ቢስ አይሆንም። ስለዚህ እነዚህ ሰዎች አንድ ከአቅማቸው በላይ የሆነ ነገር አስገድዷቸዋል ማለት ነው ፡፡ ይህን መረዳት ደግሞ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን አዲሳችን አይደለም ምክንያቱም ሁሉም ብሄር በጭቆና እና በአፈና  በነበረበት ሰዓት ከአንዴም ሁለት ሦስቴ ለማይደግፈው አላማና አቋም ከልቡ በሚመስል መልኩ መሬትን ያንቀጠቀጠ ሰልፍ አድርጓልና።

እስኪ ሁላችሁም የመለስን ሞት አስታውሱ!

ይህ ሰው ሰይጣንን በግብር የሚበልጠውና ብዙዎችን እንዲህ በሰይጣን አምሳል እንዲንቀሳቀሱ የቀረጸ ፤ ብዙዎችን ያለርህራሄ በማስገደል እና በመግደል ሁሉም የሚያውቀው ወደ ሰይጣንነት የተቀየረ አውሬ ነበረ ፤ ነገር ግን የሱን መሞት በሰላማዊ ሰልፍ እንዲያከብር እና እንዲያዝን በታዘዘ ጊዜ ብዙዎች ለሳምንታት እና ለወራት መሬት አንቀጥቅጥ ሰልፍ እና ሀዘን አድርገዋል ፣ የሀዘን ልብስ እያሰፉ ለብሰዋል ፣ ፀጉራቸው ነጭተዋል ፣ ድንኳን ጥለው ካለልክ አሽቃብጠዋል ፡፡

እና ዛሬ የትግራይ ህዝብ ሌላውን እንዲህ ሲያስደርጉ የነበሩ ሰዎች ተጠቃለው አፍነውታው እንዲህ ቢያደርጉ ለምን ይፈረድበታል ፤ ባይሆን እንደ ሌላው እንቢ አሻፈረኝ እያሉ እራሳቸውን መስዋት እያደረጉ ለቀሪው የነጻነት ፋና የሚቀዱ ግን ጎን ለጎን ማቆጥቆጥ አለባቸው እላለው ፡፡ በትግራዋይ ለ፵ ዓመታት የተሰራው ሴራና ህፅበተ ህልዮት (brainwash) በቀላሉ ለማስወገድ ተአምራዊ የእግዚአብሔር ኃይል ያስፈልጋል።

ኢትዮጵያዊነት ታላቅ ክብር ነው!

No comments: