ዘርአዳዊት ዘ፡ኢትዮጵያ
የሰው ልጅ ፡ የህይወት ጉዞ ፡ የተለያዩ ገጽታዎች የተላበሰ ነው ። ይህንን እንዲሆን ከሚያደርጉት ነገሮች ፡ ከሌሎች ሰዎች ጋር የሚኖረው ግንኝነትና መስተጋብር ነው ። እኔም ፡ እንደ አንድ ሰው ፡ የተለያዩ ሰዎች በተለያዩ አጋጣሚዎች ያወኩኝና የቀረብኩኝ ሲሆን ፡ በባህሪና በአስተሳሰብ መለክያ ሚዛን ስመዝናቸው በተለይ ባለፉት ፲፬ ዓመታት የዓለም ዓቀፍ የግንኝነት መረብ ፡ መጠቀም ከጀመርኩበት ጊዜ በ ፭ ምድብ እከፍላቸዋለው ። ዝርዝሩ እንደሚከተለው ነው ፦
፩. እውነት ፈላጊዎች ፦
እነዚህ ሰዎች የነቁ ናቸው ፡ በዓለማችን ዙርያ ፡ ምን እየተካሔደ እንደሆነ ጠንቅቀው ያውቃሉ ። እውነታው ብግልጽ ማየት ይችላሉ ። እውነታው አውቀው ዝም አይሉም ፡ ሌሎችን ለማሳወቅና ለማንቃት በተለያየ መንገድ ይሰራሉ ። ሙሉው የህይወታቸው ጊዜ ሌሎችን ለማንቃት ሊጠቀሙበት ይችላሉ ። በ አብዛኛው እነዚክ ሰዎች ከዓለም የተገለሉ ናቸው ፡ ብቸኝነትን ያዘወትራሉ ።
ያወቁትንና የነቁበት ጉዳይ ላይ ለቤተሰቦቻቸውና ጓደኞቻቸው ለመንገር አይደፍሩም ፡ ምክን ያቱም የሚያቀርቡት ጉዳይ ከባድና ያልተለመደ በመሆኑ ቤተሰቦቻቸውና ጓደኞቻቸው እንደ ዕብድ ሊቆጠሩ እንደሚችሉ ስለሚያስቡ ነው ። ቤተሰቦቻቸውና ጓደኞቻቸው ማጣት ደግሞ ቀጣይ ሂወታቸው ከባድ ሊያደርገው ይችላል ። ይህ ቢሆንም እነዚክ ሰዎች እውነቱን ለመንገርና ለማንቃጥ ቆራጥና ደፋር ናቸው ።
፪. የተሳሳቱ ወገኖች ፦
እነዚክ ፡ እስካሁን ድረስ ፡ እንቅልፍ የጣላቸው ሰዎች ናቸው ። ዓለም ውስጥ የተሳሳተ ነገር እንዳለ አያምኑም ። ስጋዊ መንግስታቸው የሚነግራቸው ሁሉ ያለ ምንም መጠራጠርና መወላወል ይቀበላሉ ። በዓለም ላይ በየቀኑ አስገራሚ ነገሮችን ይመለከታሉ ያደምጣሉ ፣ ነገር ግን በዓይናቸው ያዩትን እንኳን በመካድ መገናኛ ብዙሃን የሚነግርዋቸውን ያምናሉ ።
ህይወታቸው ለመምራት በየቀኑ የሚፍጨረጨሩ ናቸው ። ልጆቻቸው ለማሳደግ ፡ በየቀኑ ለብዙ ስዓታት በስራ ይወጠራሉ ። በዚክ ምክን ያት እውነት ለመመርመርና ለመረዳት ራሳቸው አያዘጋጁም ። ልጆቻቸው ያስከትባሉ ፣ የዘረመል ልውጥ የተደረገባቸው ምግቦች ልጆቻቸውን ይመግባሉ ።
በአካባቢያቸው ምን እየተደረገ እንዳለ ማየትና መገንዘብ አይችሉም ። መንግስታዊ ሥርዓት ላይ ሙሉ በሙሉ ተስፋ ይጥላሉ ። የመንግስታት ጉድለት በግልጽ እያዩ እንኳን አሁንም ቢሆን በእሱ ላይ ያምናሉ ። አንዳንድ ጊዜ እውነትን በአንድ ሁኔታ ውስጥ ማየት ይችላሉ፣ ግን ነጥቦቹን አያገናኙም እና የተሟላውን ምስል ማየት አይችሉም ። እነዚህ ሰዎች የእኛን እርዳታ እና ድጋፍ ይፈልጋሉ ፣ አንድ ቀን ሊነቁ ይችላሉ ። ሁላችንም እንደዚህ ነበርንና ።
፫. የህጽበተ ህልዮት ሰለባዎች ፦
የስጋዊና ሰይጣናዊ መንግሥታት ፡ የጨለማ ስራ ፡ ባለማወቅና በተሰራባቸው አዕምሮ የማደንዘዝ ሴራ የሚደግፉና ተግባራዊ ለማድረግ የሚሰሩ ናቸው ። በተለያዩ የመንግስት መዋቅሮች ፡ አባል በመሆን ፡ ይንቀሳቀሳሉ ።
በጤናው ዘርፍ ያሉ ሰዎች ፡ ልጆች እንዲከተቡ በመስበክ ፡ የጨለማ ሠራዊቶች ሴራ ያስፈጽማሉ ። እነሱም የእኛ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ።
፬. ነፍሳቸው የሸጡ ሰዎች ፦
በጨለማው የተታለሉ ሰዎች አሉ ፣ በአንድ መንገድ ወይም በሌላ መንገድ ወደ ጨለማው ጎዳና ገብተዋል ። ጥቂቶቹ ተገድለዋል ፣ አንዳንዶቹ ዝናና ሃብት አግኝተዋል ። ሌሎች ደግሞ ከፍተኛ ኃይል ተሰጥቷቸዋል ። ነፍሳቸው ለጨለማው ገዢ አሳልፈው ሰጥተዋል፣ ሰይጣናዊ መንገድ መርጠዋል ።
፭. ስልጣን የተጠሙ ሰዎች ፦
ዓለማችን በሴራቸው ባገኙት ስልጣን በአብዛኛው የተቆጣጠሩት ናቸው ። ስልጣናቸውና ሃይላቸው ከትውልድ ወደ ትውልድ ለዘመናት ሲተላለፍ እዚክ ደርሷል ። አብዛኛውን የሰው ልጅ ጥቅም አልባ እንደሆነ አድርገው ይቆጥሩታል ። በሚያሳዝን ሁኔታ እነሱ በሚችሉት በማንኛውም መንገድ ወደሚፈልጉት ሰይጣናዊ መንገድ እየወሰዱን ነው ። ለሰው ልጆች አዘኔታ ወይም ርህራሄ የላቸውም ።
No comments:
Post a Comment