✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
የሀገራችን ኢትዮጵያ ገዢ ቡድን የሆነው ኢሕአዴግ እንደ አሜባ ራሱን በማባዛት ወደ ብልፅግና እና ህወሓት ከተከፋፈለ በኋላ ልዮነታቸው መፍታት ባለመቻላቸው የኢትዮጵያን ህዝብ ለመከራ ዳርገውታል ። ላለፉት ፲ ወራት በህወሓት እና ብልፅግና ቡድኖች መካከል እየተደረገ ያለው ጦርነት የብዙ ንጽኃን ኢትዮጵያን ሕይወት ቀጥፎ ብዙዎችን ደግሞ ለከፋ መከራና ስቃይ ዳርጎናል ።
ይህ በወንድማማቾች መካከል እየተደረገ ያለው ጦርነት በፖለቲከኞች ሴራና ብሔርተኝነት የተመረዙ የዘመኑ ሰዎች በሁለት ጎራ ተከፍሎ ሲደግፍና ሲያበረታታ ማየት ደግሞ ይበልጥ ያሳዝናል ። ይህ ሁነት የ 50 ዓመታት የጨለምተኝነት የምዕራባውያን ብሔርተኝነት ስብከትና ፍደሣ (propoganda) ውጤት መሆኑ ሊታወቅ ይገባል።
ይህ ጦርነት በኢትዮጵያዊነት ለፈፀምነው ክሕደት ቅጣትና ማስተማርያ የተላከብን ቢሆንም አሁንም ከስሕተታችን ከመማር በክሕደታችን ቀጥለናል ። ጦርነት ማለት የማይተዋወቁ ሰዎች በስልጣን ላይ ላሉ የሚተዋወቁ ሰዎች ጥቅም ሲባል እርሰበርስ የሚጨፋጨፉበት ድርጊት ነው ።
ህወሓት ላለፉት 8 ወራት መቐለ ከተማን ለቃ በተንቤን በረኻ ቆይታ ከተመለሰች በኃላ ከደረገቻቸው ነገሮች አንድ በመንግሥት መሥርያ ቤቶች የሚገኙ ሰራተኞች እርሰ በርስ በጦርነቱ ዙርያ ግምገማና ግለሂስ እንዲያደርጉ ማስገደድ ነበር። ይህ ባሕሪ ለ46 ለዓመታት መንግሥት እና ድርጅት (party) በኃይል ልዮነት ሳይደረግ ስራ ላይ መዋሉ ነው ። ይህንን ትክክል ያልሆነ አሰራር የሚቃወም ሰራተኛ አለመኖሩ ደግሞ ነገሩን አስደንጋጭ ያደርገዋል።
እኔ በምሰራበት የመንግሥት ፅሕፈት ቤት በተደረገ ግምገማ ስላልተገኝሁ ግምገማው አንድ ቀን ሲቀረው ነበር ወደ ቤቴ ሰው ተልኮ ወደ ፅሕፈት ቤት እንድመጣ የተደረገው ። ግለሂስና ግምገማ ወደ ሚደረግበት ስፍራ ከደረስኩኝ በኃላ ነገሮች ለመረዳት ብዙም አልከበደኝም ። በተለያዩ ጊዜያት ፊትለፊት እና በተለያዩ መገናኛ አውታሮች ኢትዮጵያዊነት የሚሰብኩ ህወሓትን የሚቃወሙ አመለካከቶቼና ፅሑፎቼ መሞገት ያልቻሉ ፣ በመገናኛ ብዙኅን ተደጋጋሚ የብሔርተኝነት ስብከት አዕምሮአቸው በቁጥጥር ሥር የዋለ የሥራ ባልደረቦቼ እኔን ለመበቀል እና አንገት ለማስደፋት ምቹ ጊዜ ይጠብቁ ሆሯል ለካ በየተራ በጥያቄ ያዋክቡኝ ጀመር። በዚህ ወቅት ህወሓት "ኢትዮጵያን ለማፍረስ ሲዖል ድረስም ቢሆን እገባለሁ!" በማለት የተወሰኑ የኢትዮጵያ መሬቶች በቁጥጥር ሥር ያዋለችበት ጊዜ ነው ። በዚህ ምክንያትም የህወሓት ካድሬዎች እና ደጋፊዎች በከፍተኛ ደስታና ስካር ላይ ናቸው ።
የሚያስገርመው ነገር እነዚህ ወጣት የሥራ ባልደረቦች ካቀረቡልኝ ብዙ ጥያቄዎች መካከል "ጦርነቱ ትደግፋዋለህ ወይ" የሚል ነበር ።
እነዚህ ምስኪን ባልደረቦቼ ያልገባቸው ነገር ይህ በአንድ ድርጅት (ኢሕአዴግ ) የነበሩ ግለሰቦች በሥልጣን ልዮነት ምክንያት የተጀመረው ጦርነት በወንድማማቾች ሞት ስቃይ እንጂ በአሸናፊነት የሚያልቅ አይደለም ። የዚህ ጥያቄ ምላሽ ፈጣሪ በዓይናቸው እንዲያሣያቸው ጸሎቴ ነው።
የስጋ ማንነትና ምንነት የነበራትና ላለፉት ፻/100 ዓመታት ተዋርዳ ስትኖር የነበረችዋ ደካማዋ ኢትዮጵያ ጥቅምት 24 በህወሓትና በግራኝ ዐቢይ አሕመድ ሴራ በተከፈተው ጦርነት ሳቢያና አክትሞላታል። አሁን ለአዲሲቷ መንፈሳዊት ኢትዮጵያ እንትጋ። ውጊያው መንፈሳዊ ነው!
ጳጉሜ 3 ቀን ፣ 2013 ዓ/ም
No comments:
Post a Comment