EAR

አዲስ ነገር

Thursday, 14 September 2023

ይድረስ ለ "ውድብ ብሔረ አግአዚ" መንፈሳዊውን ዓይናችሁን ግለጡ!


✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ 

በቅድሚያ የኔ ጽሑፍ በመጽሔታቹ ታትሞ እንዲወጣ ስለአደረጋቹ እግዚአብሔር ይሥጥልኝ ። ለጥንታዊው የኢትዮጵያ እውነተኛ ማንነት ጥብቅና ስለምትቆሙም አድናቆቴን መግለጽ እፈልጋለሁ ።

ወንድሞች ዶ/ር አረጋዊ መብራህቱ ፣ ‘ኢዛና‘ + ኢንጂነር መርሻ፤ የህወሓትንና ጋላ–ኦሮሞን ሤራ በሚመለከት የያዛችሁትን አቋም በሚመለከት ሙሉ በሙሉ ከእናንተ ጋር ብስማማም፤ በሌላ በኩል ግን አውቃችሁም ሆነ ሳታውቁት አክሱም ኢትዮጵያውያንን በአውራጃ እና ወረዳ እየከፋፈላችሁ ተገቢና አስፈላጊ ያልሆኑ መልዕክቶችን ለማስተላለፍ መሞከራችሁ ግን ትልቅ ስህተት፣ ከባድ ወንጀል ነውና ከዚህ ሉሲፈራውያኑ ይተገበር ዘንድ ከሚመኙት ሤራና ተልዕኮ ብትቆጠቡ በጣም ጥሩ ነው።

ሉሲፈራውያኑና ሮማውያኑን ኤዶማውያንን ለብዙ ዘመናት እየታገለ ለኢትዮጵያ መጽናት ከማንም የብሔረ አግዓዚ አካባቢ የበለጠ አስተዋጽኦ ያበረከተውን ጀግናውን የዓድዋን/አክሱምን አካባቢ ሕዝብ ከከሐዲዎቹ ህወሓቶች ጋር አያይዛችሁ በመጥራትና ነጮቹ ወራሪዎች የሚጸየፉትን የዓድዋን እና አክሱምን ስም በማጠልሸት ላይ ናችሁና፤ “ዋ! ተጠንቀቁ! ትልቁን ምስል ተመልከቱ፣ መንፈሳዊውን ዓይናችሁን ግለጡ! የጠላቶቻችንን የምዕራባውያኑ ኤዶማውያንን እና የምስራቃውያኑን የእስማዔላውያኑን ሤራ አታራምዱ!” እላለሁ። አሊያ ግን እናንተም የሉሲፈራውያኑ ወኪሎች ናችሁና እንደሌሎቹ ተመሳሳይ ፍርድ ይሰጣችኋል።

ብሩክ ዓዲስ ዓመት!!

No comments: