EAR

አዲስ ነገር

Tuesday, 23 April 2024

በዘመናችን ከተሰሩ ትልቅ ሴራዎች አንዱ ሰዎች ልጅ እንዳይወልዱ ማድረግ ነው።

✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ 

ልጆችን እንደ ሸክም፣ እንደ ችግር፣ አድርጎ የማየት ነገር በወጣቱ ላይ በብዛት ይታያል። አንዳንዶች ደግሞ መልካም ያሰቡ መስሏቸው ይሁን ወይም መልካም ያሰቡ መምሰል ፈልገው አይታወቅም ግን ልጆች ተወልደው ምን ይበላሉ በዚህ ኢኮኖሚ እንዴት ይኖራሉ እንዴት ያድጋሉ ወዘተ ይላሉ። ድሮ ሰው ብዙ ሀብት ሳይኖረው እንኳ ብዙ ልጅ ወልዶ አሳድጎ ለትልቅ ደረጃ ያደርሳል። አሁን ብዙ ገንዘብ እያለው ድሮ ከነበረው በላይ እጅግ የተሻለ ምግብ፣ ልብስ፣ ትምህርት ጭምር መስጠት እየተቻለ ሰው ግን ልጅ የሚባል ማሰብ አይፈልግም። አብዛኛው ሰው እንደውም ማግባት ሁሉ አይፈልግም። አለመፈለጉን ደግሞ እንደ አዋቂነት፣ እንደ እርድና ይቆጥረዋል።

የሚገርመው ይህንን የሚያስቡት በብዛት ከአርባ እና ሰላሳ ዓመት በታች ያሉ ሰዎች መሆናቸው ነው። ማግባትና መውለድ ጥቅም ይኑረው አይኑረውኮ የምታውቀው አሁን ካለህ እድሜ በላይ ሃያ እና ሰላሳ ዓመት ስትኖር ነው። አሁን ላይ ምኑንም አታውቀውም። አይ ደግሞ ውጤቱ መጥፎ ከሆነስ ብለህ የምታስብ ከሆነ ደግሞ ከዚህ በፊት የኖሩ ሰዎች ምን አጡበት? አብዛኞቹ፣ ሁሉም ማለት ይቻላል ሙሉ እድሜያቸውን አብረው ኖረው ያለፉ ናቸው። ይህን ሲያደርጉ ደስተኛ የሆኑ አይመስላችሁም? ሰው በአጋሩ ደስተኛ ካልሆነ እድሜ ልክ አብሮ ይኖራል? በአንዱ ልጅ ካልተደሰተ ሶስት አራት ይደግማል?

የኛ ትውልድ ዘመናዊነት በሚል ስም የተሰጠውን የሐሰት ትምህርት እንደ እውነት ቆጥሮ ወደ መጥፎ አቅጣጫ እየተጓዘ ነው። የዚህ ውጤቱ ደግሞ ምን ይመስላችኋል? ደስታ ማጣት፣ በብቸኝነት መሞት። ግብረሰዶማዊነት ሁሉ። 

በዓለም የመጀመሪያዋ ፌሚኒስት ባል የላትም ነበር። አሟሟቷ ግን በጣም ያሳዝናል። በስልሳ ዓመቷ ብቻዋን ኖራ ነው የሞተችው። ከሞተች በኋላ ለተወሰኑ ቀናት ሞቷ አልታወቀም ነበር። የታወቀው አስከሬኗ ስለሸተተ ሰዎች ግራ ገብቷቸው ሊያዩ ወደ ቤቷ ሲገቡ ነው እንደሞተች ያወቁት። 

አላገባም አልወልድም የሚሉ ሰዎች በምዕራቡ ዓለም በዝተዋል። ብዙዎቹ በልቅ ወሲብ ለረጅም ጊዜ ስለሚሳተፉ የተለያዩ በወሲብ የሚተላለፉ በሽታዎችን ይሸምታሉ። syphilis, herpes, chlymedia, HIV ወዘተ። በዚህም ምክንያት እድሜያቸው ከአርባዎቹና ሀምሳዎቹ የማያልፍ ብዙዎች ናቸው። ይህ ነው እንግዲህ አጉል አወቅኩ ሰለጠንኩ ብሎ የማሰብ ጦሱ።

No comments: