EAR

አዲስ ነገር

Tuesday, 10 February 2026

ለዓመታት እውነትን በመያዝ የሉሲፈራዊያንን የጥፋት ዕቅድና ተግባር በተለያዮ መንገዶች ሳጋልጥ እንደ ዕብድ ተቆጥሬአለሁ


✍ ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ

ለዓመታት እውነትን በመያዝ የሉሲፈራዊያንን የጥፋት ዕቅድና ተግባር በተለያዮ መንገዶች ሳጋልጥ እንደ ዕብድ ተቆጥሬአለሁ፣ ተሰድቤአለሁ ፣ ከሰዎች እንድገለል ተደርጌአለሁ በአጠቃላይ በሕይወቴ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ደርሶብኛል አሁንም እየደረሰኝ ነው። እግዚአብሔር ይመሥገን አሁን ግን በአንጻራዊ ደረጃ ብዙ ሰው እውነታው እያወቀ፣ እየተረዳና እየገባው ነው።

የማቀርባቸው መረጃዎችና ማስረጃዎች "የሴራ ትንተና ንድፈ ሓሳቦች/Conspiracy Theory" እንጂ እውነታ አይደሉም ተብለው ብዙ ጊዜ ተተችተዋል። የጄፍሪ ኤፕሽተይን ሰነዶች ይፋ ከተደረጉ በኋላ ግን እውነታው ገሃድ ስለወጣ ማስተባበልና መቃወም የማይቻልበት ሁኔታ ተፈጥሯል።

የ "Conspiracy Theory" ዘመን አልፏል። ዓለም የምትመራው ህጻናትን በሚደፍሩ እና ለሰይጣን ግብር በሚያደርጉ፣ የሰው ልጅ ስጋን በሚበሉ እና ደም በሚጠጡ የሉሲፈር አገልጋይ ሰዎች ወይም ቡድኖች መሆኑ እያወቀ መጥቷል።

❝እውነት ስናገር የዚህ ዓለም ሰዎች ይጠሉኛል። ሐሰት እንዳልናገር ደግሞ ፍርድህ ያስፈራኛል። ከዚህ ሁሉ ግን ዝም ማለት ይሻለኛል።❞  --- ቅድስ ይስሐቅ

በመጨረሻም፣ ፍትሕ ምንም ይሁን ምን ያሸንፋል። በዚህ ዓለም ባይሆን በመጨረሻው ዓለም። ለዚህም እኮ ነው የፍርድ ቀን ያለን።

❖[የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፪፥፪፡፫ ]❖

“ነገር ግን የማይገለጥ የተከደነ፥ የማይታወቅም የተሰወረ ምንም የለም። ስለዚህ በጨለማ የምትናገሩት ሁሉ በብርሃን ይሰማል፥ በእልፍኝም ውስጥ በጆሮ የምትናገሩት በሰገነት ላይ ይሰበካል።”

No comments: