EAR

አዲስ ነገር

Thursday, 5 February 2026

⚠️ የፕሮቴስታንት እንቅስቃሴ መጨረሻ


ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ

በቅድሚያ ይህ ጽሑፍ በፕሮቴስታንት እምነት ክሽፈት ለመደሰት ያልተጻፈ መሆኑን እገልጻለው። የተጻፈው ስሜታዊነትና የእውነት ፍርሃት የሌላቸው ሰዎች አንብበው እንዲያስቡበት ነው። 

ለምዕራቡ ዓለም የግብረገብ መላሸቅ፣ ምእመናን ከአምልኮ ደጃፋቸው ሳር እንዲግጡ መሆናቸው፣ ምዕመናን እርቃናቸውን እንዲያመልኩ ወይም በሌላ ጊዜ የውስጥ ሱሪያቸውንና ጡት መያዣቸውን አውልቀው እንዲያመልኩ ሲነገራቸው ማድረጋቸው፣ ይባስ ብሎ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ከሚጋጩት እንስት ቀሳውስት እስከ ግብረ ሰዶማውያን ጋብቻ “ባርከው” መፈጸማቸው ስናይ ለመሆኑ ለዚህ ያበቃቸውን ነገር መጠየቃችን አይቀሬ ነው። 

የሃይማኖት መጻህፍት የስነ ጥበብ፣ ፍልስፍናና ስነ ልቦና ሙያ ጋር በመጨባበጥ ምእመናን ከመንፈሳዊ ልዕልናቸው ይልቅ ምድራዊ ቂልነታቸውን የሚያባብሉበት ማስደሰቻ የሆነበትን ሃይማኖት እናውቀዋለን። 

ለነዚህ ሁሉ መንገድ የሳቱ፣ ግራ የሚያጋቡ መንገዶች በር የከፈተው ሃይማኖት ፕሮቴስታንት ይባላል። ፕሮቴስታንት እምነት ይህን እንዴት ሊያደርግ እንደቻለ አንኳር እሳቤዎቹና ድርጊቶቹን ተመልክተን መረዳት እንችላለን። 

የመጀመርያው መጥፊያ መንገዱ መጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚ፣ አስተማሪ ሊቅ አያስፈልገውም ሁሉም አንብቦ መረዳት ይችላል፣ ፈጣሪ ይገልጽለታል ማለታቸው ነው፤ ይህም እርስ በእርስ እየተከፋፈሉ፣ ተለያይተው፣ ተለያይተው ዛሬ ላይ ለአንድ ሰው አንድ ቤተ ክርስቲያን እስኪሆን ድረስ በየሰፈሩ መሰብሰብያ እያቋቋሙ ነው። ሃይማኖት እንደጸጉር ይበዛል የተባለው ትንቢት እንዲህ ኖሯል መምጫው?

ሁለተኛ ይህ አመለካከት ግለሰቡን ከማንኛውም ስርዓት ውጭ እንዲሆን፣ እረኛ እንዳይኖረው፣ ፈጣሪ በምድር ያስቀመጣቸው ሐዋርያትን ትምህርት ወርሰው የቀደመችው መንገድ ሳትበረዝ እንድትቆይ የሚያደርጉ አባቶች እንዲለያይ በማድረግ ግለሰቡን የሃይማኖት ስርዓት አልበኛ እንዲሆን፣ ኮምፓሱ የጠፋበት መርከበኛ እንዲሆን አድርጎታል። ይህም ግለሰቡ መንፈስ ገለጠልኝ እያለ ምእመናኑ በመጀመሪያ የተቀመጠ ቀይ መስመር ከሚጠበቁ ይልቅ የ “ፓስተራቸው” ሙድ እስረኞች አድርጓዋል። ለዚህም ነው ሳር ጋጡ፣ ጡት መያዣ አውልቁ፣ እርቃን ሁኑ፣ ግብረሰዶም አጋቡ የሚሉ ጋጠ ወጥ ድርጊቶች ተከታይ የሆኑት። ስርዓት! ስርዓት! ስርዓት! ያስፈልጋል!

ሦስተኛው ከዚህ አቅጣጫ መጣፋት ጋር በሚፈጠረው ባዶነት ስሜት ለማካካስ ሰብሰብ እያሉ የስነ ልቦና ባዶነታቸውን የሚጠጋገኑበት መድረክ ይፈጥራሉ። ወደ መዝናኛ ቦታዎች ጊታር ተሸክሞ መሄድ፣ “ሲነጋ ከእንቅልፍህ ተነሳ” የሚሉ የስነ ልቦና መጻህፍት “ፓስተሮቻቸው” መሞነጫጨር ወዘተ. ተከትለው ይመጣሉ።

ከሁሉ የከፋው ግን ይህ ማስመሰል፣ ይህ ግብዝነት ልኩን ያለፈበት ሰው በቃኝ ብሎ ከፈጣሪው ተቆራርጦ ኢ-አማኝ ቀስ ብሎ ደግሞ መንፈሱ ስለማያስቀምጠው ሰይጣን አምላኪ እስከ መሆን ሊደርስ ይችላል።

ለዚህ ነው ፕሮቴስታንቶች ምእመኖቻቸውን በመንፈሳዊ ምግብ ማጥገብ ስለማይችሉና ራሳቸውም ረሃብተኛ ስለሆኑ የሌሎች ሃይማኖቶችን በመልከፍ የሚታወቁት። ሰውን ወደ ፕሮቴስታንት የማስቀየር ከፍተኛ ጥማት ያላቸው ባዶነታቸውን ለማምለጥ፣ ከፈጣሪ ጋር ይበልጥ ግንኙነት ለማግኘት፣ በመንፈስ ለመጥገብ ሌላውን “ጌታን ተቀበል” በማለት እረፍት ይነሳሉ። 

የዘመናዊው ዓለም ቁሳዊነት፣ ብኩንነት፣ ጽንፈኝነት ሚስጥሩ ይህ ነው። መንግስታትም የፕሮቴስታንት እምነትን የሚወዱት ለዚህ ነው። የሚስጥር ማህበራቱም ቢሆኑ የሰው ዘርን ኮምፓስ በማጥፋት፣ በጽፈኝነት በማሰለፍና በማጋጨት፣ በመጨረሻም አብዝሃውን የሰው ዘርን በሃይማኖት ተስፋ እንዲቆርጥ በማድረግ ኢ-አማኝ ካደረጉ በኋላ፣ ይህም የቀረውን ሃይማኖት ለማጥፋት ከተጠቀሙበት በኋላ ኢ-አማኝነት እራሱ የሚፈጥረውን ግጭት ተከትሎ በሚታየው አሰቃቂ ግፍ ሲከሽፍ፣ የዛኔ የሉሲፈር ዶክትሪን ታውጆ አውሬው ይነግሳል።

በዚህ ሳምንትም የኢትዮጵያ መሠረተ ክርስቶስ 'ቤተክርስቲያን' ግብረሰዶማዊነት የሚቃወሙ አባሎችዎ ከአባልነት ማገድዋ ይህንን የጥፋት መንገድ እየተጓዙ ለመሆኑ ተጨማሪ ማስረጃ ነው።

ፕሮቴስታንት 'ቤተክርስቲያን'  = የኤሳው ቤተክርስቲያን 

በአሁኑ ወቅትም የፕሮቴስታንት እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ ሀገራችን ሰሜናዊ ክፍል የዕውነተኛዋና ቀጥተኛዋ ርትዕት ተዋሕዶ እምነት አማኝና ጠባቂ በመሆኑ ከፍተኛ ሃይማኖትን የማስካድና የማስቀየር እንቅስቃሴ በተደራጀ መልኩ እየተካሄደበት ነው።

ይህ እንቅስቃሴ 'ሰሜኑ ለኢየሱስ' 'ትግራይ ለኢየሱስ' በሚል መሪ ቃል በግልጽና በድብቅ እየተካሄደ ነው። አሳዛኙ ነገር የቤተክህነቱና የቤተምልክናው አካላት በወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ በመጠመዳቸው ለእዚህ የጥፋት እንቅስቃሴ ተገቢ ትኩረት ሊሰጡት አልቻሉም።

No comments: