ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
- · የጌታችን መድሓኒታችን እየሱስ ክርስቶስና የእናቱ ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም የልደት ቀን መስከረም ፩ ነው።
- · ታኅሳስ ፳፭/፳፱ የአረማዊ ልምዶች መስራች ባቢሎናዊ ኒምሮድ የልደት ቀን ነው።
- · የገና ዛፍና የገና አባት(Santa Claus) የአረማዊ አምልኮ መገለጫ ናቸው።
ሃገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያ እግዚአብሔር ከቅዱስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ስጋ ለብሶ ወደ ምድር በእየሩሳሌም ተወልዶ
በመምጣቱ (በመገለጡ) እግዚአብሔር እየሱስ ክርስቶስ ከተወለደባት ቀን ጀምሮ ዓመተ ምሕረት
(የምሕረት ዓመት) በማለት የቀን መቁጠርያዋ መሠረት አድርጋዋለች።በዚህ መሠረትም የጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ምሕረት ለመስጠት ወደ ምድር ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ የነጻነትና የምሕረት ዓመት (ዘመን) ነው።
የኢትዮጵያውያን የቀን አቆጣጠር መሠረቱም ይህ ሆኖ ሳለ ማለትም የጌታችን መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ልደት አንድ ብለን ዓመተ ምሕረትን መቁጠር ከምንጀምርበት መስከረም ፩ (አንድ) ሆኖ ሳለ ታኅሳስ ፳፱ የልደት (ገና) በዓል ብለን ማክበራችን ለምን ይሆን፧ ይህ ማለት ከእውነተኛው የጌታ ልደት ሦስት ወር ከ፳፱ ቀናት በኃላ መሆኑ ነው።
ምዕራባውያን የቀን አቆጣጠራቸው ባቢሎናዊ የባዕድ አምልኮ መሠረቱ ነው።በዚህ ምክንያትም ከእውነተኛው የኢትዮጵያውያን የቀን አቆጣጠር ይለያል።ታኅሳስ ፳፱ የጌታችን
መድሓኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ልደት ከምዕራባውያን አረማዊ በዓል በአንድ ሳምንት ልዩነት መከበሩ ለምን ይሆን ፧ ታኅሳስ ፳፱ የጌታችን
መድሓኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ልደት ከምዕራባውያን አረማዊ በዓል በአንድ ሳምንት ልዩነት መከበሩ ለምን ይሆን ፧ ምዕራባውያን ታኅሳስ ፲፭ ወይም
ዲሰምበር(December) ፳፭ ምስራቃውያን ታኅሳስ ፳፱ ወይም ጃንዋሪ(January) ፯ ያከብሩታል። በአንድ ጌታ በዓል
ይህ ሁሉ ልዩነት ለምን ፧
በስድስተኛውም ወር መልአኩ ገብርኤል ወደ ኢትዮጵያዊቷ ቅድስት ድንግል ማርያም ከእግዚአብሔር ዘንድ ተላከ መልአኩም ወደ እርስዋ ገብቶ ‹‹ደስ ይበልሽ ጸጋ የሞላብሽ ሆይ፥ ጌታ ከአንቺ ጋር ነው፤ አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ›› አላት።መልአኩም መልሶ ‹‹ማርያም ሆይ፥ በእግዚአብሔር ፊት ጸጋ አግኝተሻልና አትፍሪ። እነሆም፥ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ። እርሱ ታላቅ ይሆናል የልዑል ልጅም ይባላል፥ ጌታ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል›› አላት።
ማርያምም ከዚያ በፊት በድንግልና ፀንሳ በድንግልና ስለወለደች ሴት ከቶ አልሰማችምና ፤ መልአኩን፥፡‹‹ወንድ ስለማላውቅ ይህ እንዴት ይሆናል፧›› አለችው።
መልአኩም የአብርሃምን ልጅ እስራኤላዊውን ዘካርያስን እንደነቀፈው ፤ የመልከ ጼዴቅን ልጅ ኢትዮጵያዊቷን ቅድስት ድንግል ማርያምን አልነቀፋትም ፤ መንፈስ ቅዱስ በአንቺ ላይ ይመጣል አላት እንጂ ‹‹የአምላክን እናት የሚያከብርና የሚቀድስ ከሥላሴ አንዱ አካል እነሆ››
መልአኩም ሁለተኛ መልሶ እንዲህ አላት ‹‹የልዑልም ኃይል ይጸልልሻልዕ ፥
‹‹ የልጁ እናት ትሆነው ዘንድ የሚያፀናት ከሥላሴ ኹለተኛ አካል እነሆ››ሦሥተኛም መልአኩ እንዲህ አላት፥‹‹ስለዚህ ደግሞ ከአንቺ የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል። ከድንግል የተወለደ ከሥላሴ ሦሥተኛ አካል እነሆ፦›› ---(የሉቃስ ወንጌል ፩፥፪፬፡፫፫)።
ገዳማውያን አባቶች እንደሚነግሩን ጌታችን መድሓኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የተጸነሰው ታኅሳስ ፩ ነበር።ይህ ቀንም ቃል ስጋ የሆነበት ጊዜ ነበርና ትስብዕቱ ይባላል። ማለትም ከሁለት አካላት ማለትም ከመለኮትና ከሰውነት አካላት አንድ አካል ከሁለት ባሕርያት ማለትም ከመለኮትና ከሰውነት ባሕርያት አንድ ባሕርይ ሆነ ማለት ነው። (ዮሓ ምዕ ፩)
ታኅሳስ ፩ የጌታ የጽንሰት ዕለት ከሆነ በዚህ ቀመር መሰረት ከ፱ ወርና ከቀናት በኋላ መስከረም ፩ አንድ የጌታችን ምድሓኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የልደት ቀን ይሆናል።በተመሳሳይም የወላዲተ አምላክ እናታችን ድንግል ማርያም የጽንሰት ቀን ታህሳስ ፯ በመሆኑ የልደትዋ ቀን ከቅዱስ ልጅዋ ጋር መስከረም ፩ ይዉላል።ይህም የግብጻውያን መጽሓፍ በሆነው መጽሐፈ ግጻዌ መስከረም ፲ ቀን የእግእዝትነ ማርያም የልደቷ ቀን መታሰብያ በዓል ነው ይላል።
ይህ የ ፩ ቀናት ልዩነት የተፈጠረዉ በጁልያን (Julian) አቆጣጠር በ፲፮ኛው ምዕተ ዓመት 1582 የካቶሊካውያን ሊቀ ጳጳስ ግሪጎሪ ፲፫ኛው ከነበረው የተለመደ አቆጣጠር የርሱ የሆነው አዲሱ የቀን አቆጣጠር ከጁልያን ካላንደር በ፲፩ ደቂቃት፣ ፲፪ ካልዒታት አጥሮ ስላገኝው አቆጣጠሩ
ቀይሮታል።ይህ ልዩነትም በ128 ዓመታት ውስጥ ፲፩ ደቂቃዎቹ ተደምረው የአንድ ሙሉዕ ቀን ልዩነት እንዲፈጠር አድርገዋል።በዚህ ምሰረትም
ከ፬ኛው ምዕተ አመት እስከ ፲፩ኛው ምዕተ አመት ውስጥ ማለትም ፲፪ኛው ምዕተ አመት ላይ ፲ ሙሉዕ ቀናት ልዩነት ሊፈጠር ችሏል።በዚህ
መሰረትም በበዓላት አከባበር ላይ ልዩነት እንዲፈጠር ሆኗል።ካቶሊካውያንንና ኦርቶዶክሳውያን ይህንን የቀን ልዩነት ከመፈጠሩ በፊት
የልደት በዓል በአንድ ቀን ማለትም ታኅሳስ ፲፭ ወይም ዲሰምበር 25 ያከብሩት እንደነበር ጥንታዊ የሆኑ የታሪክ ማስረጃዎች ያስገነዝባሉ።
የልደት/ገና በዓል አረማዊ ነው።
ታኅሣሥ 25 የሚከበረው የገና በአል ብዙ ሰዎች
የክርስቲያን በዓል እንደሆነና ጌታችን መድሓኒታችን እየሱስ ክርስቶስ
ልደት የሚከበርበት ቀን እንደሆነ አድርገው ያስባሉ። ጌታችን መድሓኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የተወለደው ታኅሣሥ 25 እንዳልሆነ ከላይ ተገልፇል።ይሁን እንጂ በዚያ
ቀን የተወለዱ በርካታ የአረማውያን አማልክት አሉ።ከጥንት የባቢሎናውያኑ
ጀምሮ የፀሐይ አምላክ መወለዱን ወይም ዳግም መወለድ ታኅሣሥ 25 በተለያዩ ስሞች ወይም መጠሪያዎች ይከበር ነበር።
ጌታችን መድሓኒታችን እየሱስ
ክርስቶስ ታኅሣሥ 25 እንዳልተወለደ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃዎች ማቅረብ ይቻላል።
የሕዝብ ቆጠራ - ኢየሱስ
ከመወለዱ ትንሽ ቀደም ብሎ አውግስጦስ ቄሳር “የዓለም ሕዝብ ሁሉ እንዲመዘገብ አዋጅ አወጣ።” እያንዳንዱ
ሰው “ወደየራሱ ከተማ” በመሄድ መመዝገብ ይጠበቅበት
ነበር፤ ይህም ለአንድ ሳምንት ወይም ከዚያ በላይ ጉዞ ማድረግን ይጠይቅ ይሆናል። (ሉቃስ
2:1-3) ይህ ትእዛዝ የወጣው ግብር ለመሰብሰብ ወይም ወታደሮችን ለመመልመል ታስቦ ሊሆን ይችላል፤
አዋጁ የወጣው መቼም ይሁን መቼ፣ አብዛኛው ሕዝብ እንዲህ ያለ ጉዞ ማድረግ እንደማይፈልግ ግልጽ ነው። በመሆኑም አውግስጦስ በቅዝቃዜው
ወቅት እንዲህ ያለ ጉዞ እንዲያደርጉ የሚያስገድድ አዋጅ በማውጣት አብዛኛውን ሕዝብ የሚያስቆጣ ድርጊት እንደማይፈጽም የታወቀ ነው።
እረኞች - በዚያን
ወቅት “ሌሊት ሜዳ ላይ መንጎቻቸውን ሲጠብቁ የሚያድሩ
ነበሩ። (ሉቃስ 2:8) መንጋዎቹ ክረምቱን የሚያሳልፉት በጉሮኗቸው ውስጥ ሆነው ነበር። እረኞች መንጋቸውን ሲጠብቁ በሜዳ ማደራቸውን ከሚናገረው የወንጌል ዘገባ አንጻር ሲታይ የገና በዓል ቅዝቃዜ በሚበረታባቸው ወራት መከበሩ ራሱ ቀኑ ፈጽሞ ትክክል እንዳልሆነ ያስገነዝባል።ራሱ ጌታችን መድሓኒታችን
እየሱስ ክርስቶስ ወንጌል ሲስብክ "ሽሽታቹ በክረምት ወይም በሰንበት
እንዳይሆን ጸልዩ።" ---ማቴዎስ ፳፬፡፳
መስከረም - የምዕራባውያን የቀኖችና ወሮች ስያሜ ቀጥታ የጣዖት አምልኮዋቸው
የሚገልጹ ሲሆኑ የኢትዮጵያውያን ግን የእግዚአብሔርን ክብር ከፍ በማድረግ የሚያከብሩ ናቸው። ጌታችን መድሓኒታችን እየሱስ ክርስቶስ
ከተወለደበት ዘመን ጀምሮ ዓመተ ምሕረት በመባል ይጠራል። ምክንያቱም ክርስቶስ በመወለዱ ምሕረት ተገኝቷልና። በዚህ መሰረትም አባቶቻችን
ክረምት የብሉይ ኪዳን የሃጥያት ምሳሌ ሲያደርጉት መስከረም ሲጠባ የሚመጣው ወቅት ደግሞ የአዲስ ኪዳን ምሥራች የምሕረት ወቅት ያድርጉታል። መስከረም ማለትም ከረመ ከረመ፥ ምሴተ ክረምት፣ የክረምት መካተቻ ማለት ነው።
ኢየሱስ በታኅሣሥ 29 (ወይም እንደ አውሮፓውያን
አቆጣጠር ታኅሣሥ 25) መወለዱን የሚያሳይ መረጃ ከሌለ ገና በዚህ ወቅት የሚከበረው ለምንድን ነው?
ታኅሣሥ 25 የሚከበረው የገና በአል ብዙ ሰዎች የክርስቲያን በዓል እንደሆነና ጌታችን መድሓኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ልደት የሚከበርበት ቀን እንደሆነ አድርገው ያስባሉ። ጌታችን መድሓኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የተወለደው ታኅሣሥ 25 እንዳልሆነ ከላይ ተገልፇል።ይሁን እንጂ በዚያ ቀን የተወለዱ በርካታ የአረማውያን
አማልክት አሉ።ከጥንት የባቢሎናውያኑ ጀምሮ የፀሐይ አምላክ መወለዱን
ወይም ዳግም መወለድ ታኅሣሥ 25 በተለያዩ ስሞች ወይም መጠሪያዎች ይከበር ነበር።የቤተ ክርስቲያን መሪዎች በቅዝቃዜው ወቅት መገባደጃ ላይ ያለውን
ይህን ቀን የመረጡት ‘ድል የማትደረገው ፀሐይ የልደት ቀን’ ከሚከበርበት የሮማውያን አረማዊ ክብረ በዓል ጋር እንዲገጣጠም ፈልገው” ስለነበረ ይመስላል።
የኢትዮጵያ ቅድስት ቤተ ክርስትያን ምንም ስህተት እንደሌለባት እምነቴ ነው። ምክንያትቱም ራሱ
ኢትዮጵያዊው እየሱስ ክርስቶስ ስለመሰረታት። ሆኖም አስመሳይና ቅጥረኛ አገልጋዮች ይህንን የጌታችን የልደት ቀን ቀይረዉታል። ይህም
እውነተኛው የኢትዮጵያ ትንሳኤ በሚገለጥበት ጊዜ እውነቱ ይወጣል። በተመሳሳይ የጌታችን መድሓኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የልደት ቀን
በተመሳሳይ ቀን የሚያከብሩ መናፍቃን ከየይሖዋ ምሥክሮች ውጪ ይገርማሉ። ምክንያቱም እምነታቸው ከምዕራባውያን አረማዊ መነሻ ያለው
ሆኖ ሳለ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን የተሳሳተው የልደት ቀን እኩል ማክበራቸው ነው።
ታኅሣሥ 25 የሚከበረው የገና
ወይም የክርስቶስ ልደት በዓል የሚሉት በመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታችን ወደ ዘፍጥረት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ይወስደናል።ኒምሮድ የተባለ
ሰው የእግዚአብሔርን እውነት የሚቃወሙ የብዙ አረማዊ አምልኮቶች መስራችና መነሻ ነው። አለማችን በዲያብሎስ ውሸት እየተታለለ ነው።ይህም በታልቁ የእግዚአብሔር ቃል እንደተገለጸው ወይም ትንቢት እንደተነገረለት እየተፈጸመ ነው።
‹‹ታላቁም ወደታች ተጣለ ፤ እርሱ ሰዎችን ሁሉ የሚያስተው ዲያብሎስ ወይም ሰይጣን ተብሎ የሚጠራው የቀድሞ እባብ ነው። እርሱ ወደ ምድር ተጣለ ፤ የእርሱም መላእክት ከእርሱ ጋር አብረው ተጣሉ።››
---የዩሐንስ ራዕይ ፲፪፡፱
ዲያብሎስ ጥንታዊው የባቢሎን
አረማዊ የልደት ቀን ዘመናዊነት በመጨመር ክርስትያናዊ በማስመሰል የጌታችን መድሓኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ልደት ነው በማለት አረማዊ
አምልኮው እያስፈጸመ ነው።
"እርሱም በእግዚአብሔር
ፊት አዳኝ ነበረ ፤ ስለዚህም በእግዚአብሔር ፊት ኃያል አዳኝ እንደ ኒምሮድ ተባለ።" ዘፍጥረት፲፡፱ ላይ የሚገኝ ቅዱስ ቃል ነው። ኒምሮድ የኖህ ታላቅ የልጅ
ልጅ ነው።"የገነት ንግሥት" ተብላ የምትታወቀው የግብጽዋ ጣዖት አይሪስ ልጅ ታህሳስ ፳፭ ነበር የተወለደቺው። "የገነት ንግሥት" የሚለው ስያሜ የኒምሮድ እናት ሴሜራሚስ ቀጥታ በመውሰድ
ትጠቀምበት ነበር።ናምሩድ ሴሜራሚስ እናቱን አግብቷት ነበር።እናቱም ሚስቱም የነበረቺው ሴሚራመስ ከናምሩድ ህልፈት በኋላ የኒምሮድን
ሕልውና እንደ መንፈስ አንድ አካል የሚገልጸውን ክፉ ትምህርት አስተጋባች።
ከደረቀችና ካረጀች ፍሬ መስጠት
ካቆመች ዛፍ ላይ አንድ ቀን አንዲት ክፍልዋ ማቆጥቆጥ ሲጀመር በማየትዋ ይህ የኒምሮድ ሞት በ አዲስ ህይወት የመቀየሩ ምልክት ነው
ብላ ታምን ነበር።ኒምሮድ በተወለደበት በእያንዳንዱ አመት ቅጠሉ የማይረግፍ ዛፎችን እየጎበኘና ስጦታው ያስቀምጣል የሚል አጉል እምነት
ነበራት።ታኅሣሥ 25 የኒምሮድ የልደት ቀን ነበር። በተጨማሪም ይህ የገና ዛፍ ትክክለኛ መነሻ ነው።
የገና ዛፍ
የገና ዛፍ አረማዊ በሆነው
በዓል ላይ እንደ አምልኮ መገለጫ በማድረግ ኢትዮጵያውያን ሉላዊነትና ዘመናዊነት ባመጣብን ጣጣ እየተጠቀምንበት ነው።ሰው ሰራሽ የሆነው
የገና ዛፍ ለመግዛት የምናደርገው ጥድፍያም አስገራሚ ነው።ምዕራባውያን ስለአደረጉት ብቻ ትክክል የሚመስለን አሳዛኝ ፍጥሮች ሆነናል።ኢትዮጵያዊነታችን
ሽጠናል። በዚህ ጥፋትም የመገናኛ ብዙሓን የማስታወቅያና የበዓል መርሃግብሮች ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው አምናለው። የገና ዛፍ አረማዊ መገለጫ
ከላይ እንደተገለጸው በቀጥታ ከኒምሮም የእናቱና ሚስቱ የነበረቺው
ሴሚራመስ አጉልና ክፉ ከኒምሮድ ሞት በኋላ የነበራት እምነት
ጋር የሚያያዝ ሲሆን ከጊዜያት በኋላ ሌሎች ባዕዳዊ አምልኮዎች እየተጨመሩበት የመጣ ነው።
በዞራስተርን የሁለትአማልክት
ዕምነት መሠረት ክፉውና ደጉ የተባሉ ሁለት አማልክቶች አሉ። እንደ ዕምነቱ አስተሳሰብ ከሆነ እዚህ ምድር ላይ የሆነው እየሆነው
ያለውና የሚሆነውም ማንኛውም ነገር በሙሉ የሚከናወነው በእነዚህ በሁለቱ አማልክቶች ፉክክር ነው።ክፉው አምላክ ከሰለጠነ (የበላይ
ከሆነ) በምድር ላይ ክፉ የሆኑ ብዙ ነገሮች ይከሰታሉ። በተቃራኒው ደግሞ ደጉ አምላክ ከሰለጠነ በጎ ነገሮች ይከሰታሉ ማለት ነው።
ምዕራባውያኑ ታዲያ ደጉን አምላካቸውን ማለትም ጣዖታቸውን ሳተርን ብለው ይጠሩታል።ሳተርን ሌላኛው የኒምሮድ መጠርያ ስያሜ ነው።
በምዕራቡ ዓለም የክረምቱ ወቅት
በጣም አስቸጋሪ ነው። ዛፎች ሁሉ ቅጠሎቻቸው ይረግፋሉ። ልምላሜ አይታይባቸውም።ፅድ ግን በተፈጥሮው ይህን አስቸጋሪ ወቅት ተቋቁሞ
የማለፍ ኃይል አለው። በመሆኑም ፅድ ክፉውን ዘመን (ክረምቱን)ተቋቁሞ መልካሙ ዘመናቸው እስኪመጣላቸው ድረስ በልምላሜ ይቆይላቸዋል።
ይህም ሳተርን (ደጉ አምላካቸው) ከክፉውአምላክ ለመሸሸግ በፅድ ውስጥ
ተደብቆ ይኖራል ብለው ያመናሉ። ይህም ሴሚራተስ የኒምሮድ እናትና ሚስት ኒምሮድ በዛፍ ላይ ስጦታዎች ያስቀምጣል ብላ ማመንዋ ለዚህ
እምነት መሰረቱ ነው።
ምስጋና ለፅዱ ይሁንና ደጉ
አምላካቸውን ደብቆ ስላቆየላቸው ባለውለታ ስለሆነ የደጉን አምላክ የእንኳን ደህና መጣህ በዓልሲያከብሩ ታዲያ ፅድን ለበዓላቸው ማድመቂያነት
ይጠቀሙበት ነበር። ይኸው ትውፊታቸው ዛሬም ድረስ አለ። በአጭሩ ከጥንት ጀምሮ እነርሱ ይኽን በዓል የሚያከብሩት ሳተርን ለተባለው
ጣዖት (ደጉ አምላክ) ያደርጉት የነበረው ሥርዓት ነው።በዚህ ዓይነት ሁኔታ ታላቁ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ክርስትናን በአዋጅ ካስፋፋበት
ጊዜ ጀምሮ በውጭው ዓለም ጥንት የነበሩብዙ ጣዖታዊ በዓላት ክርስቲያናዊ በዓል መስለው አሁንም ድረስ በብዙ ሀገራት እየተከበሩ ይገኛሉ።
የገና ዛፍ በጣም ትልቅ ትርጉም አለው ግን ክርስትያናዊ ፍቺ አይደለም። ኒምሮድ የጥንታዊትዋ
ባቢሎን ንጉሥ ከሞቱ በኃላ የፀሐይ ግዑዝ ባህርይ እንደነበረና በዚህም ምክንያት አምላክ እንደሆነ በአረማውያን ይታመናል። የገና
ዛፍ ታሙዝ ነው የተገደለው አምላክ እንደገና በህይወት ይመጣል ተብሎ የሚታመንበት።
የገና አባት / Santa Clause
ስለ ገና አባት ኢትዮጵያዊ
የሆነ መረጃ ሳፈላልግ የኔ ድክመትም ይሆናል ምንም ማግኝት አልቻልኩም።
ይህ ቃል ወይ መጠርያ በቀጥታ ከምዕራባውያንና ምሥራቃውያን የተወሰደ ይመስላል። በአሁኑ ወቅት ምዕራባዊ አለባበስና ሁኔታ ያለው
ቀይ ልብስና ነጭ ሰው ሰራሽ ጺም ያለው ሰው ኢትዮጵያዊ ልጆችን ሰለባ እያደረገ ነው።
ሳንታ (የገና አባት) የሰይጣን ሰንሰለት ነው። ሳንታ (የገና አባት) ጨርሶ ክርስቲያናዊ አይደለም ፣ ነገር ግን የሳተርን መልክዓ ምድር በመባል
የሚታወቀው የጥንት የጣዖት አምልኮ ድነት ነው።የገና በዓል አመጣጥ በአረማውያን አረመኔ ክብረ በዓላት ውስጥ የሚገኝ ሲሆን በፀሐይ
የተመሰለው የጥንቷ የሞት መድረክ ነው።
የሞተው የሟች አምላክ፣ የሲኦል
ጣኦት አምላክ እንደመሆኑ መጠን ሉሲፈር ከይሁዳዊ፡ክርስትና ባህል ውጪ ባሉ ባህሎች ይመለክ ነበር።የሟች አምላክ ጥንት ዘመን በበርካታ
የተለያዩ ሕዝቦች ባህል መሠረት የተለያዩ ስያሜ አሉት። ግብፃውያን
ኦሳይረስ፣ ከነዓናዊያን ባአል፣ ባቢሎናዊያን ቤል ወይም ማርዱክ፣ ግሪኮች ዳዮኒሰስ እና የፋርስ ሚትራስ ያመልኩ ነበር።የሟች አምላክ
ከቬነስ ጋር ተመሳሳይነት አለው፣ እሱም የመጀመርያው የሮማይስጥ (ላቲን) መጠርያው ሉሲፈር ነበር። በተጨማሪም እርሱ በፀሐይ የሚወከለው
ሲሆን ከፀሐይ ግርዶሽ (ፕላኔቷ) ጋር በማነፃፀር "ከምሽቱ ጩኸት" (ሳተርን) ከፀሐይ ግርዶሽ ጋር ይመሰረታል።እንደ ሙስሊሞች አምላክ፣ የሙታን ነፍሳትን ይመራ ነበር። እናም፣ ቀደምት
ጣዖት አምላኪዎች እሱን ማምለክ አስፈላጊ እንደሆነ ስላመኑ ይህንን ክፉ ወደ
አምላክ ደረጃ ከፍ አደረጉት።
ጥሩው አምላክ መልካም ነገርን
መሻት ቢጠይቅበትም ክፉው አምላክ የክፋት ድርጊትን ይጠይቃል። ስለዚህም ክፉውን ለመከላከል ለአማልክቱ አጋንንት ክፉ ነገሮችን መስራት አስፈላጊ ነበር። የህጻናት መሥዋእትም
ያቀርቡለት ነበር።ስለዚህም እስራኤላውያንም የራሳቸውን ልጆች ሞሎክ ለሚባለው የከነዓናውያን አምላክ መሥዋዕት ያቀርቡለት ነበር።ሞሎክ
ባቢሎናውያን "የፀሐይ ኮከብ" የሚሉት ሳተርን (ኒምሮድ) ነው።በግሪካውያን አፈ ታሪክ
የሚገኝው ልጆቹን የሚውጠው የክሮኖስ ታሪክም ከዚህ አምልኮ ጋር የተያያዘ ነው።
ይህንን ሰይጣናዊ አምልኮ የባቢሎን
ውላጅ በሆነቺው ጸረ ክርስቶስ የካቶሊክ ቤተክርስትያን የቀጠለ ሲሆን ይህም የኢሉሚናቲ አባላት አሁንም ልጆች መሥዋዕት በማድረግ
ሰይጣንን የሚያስደስቱበት መንገድ ነው።መልኩ ቀይሮ ሳንታ በ ፬ኛው ምዕት አመት በትንሽዋ ኤስያ በነበረው የካቶሊክ ቄስ ቅዱስ ኒኮላስ
የተሰመ ነው።ቄስ ኒኮላስ በበጎ ስራውና ስጦታዎችን በመስጠት ይታወቅ ነበር።ይህ ልምድም መጀመርያ አካባቢ ወደ አውሮፓ የተዛመተ
ሲሆን ወደ አሜሪካ ውስጥ የተለመደው ደግሞ የዳች ሰዎች መስፈር ሲጀምሩ ነው።
ይህ መልኩ ቀይሮ የመጣው የዲያብሎስ
የማታለያ ዘዴ አሁን በመላው አለም ተቀባይነት አግኝቷል። በሃገረ እንግሊዝ አሮጌው ኒኪ (Old Nicki- Saint
Nokolas) ማለት በቀጥታ ዲያብሎስ ማለት ነው።ይህ ቃል የተወረሰው ከሆላንዳውያን(ዳች) ህዝቦች ነው።ይህም የኦክስፎርድ መዝገበ
ቃላት በማየት ማረጋገጥ ይቻላል።ሳንታ ወይም የገና አባት ልጆች እውነተኛ አባት የሆንነውን ጌታችን መድሓኒታችን እየሱስ ክርስቶስ
እንዳያውቁትና እንዳያዩት ዲያብሎስ ለማታለያ የፈጠረው ገጸ ባህሪ ነው።
ከላይ ከቀረቡት ነጥቦች አንጻር
እውነተኛ ኢትዮጵያውያን በገና በዓል በሚደረጉት ልማዶች መካፈል ይኖርባቸዋልን፧ አምላክ ለእሱ የሚቀርበው አምልኮ እሱን ከማያመልኩ
ሰዎች ሃይማኖታዊ እምነቶችና ልማዶች ጋር መቀላቀሉ ያስደስተዋልን፧ ሐዋርያው ጳውሎስ በቆላስይስ ፪፥፰ ላይ እንዲህ ሲል አስጠንቅቋል
"እንደ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን፣ እንደ ሰው ወግና እንደ ዓለማዊ እንደ መጀመሪያ ትምህርት ባለ በፍልስፍና
በከንቱም መታለል ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠበቁ።"
ሐዋርያው እንደሚከተለው በማለትም
ጽፏል "ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤
ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና፧ ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው፧ ክርስቶሽ ከቤልሆር [ሰይጣን] ጋር ምን
መስማማት አለው፧ ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው፧"
—፪ ቆሮንቶስ ፮፥፲፬-፲፭
በስተመጨረሻ ማለት የምፈልገው
ነገር ኢትዮጵያውያን ባህላችን መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሆኑ ተረድተን ከአረማዊ የምዕራባውያን አምልኮ ጸድተን አምላካችን ማክበር አለብን።
"በዓለም ከሚገኝ
እድፍ በመጠበቅ ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ ለእግዚአብሔር ለማቅረብ ይጥራሉ።"
—ያዕቆብ ፩፥፳፯
ታኅሣሥ 10, 2007 ዓመተ ምሕረት