ከዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
ለናሁሰናይ በላይ የተሰጠ መልስ
ወንድም ናሁሰናይ ፅሑፍህ ትክክለኛው የወያኔ ወቅታዊው የተዳፈነውን የዘረኝነት እሳት የሚያቃጣጥል ሆኖ አግኝቸዋለው።ታሪክ ማወቅ ካለፈው መጥፎና ጎጂ ሁኔታ ተምረህ ለቀጣዩ ትውልድ የትመቻቸ ሁኔታ ለመፍጠር እንጂ ለመወቃቀስና ለጥላቻ መሆን የለበትም።ይህም የቴዲ አፍሮ የሁል ግዜ አቅጣጫ ነው።ማወቅ ያለብህም ቴዲ አፍሮ ፖለቲከኛ ሳይሆን የእግዚአብሔርን መንገድ ተከትሎ ሙዚቃን በመጠቀም ፍቅር፣እውነትንና ኢትዮጵያዊነትን የሚሰብክ ምርጥ ልጅ ነው ።ሆኖም ወያኔ የፈጠረብህን የጥላቻና የከፋፍሎ መግዛት መንፈስ ይህንን እውነት እንዳታይ አርጎሃል።እውነትም ጨለማና ብርሃን ሊገናኙ አይችሉምና።"እንዳለፉት አንዳንድ መንግስታትእና ሊሂቃን ኢትዮጵያን ሳያውቁ ኢትዮጵያን የመሩ ሰዎች ናቸው"ብለህ ፅፈሃል።የሚገርመው ነገር ከማንም በላይ አንተ ኢትዮጵያን የምታውቃት ለማስመሰል መሞከርህ ነው።ከጽሁፍህ እንደተረዳሁት ላንተ ኢትዮጵያ ማለት ወያኔ ነው።በዚህ ምክንያትም ስለ አለፉት መንግስታት እንኳን በጎ ነገር ለመጥቀስ አልሞከርክም።ታሪክህን ከጨለምተኝነት ወጥተህ ለመገንዘብ ከመኮርክ እስከ አለፈው አርባ (40)አመት ድረስ ኢትዮጵያ እግዚአብሔርን ባስቀደሙ ነገስታት ትመራ ነበር።ቴዲ አፍሮም ይህንን በሚገባ ስለሚያውቅና ስለአመነብተ ስለ ነገስታቱ ዘፈነ።ሃጸይ ሃይለስላሴ ለኢትዮጵያ የዋሉት ውለታ ከወያኔ በላይ ነው።ይህንንም ለመረዳት አእምሮህን በነጻ መንፈስ መሙላት ግድ ይላል።ሃጸይ ሃይለስላሴ በየቀኑ በማስቀደስ ከፈጣሪ ጋር በመማከር አገሪትዋን ይመርዋት ነበር።እዚህ ላይ ብዙ ስለ ሃጸይ ሃይለስላሴ በጎ ስራዎች መዘርዘር ይቻላል።መገንዘብ ያለብህም ንጉሱም እንዳንተ ሰው መሆናቸውና ስህተት ሊሰሩም እንደሚቹሉም ነው።አንድ ህዝብም መመራት ያለበት በትክክለኛው የእግዚአብሔር መንፈስ ባስቀደመ መንገድ እንጂ ስለ ስጋ ብቻ በሚጨነቅና ሰይጣናዊ በሆነ መንግስት አይደለም።እስቲ ሃጸይ ምኒሊክ ጣልያንን ያሸነፉት በመሳርያና በቴክኖሎጂ የተሻሉ ስለነበሩ አይደለም።ኢትዮጵያዊው አስተባብረው ታቦተ ጊዮርጊስ ተሸክመው ፈጣርያቸው አምነው እንጂ(ጥቁር ሰው)።የወያኔ ስራም ልንገርህ ኤርትራን በመሸጥ መልሶ ደግሞ የአንድ ዘር ልጆች በፖለቲከኞች የፍላጎት አለመጣጣም ምክንያት እርሰበርሱ አፋጁት(ዝሆኖች ተጣልተው ሰበሩት ድንበሩን፡ዳህላክ)።ወንድሜ ኢትዮጵያ ሃገረ እግዚአብሔር መሆኗ አትርሳ።ስለዚህም ስለዚሲባል እግዚአብሔርን የሚያስቀድም ማንነታችንን የሚጠብቅ ንጉስ ያስፈልጋታል።በዚህ ምክንያትም ከ አርባ አመት በፊት የነበሩት ነገስታት ቤተ ክርስትያንን በማሳነጽ(ታቦተ ጽዩን አክሱም ያረፈበት ቤተ ክርስትያን ያሁኑ ገጽታው እንድይዝ አድርገው ያሳነጹት ሃጸይ ሃይለስላሴ ናቸው።) ሰንደቅ አላማችን ላይ ቅዱሳት ምልክቶች በማስቀመጥ ይገልጹት ነበር።በሃጸይ ሃይለስላሴ ግዜ በነበረው ሰንደቅ አላማ ያለው አንበሳም የይሁዳ አንበሳ ይባላል።ይህም በዜባዊ ትርጉሙ እየሱስ ክርስቶስን ይወክላል።ወንድም ናሁሰናይ ስለ እውነት የምትቆረቆር ከሆነ እስቲ በወያኔ ሰንደቅ አላማ ላይ ያለው ባለ አምስት ጫፍ ኮከብ(pentagram) ትርጉሙ ምን ይሆን? የብሔር ብሔረሰቦች እኩልነት ብለህ እንዳታስቀኝ።ባይሆን ትርጉም ልንገርህ ይህ ባለ አምስት ጫፍ ኮከብ በሰይጣን አምላኪዎቹ የምስጥር ማህበራት ዘንድ ሰይጣናዊ ትርጉም ያለውና ፈጣሪን የመካድ ምልክት ነው።እስቲ ይህንን ኮኮብ ለምን እንዳስቀመጡት ጠይቃቸው።ናሁሰናይ አሁን የሚያስፈልገን የወያኔ የመለያየት ሴራ ሳይሆን ፍቅር አንድነትና እምነት ነው።ይህንን የሚያስተምሩንን ሰዎች ማክበር እንጂ በጥላቻ ማየት የለብንም።ቴዲም ፍቅር ያሸንፋል ማለቱ እውነት ነው።ምክንያቱም መጽሓፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ፍቅር ነው ይላልና።እግዚአብሔርም አሸናፊ ነውና።
"ቂም በቀል ክፉ ነው።
ከ አምላክ ያለያያል።
ጃ ያስተሰርያል"
"ቅርብ ነው አይርቅም የኢትዮጵያ ትንሳኤ
በአንድነት ከገባን የፍቅር ሱባኤ"
ኢትዮጵያ የቃልኪዳን ምድር።
ኢትዮጵያ ትቅደም ።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር።