ዘርአዳዊት ዘ-አቢሲንያ
የመጽሐፈ ገጽ (facebook)
የማህበራዊ ትስስር መካነ-ድር መስራችና ባለቤት ማርክ ዙከምበር በቅርቡ ከቻይናዊት ሚስቱ የመጀመርያ ሴት ልጅ ወልዷል።ማርክ ለልጁ የመልካም ምኞት ደብዳቤም ጽፎላታል።
በትላንትናው ዕለት በመጽሓፈ ገጹ በለጠፈው ደብዳቤ ከይዘቱ መረዳት የሚቻለው ማርክ ዙከምበር ለመጪው ትውልድና ለልጁ በቴክኖሎጂ የተሳሰረ አንድ የአለም ስርዓት እንደሚመኝላቸውና ጥሩ ተስፋም እንዳላቸው እሱም ይህንን እውን ለማድረግ እንደሚሰራ ገልጿል።
አንድ የአለም ስርዓት የአውሬው የመጨረሻ ዕቅድ መሆኑ መጽሓፍ ቅዱስ በየውሓንስ ራዕይ ይነግረናል።ማርክ ዙከምበርግ ከሰላቢ እጆች( ኢሊሙናቲ)ና የስለላ ድርጅቶችና ከቢልደርበርግ የምስጥር ማህበር ጋር እንደሚሰራ ይታወቃል።በአንድ ወቅትም ማርክ ዙከምበር አንድ የ አለም ስርዓትን የሚሰብክ ዎርልድ ኦርደር የተሰኝ የሄንሪ ኪሲንገር መጽሓፍ እያነበበ እንደሆነ በመጽሓፈ ገጹ ላይ ለተከታየቹ ለጥፎ ነበር።
የመጽሐፈ ገጽ መካነ-ድር የአለምን አጀንዳዎች ፖለቲካዊ ጉዳዮችን የመወያያ አርዕስቶች ለማድረግና የ አለምን ህዝብ በሚፈልጉት አቅጣጫ ለመንዳት ሰላቢ እጆች ይጠቀሙበታል።
እዚህ ከተለጠፈው ምስል(የማርክ ዙከምበር) ጀርባ የሚታየው ጽሑፍ "Our Mission_To make the world more open and
connected"ይላል።ማለትም የመጽሓፈ
ገፅ(facebook) ዓላማ አለማችንን ግልጽ በማድረግ ግለኝነትንና ምስጥርን በማስቀረት በሰዎች ዘንድ ትስስር መፍጠር ነው።ይህም
ማለት በመጽሓፈ ገጽ በኩል የአለም ህዝብ የባህል እምነት የመሳሰሉት ልዩነቶች በዘመናዊነትና ስልጣኔ ሽፋን አንድ ማድረግና ትክክለኛውን
ነገር እውነት ካልሆነው ነገር በአንድ የአለም ስርዓት አስማምቶ እውነትን ለመቅበር ስለሚረዳቸው ነው።
ደብዳቤው ለመንበብ>>>
ደብዳቤው ለመንበብ>>>
ኅዳር 21
2008 ዓመት ምሕረት