EAR

አዲስ ነገር

Tuesday, 29 December 2015

የሃሎዊን (Halloween)በዓል እውነታ

ዘርአዳዊት -ኢትዮጵያ


በምዕራባውያን ዘንድ በዛሬው ዕለት ማለትም ጥቅምት ፴፩ እ.ፈ. የሚከበረው የሃሎዊን በዓል ባብዛኛው የሚታወቀው የአሜሪካውያን ተደርጎ ነው።ይሁን እንጂ ይህ በዓል በብዙ የዓለም ክፍሎች ተወዳች እየሆነ መጥቷል።ሃሎዊን የሞቱ ቅዱሳንን ለማሰብ በሚል ይጀመር እንጂ ድርጊቱ የሙት መንፈስ የሆነውን ሰይጣንን ለማሰብ የተሰራ ለመሆኑ የድርጊቱ ክንዋኔ ያስረዳል።ሃሎዊን ከመንፈሳዊ ፍጥረታት ጋር ለመገናኘት ታስቦ የሚደረግ ጥንታዊ አረማዊ በዓል ነው።አብዛኛዎቹ ፍጥረታት ደግሞ የሚያስፈሩና የሚያስደነግጡ ናቸው።የበዓሉ ያከባበር ሁኔታም ስይጣናዊ መሆኑ ይናገራል።የሚያስፈራ ምስልና ቅርጽ፤ ጥርሱ ያገጠጠ፤ ዓይኑ ያፈጠጠ፤ አጽሙ  የተቆጠረ ማስጠሎ ነገር ለብሶ ወይም አጥልቆ  ሰውን በማስደንገጥና በማስፈራራት ይከበራል።ዛሬም ድረስ በዓለም ዙርያ ብዙ ሰዎች በዓሉ በሚከበርበት ጥቅምት ፴፩ እ.ፈ.አ የሙታን መናፍስት ብለው ከሚጠርዋቸው የሞቱ ሰዎች ጋር ለመገናኘት ጥረት ያደርጋሉ።የጥንቶቹ አውሮፓ ኬልቶች ሥርዓተ አምልኮ የሚከተሉ በሺ የሚቆጠሩ የዊካ እምነት(የጥንቆላ ሥርዓት የሚከተል ሃይማኖት)ተከታዮች ዛሬም ሃሎዊንን የሚጠሩት ሳምሄን በተባለው ጥንታዊ ስሙ ሲሆን በዓመቱ ውስጥ እጅግ ቅዱስ እንደሆነ ምሽት አድርገው ይቆጥሩታል።ይህ ባዕዳዊ አምልኮ በዓል ባለማወቅ ወይም ዘመናዊነት መስሎን ከማክበር መቆጠብ ይጠበቅብናል።