ዘርአዳዊት ዘ-ኢትዮጵያ
ከጓደኛየ ጋር ሻይ እየጠጣን ነው።ከድምጽ ማጉያው የቴዲ አፍሮ በሬጌ የሙዚቃ ስልት የተሰራ "ኦ አፍሪካየ" የሚል ዜማ ይደመጣል።ታድያ የቴዲ ሙዚቃዎች ከልብ የማደምጣቸውና ኢትዮጵያዊነቴን መልሰው የሚነግሩኝ በመሆናቸው ብዙዎቹ ከነ ግጥማቸው አብሬው እጫወታለው።በዚህ ጊዜ ነበር አብሮኝ የነበረው ጓደኛየ አብሬው እኩል ሙዚቃው በመጫወቴ እየተገረመ
"የዮቶር ልጅ ርሥቱ
አባይ ሆኖ ጣና ዳር ቤቱ"
የሚለው ግጥም ከአፌ ሳወጣ ደግሞ ይሄ ቴዲ የሚሉት ሰው ያማይጫወተው ሙዚቃ የለም ዩቶር ደግሞ ማነው አባይ ሆኖ ጣና ዳር ቤቱ ማለቱስ ምንድነው ፧ በማለት ጠየቀኝ።እኔም
ባለማወቁ ሳይወሰን ለማወቅ በግልጽ በመጠየቁ አድናቆቴ በመግለጽ ያሁኑ ትውልድ ንግሥና የሆነውን ኢትዮጵያዊነት በመጣል ፖለቲከኞች የሰጡት የዘርና የጎሳ ድራማ መሪ ተዋናይ በመሆኑ ኢትዮጵያዊነት የሚነግሩት የተደበቀው ታሪኩ ጥንታዊው የብራና መጻሕፍት በማጥናት ከእግዚአብሔር ጋር እንዲገናኝ የሚያበሩለት መብራት በጨለማ እየቀየረው በመሆኑ ያሳዝናል።
ጓደኛየ ጥያቄ ስለጠየቀኝ ግን ውስጤ በጣም ደስ ብሎታል።ምክንያቱም ኢትዮጵያዊነት ታላቅ ክብር ሆኖ በዘመናዊነትና በባድ ትምህርቶች ተሸፍኖ እንዳይታወቅ ስለተደረገ ይህንን ገልጾ ለሰዎች ለማስረዳት ፍላጎቴ ከፍተኛ በመሆኑ ነበር።
ሙዚቃው እንዲደገም በማድረግ እያንዳንድዋ ስንኝ ምን ትርጉም እንደያዘች ለማስረዳት ጀመርክ።ታድያ የውይይታችን
ሃሳብ የሚመሰረተው በእግዚአብሔር ቃል በሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ነው።የኢትዮጵያ መሠረትም እግዚአብሔር ነው።ዩቶር ማነው ፧ ዩቶርም መጽሓፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኝ የሰው ስም ነው።ታድያ ቴዲ
ይህ ሰው ኢትዮጵያዊ በመሆኑ ነበር ስሙ ጠርቶ ሙዚቃ ለመሥራት የደፈረው።
ኦሪት ዘኁልቅ 12 ላይ እንዲህ የሚል ቃል ይገኛል ‹‹ሙሴም ኢትዮጵያዩቱን አግብቷልና ባገባት በኢትዮጵያዩቱ ምክንያት ማርያምና አሮን በርሱ ላይ ተናግሩ።እነርሱም በእዉኑ እግዚአብሔር በሙሴ ብቻ ተናግሯልን፧ በእኛስ ደግሞ የተናገረ አይደለምን አሉ እግዚአብሔርም ሰማ…›› ሙሉው ቃል ማንበብ ይቻላል።
ዮቶር የሙሴ አማት፤ የኢትዮጵያዊትዋ የሲጳራ አባት ነው፡፡ ሙሴ እብራዊያንን ከግብጽ ባርነት ለማላቀቅ አምላክ ሲመርጠው፤ ወደ ምድያም ምድር ተሰድዶ ለ40 ዓመታት ኖሯል፡፡ ሙሴ በዚያም ሳለ የዮቶርን በጎች ይጠብቅ ነበር፡፡ ዮቶር የምድያም ካህን ሲሆን፤ አብርሃም ከሳራ ቀጥሎ ያገባት ኬጡራ- ከልጅ ልጆች ውስጥ 7ተኛ ትውልድ ምድያም ከሆነው ወገን ነው፡፡ ዮቶርም ልጁን ሲጳራን ዳረለት፡፡ ሁለት ልጆችንም ወለደ፡፡ አልዓዛር እና ጌርሳምን፡፡
ሙሴ ከልጆቹ እና ከሚስቲ ሲጳራ ጋር ወደ ግብጽ ሲመለስ በመንገድ ላይ እግዚአብሔር ሊገድለው የነበረ ሲሆን ሲጳራ ባልጩት አንስታ የልጇን ሸለፈት ከገረዘች በኋላ ሙሴ ከሞት መትረፉንም በኦሪት ዘጸአት 4፡26 ላይ ተጽፎ እናገኛለን፡፡ይህም ኢትዮጵያውያን
ግርዘትን በኦሪት ጊዜም ይፈጽሙ እንደነበር የሚያረጋግጥ ነው።
ካህኑ
ዮቶር ከዘመናት በኋላ የልጅ ልጆቹንና የሙሴን ሚስት (ሲጳራን) ይዞ ሙሴን ሊጎነኘው ሄዷል፡፡ ሙሴም ዕብራዊያንን ይዞ ከግብጽ ምድር ሥለወጣ እና ዮቶርም እግዚአብሔርን ሊያመሰግን በተገናኙበት ጊዜ፤ ሙሴ በዕብራዊያንን ላይ ተስፋ ቆርጦ እና ለማስተዳደርም አስቸግረውት ሲሰቃይ፤ ሕዝብን የማስተዳደርን ጥበብ፣ ዘዴ እና ሥልጣኔ ዮቶር አስተምሮታል፡፡
ሕዝብን የማስተዳደር ጥበብ ግሪካዊያን የዲሞክራሲን ጽንሰ ሐሳብ ከመስበካቸው በፊት ከብዙ መቶ ዓመታት በፊት መሆኑን ስናስብ ዮቶር የቀደምት ሥልጣኔ መምሕር እና የጥብብ ሰው እንዲሁም በእምነቱን በኩል ካህን የነበረ ታላቅ ሰው ነው!
ሕዝብን የማስተዳደር ጥበብ
1.መሪው በእግዚአብሄር ፊት ለሕዝቡ ይቆማል
2 ሥርዓቱንም ሕጉንም ያስተምራል፤ ያሳያል
3. መሪውም ከሕዝቡ አዋቂዎችን ይመርጣል፤ (እግዚአብሔርን የሚፈሩትን፤ የታመኑትን፤ የግፍንም ረብ የሚጠሉትን፤) እነርሱንም አለቃ አለቃ ድርጎ መምረጥ
4.በሕዝብ ላይ ይፈርዳሉ፤ ከዚሕ የበለጠውንም ወደ መሪው ይወስዱታል፤ ለመሪውም ሸክሙን ያቀሉለታል…ዮቶር ይሕንን ሥርዓት ለሙሴ አስተማረው፡፡
2 ሥርዓቱንም ሕጉንም ያስተምራል፤ ያሳያል
3. መሪውም ከሕዝቡ አዋቂዎችን ይመርጣል፤ (እግዚአብሔርን የሚፈሩትን፤ የታመኑትን፤ የግፍንም ረብ የሚጠሉትን፤) እነርሱንም አለቃ አለቃ ድርጎ መምረጥ
4.በሕዝብ ላይ ይፈርዳሉ፤ ከዚሕ የበለጠውንም ወደ መሪው ይወስዱታል፤ ለመሪውም ሸክሙን ያቀሉለታል…ዮቶር ይሕንን ሥርዓት ለሙሴ አስተማረው፡፡
ካህኑ ዩቶር ኢትዮጵያውያን የሰው ልጅ ስልጣኔ ምንጭ መሆናቸው አስረጂ የሚሆን ታላቅ አባት ነበር።የቴዲ አፍሮ ዜማ ይቀጥላል
…የማንነት የእምነቴን ማዕተብ
(ዜግነቴን ሳሰላስል)
ለካ አፍሪካውነቴ ስቸዋለው
(ዜግነቴን ሳሰላስል)
ውየ አድሬ ስጀመር ማሰብ
(ዜግነቴን ሳሰላስል)
ብርድ አይሞቅም በጋ አይበርድም
(ዜግነቴን ሳሰላስል)
ማንነት ህያው ነው አይለወጥም ኦላ!!
ዜግነቴ ሳፈላልግ
እግሬ ሲዞር ባቋራጩ
ለካ ቤቴ እኔ አፍሪካ ነው
ቤቴ አባይ ላይ ነው
የዮቶር ልጅ ርሥቱ
አባይ ሆኖ ጣና ዳር ቤቱ
ጥበብ ርቄ ሥቀዳ
እንዴት ልሁን ለወንዜ ባዳ ?
ጠምቶኝ ተኛሁ አባይ ዙሪያ
ከሠው መጀመሪያ
ነቅቼ። ኦላ!!
አባይ ሆኖ ጣና ዳር ቤቱ
ጥበብ ርቄ ሥቀዳ
እንዴት ልሁን ለወንዜ ባዳ ?
ጠምቶኝ ተኛሁ አባይ ዙሪያ
ከሠው መጀመሪያ
ነቅቼ። ኦላ!!
የሁሉም ነገር መጀመርያ የሆነቺው ኢትዮጵያ አፍሪካ ይህንን ዕውነታ የሚያውቁ ምዕራባውያን
እውነታው ለዘመናት ደብቀውት የኢትዮጵያውያን አፍሪካውያን
ማንነት ለመቀበር ሲሞክርይ ኖሮዋል።ይህ በጊዜው መልስ የሚያገኝ ጉዳይ ነው የኛ ማንነታችን በማወቅ ወደ እውነታው መጓዝም ይጠይቃል።
ዜግነቴ ሳፈላልግ
እግሬ ሲዞር ባቋራጩ
ለካ ቤቴ እኔ አፍሪካ ነው
ቤቴ አባይ ላይ ነው
አባይ ኦሪት ዘፍጥረት
2፡10-14 ላይ ከ አራቱ ታሪካዊ የሆኑ ወንዞች ውስጥግዮን ወይም አባይ የኢትዮጵያ ምድር ከቦ ኤደን ገነት መሆንዋ አረጋግጧል።ሌሎቹ
የተጠቀሱት ወንዞች ወርቅና የከበረ ድንጋይ ያላቸው መሆኑ ሲገልጽ ጤግሮስና ኤፍራጦስ ይፈሳሉ ይላል እንጂ እንደ አባይ ያጠጣሉ አላለም።ስለዚ
አዳም ኢትዮጵያዊ ለመሆኑ በቂ ማረጋገጫ ነው።ታድያ መነሻችን ጥለን ምዕራባውያን መከተል ምን ይሉታል፧ ኢትዮጵያዊነት ታላቅ ማንነትና
ክብር ነውና የአባቶቻችን እምነት በመልበስ ወደ እውነተኛው ማንነታችን በተግባር እንመለስ።
ህዳር 7, 2008 ዓመተ ምሕረት
መቐለ